Yekin Menged Media and Communication plc

  • Home
  • Yekin Menged Media and Communication plc

Yekin Menged Media and Communication plc event organization, digital marketing, designing and printing, advertising & promotion, media relations, audio-video production,

❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤  ሽራፊ ቀለማት ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤እንደ መግቢያየእኔ ትውልድ ከአሁኑ ትውልድ ጋር/ ከልጆቼ ትውልድ ጋር ማለቴ ነው/ ሲነጻጸር ብዙ የቀለማት ዓይነቶችን ለመረዳት ሩቅ ነበር ብ...
13/03/2024

❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ ሽራፊ ቀለማት ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

እንደ መግቢያ
የእኔ ትውልድ ከአሁኑ ትውልድ ጋር/ ከልጆቼ ትውልድ ጋር ማለቴ ነው/ ሲነጻጸር ብዙ የቀለማት ዓይነቶችን ለመረዳት ሩቅ ነበር ብል አልተሳሳትኩም። በአዲስ አበባ ተወልዶ እንዳደገ አንድ ወጣት ማለቴ ነው። ምናልባት ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ያሉ የዕድሜ እኩዮቼ ለቀለማት ከእኔ የተሻለ ቅርብ ሳይሆኑ ይቀራሉ? በትምህርት ቤት ከሚያገኙት ጥቂት ግንዛቤ ባለፈ ቢያንስ የአካባቢያቸው ማኅበረሰብ አለባበስ ደመቅ ደመቅ ያሉ ቀለማት ያላቸው አልባሳት የሚጠቀሙበት አካባቢዎች ከብዙ ቀለማት ጋር ለመተዋወቅ የተሻሉ ናቸው። ለምሳሌ እንደ ሐረሪ ዓይነት ከተማ ነዋሪዎች እዚህ ላይ ማንሳት እንችላለን።
ሁላችንም ግን እንደ በልጅነታችን ይነስም ይብዛ ስለመሠረታዊ ቀለማት ዓይነቶች ተምረናል። ጥቂቶቻችን ደግሞ ጠለቅ ያለ የቀለማትን ንድፈ ሐሳብ ዘግይተንም ቢሆን አውቀናል። የሥራ ጠባያችን ከቀለማት ጋር ቅርብ ስለሚያደርገን ማለት ነው። ቀለማት ከቀለምነታቸው ባለፈ የቀለማትን ንድፈ ሐሳብ /ቲዮሪ/ ማወቅ በአካባቢያችን ያሉትን ዓለማት ለመገንዘብ ብቻ ሳይሆን ጥሩ ጥምረት ያለው ንድፍ / ቅንጅት ለመፍጠር በእጅጉ ይጠቅማል ይላሉ ባለሞያዎቹ። ቢያንስ ቢያንስ የመኖሪያ ቤታችንን እና የሥራ ቢሯችንን በአግባቡ ለማስዋብ እንገለገልበታለን በማለት።
በዚህ መጣጥፌ የቀለም ንድፈ ሐሳብ ምንድነው? የቀለም ንድፈ ሐሳብ ለምን ወሳኝ ይሆናል? የቀለም ሞዴል ዓይነቶች እና በሕይወታችን ቀለማትን የበለጠ ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም እንዴት እንደምንችል በሦስት ክፍሎች ከፍለን በዝርዘር እንመለከታለን።

ክፍል አንድ
ቀለም ምንድነው?
የቀለምን ትርጉም በአግባቡ ሳናውቅ በቀለማት ዙሪያ ግን ብዙ ጊዜያችንን እናሳልፋለን። ዋናው ቁምነገር ግን ቀለም አመለካከት/ እይታ ነው። ይህንን የቀለም ትርጉም ስንቶቻችን ቀድመን አውቀናል? ዓይኖቻችን የሆነ ነገር አይተው መልዕክቱን ወደ አእምሯችን ይልኩታል። አእምሯችን ደግሞ ቀለሙ ምን እንደሆነ ይነግረናል። ዕቃዎች በተለያየ ዓይነት ሞገድ ባንድ / ዌቭ ሌንግዝ/ ቅንጅት / ሬዲዮ ጋማ ጨረሮች እና ሌሎች/ ብርሃንን ያንጸባርቃሉ። አእምሯችን እነዚህን ሞገድ ባንዶች ቅንጅት ይወስድና ቀለም ወደምንለው ነገር ይተረጉመዋል።
ፖል ክሊ የተባለ ባለሞያ እንዳለው “ ቀለም አእምሯችን እና ዓለማችን የሚገናኙበት ስፍራ ነው።
የቀለም ንድፈ ሐሳብ ምንድነው?
የቀለም ንድፈ ሐሳብ ቀለማትን የመጠቀም ሳይንስና ጥበብ ነው። ይህም የሚያስረዳው የሰው ልጅ ቀለምን እንዴት እንደሚመለከት / አካላዊና ስነልቦናዊ/ እና ቀለማት እንዴት እንደሚዋሃዱ፣ እንደሚዛመዱ እና እርስ በርስ እንዴት እንደሚለያዩ ነው።
ቀለማት የሚያስተላልፉት መልዕክት ወሳኝ ነው።
ለቀለም ንድፈ ሐሳብ የበለጠ ተግባራዊ ትርጉም እንስጠው ካልን የቀለም ንድፈ ሐሳብ የሆነ ቀለም በኅትመት፣ ኮምፒውተር ላይ ሲሳል እና በሌሎች መንገድ ሲወጣ ምን እንደሚመስል የሚገልጽ እና ሁሉን አቃፊ እና ፈርጀ ብዙ ገጽታዎቹ ያሉት የሞያ ዘርፍ ነው።
በቀላሉ የቀለም ንድፈ ሐሳብ ዕለት በዕለት ለምናደርገው ነገር የሆነ መልክ ያለው ቅርጽ ይፈጥርልናል። ነገር ግን ሁል ጊዜ ሙሉ ለሙሉ መገንዘብ ላንችል ወይም በዝርዘር ለማስረዳት አግባብ ያላቸው ቃላት ላናገኝ እንችላለን።
በመሠረቱ የቀለም ንድፈ ሐሳብ ለተስማሚ ንድፎች እና ለአውዱ የሚሆኑ ቀለም ቅንጅቶች የሚጠቅሙ ቀለማትን በመምረጥ የሚያገለግል ምርጥ ተሞክሮዎች ስብስብ ነው።
ያም የተወሰኑ የቀለም ውኁዶች ለሰው ልጅ ዓይን እና በአስፈላጊው ሥፍራ የተስማማና የበለጠ ሳቢ የመሆን ሐሳብ ነው።
የቀለም ንድፈ ሐሳብ ለምን በጣም ጠቃሚ ሆነ?
በዕለት ተዕለት ኑሯችሁ ምንም ያህል ከቀለም ጋር የተገናኘ ሥራ የምትሠሩ ቢሆን የቀለም ንድፈ ሐሳብ አሠራር ግንዛቤ መያዝ ሁልጊዜ ቅርብ ነው። ቀለም ለብራንዲንግና ማርኬቲንግ ሥራ አንድን ምርት እንዲታወቅና ትኩረት እንዲስብ ለማድረግ ወሳኝ ነው።
ስለ ብራንድ መለያውም ፈጣን መልዕክት ያስተላልፋል። ብራንዲንጋችሁ ብሩኅ፣ ሳሳ ያለ ቫዮሌንት ከሆነ ከደማቅ ጥቁር ቀለም ብራንዲንግ በጣም የተለየ መልዕክት ያስተላልፋል።
ዛሬ ላይ በጣም ፈጣን ጊዜያት ላይ እንገኛለን። እናም የምናስተላልፈው መልዕክት በፍጥነት እና ውጤታማ በሆነ መንገድ መተላለፍ አለበት። ወደ አእምሮ የሚተላለፈው መልዕክት 90% የሚታይ ከሆነ የቀለም ንድፈ ሐሳብ ትክክለኛውን መልእክት ለማስተላለፍ / ለብራንዲንግ እና ማርኬቲንግ/ እና ሰዎች ላይ ተጽእኖ ለማሳደር / ለሽያጭ/ አስፈላጊ ነው።
ለዚህ ነው የቀለም ስነልቦና / እና የእያንዳንዱ ቀለም ትርጉም/ ወደ ጎን መተው የለበትም የሚባለው።
ነገር ግን እንደ አንድ ሥራ ፈጣሪ አንድ ምርት ብታመርቱና ማሸጊያ ካርቶኑን ሙሉ ቀይ ቀለም በመለቅለቅ ቀይ ቀለም ለኮካኮላ ስኬታማነት ያደረገውን ታላቅ አስተዋጽኦ ለእናንተም እንዲሠራ መጠበቅ የለባችሁም። ለዚያ ዓይነት ስኬት እስከ አሁን ስለቀለማት ካነሳነው የበለጡ ሌሎች ተጨማሪ ያላነሳናቸው ጉዳዮች አሉት። ምንም እንኳን በማርኬቲንግ እና ሽያጭ ሥራ ላይ የተሰማራችሁ ባትሆኑም የቀለም ንድፈ ሐሳብ ለማንም ሰው ምንጊዜም አስፈላጊ ነው። የመሳል ወይም የመንደፍ ፍላጎት ካላችሁ ደግሞ ስዕላችሁ እና ንድፋችሁ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን እና ለቀለም ያላችሁ እይታን ማሳደገድ እንድትችሉ ይረዳችኋል።
እናም ሰዓሊ፣ ዲዛይነር ወይም የፈጠራ ሰዎች ባትሆኑም ስለ ቀለም የበለጠ ካወቃችሁ በሁሉም የሕይወታችሁ ዘርፍ በአግባቡ መናገር እንድትችሉ ያግዛችኋል።
የቀለም ሞዴሎች
ሦስት ዓይነት የቀለም ሞዴሎች አሉ። ስለእያንዳንዳቸው ልታውቋቸው የሚገቡ ነገሮች እነሆ።
አር ጂ ቢ /ቀ ግ ብ / ቀይ አረንጓዴ ሰማያዊ - ሬድ ግሪን ብሉ


የምናያቸው ቴሌቭዥኖች፣ ፕሮጀክተሮች እና የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎች ስክሪኖች አር ጂ ቢ ሞዴልን እና ቀይ፣ አረንጓዴ እና ሰማያዊ ቀለማትን እንደ አንደኛ መደብ ቀለማት / ፕራይመሪ ቀለማት/ ይጠቀማሉ።
አር ዋይ ቢ ሞዴል ቀለማትን ለመቀላቀል ሲያገለግል አር ጂ ቢ ሞዴል ደግሞ ብርሃንን በመቀላቀል ሌሎች ቀለማትን ለመፍጠር ይጠቀማል።
ይህም አር ጂ ቢን ከመቀነሻ ይልቅ መጨመሪያ ቀለም ሞደል ያደርገዋል። በነጭ ቀለም ጀምሮ ቀለማትን ከእርሱ ላይ ቀንሶ ከመውሰድ ይልቅ መጨመሪያ ነው። አር ጂ ቢ በጥቁር በመጀመር እና የተለያየ ጥንካሬ ያላቸውን ቀይን አረንጓዴን እና ሰማያዊ ብርሃን ምንጮችን ይጨምራል።
ብዙ ብርሃን በጨመራችሁ ቁጥር ቀለሙ የበለጠ ብሩኅ እየሆነ ይሄዳል። ሁሉንም /ሦስቱንም ቀለማት ብርሃን በእኩል መጠን ብናዋህዳቸው ንጹህ ነጭ ብርሃን እናገኛለን።

ሲ ኤም ዋይ ኬ ሲያን ማጄንታ የሎ እና ኪ ወይም ጥቁር

ማንኛውም የታተመ ነገር ላይ የምታዩት የቀለም ሞዴል ሲ ኤም ዋይ ኬ ነው። ይሀም እንደ አር ጂ ቢ ሞዴል ተመሳሳይ የቀለም አማራጮችን ይይዛል። ነገር ግን እንዳትሳሳቱ እነዚህ ሑለት የተለያዩ የቀለም ሞዴሎች ናቸው።
ከአር ጂ ቢ በተለየ ሲ ኤም ዋይ ኬ ቀናሽ ውኅድ ቀለም ሞዴል ነው። ቀለማት የሚታተሙት በነጭ ወረቀት ላይ የማተሚያ ቀለምን በመጨመርና ብርሃንን በመቀነስ ነው።
እናም ከአር ጂ ቢ በተለየ ሲ ኤም ዋይ ኬም የተለያዩ የመጀመሪያ መደብ / ፕራይመሪ ቀለማትን ይጠቀማሉ። ምክንያቱም ሲያን፣ ማጄንታ፣ ቢጫ እና ጥቁር ማተሚያ ፕሪንተሮች ወረቀት ላይ ብዙ ዓይነት ቀለማትን ያትማሉ።
አስታውሱ የኅትመት ውጤቶችን ለማምረት ሲ ኤም ዋኬን ብትጠቀሙም እንኳን በአር ጂ ቢ ምትክ ሲ ኤም ዋይ ኬን የድርጀት አርማችሁን ማናቸውም ኤሌክትሮኒክ ምስል ማሳያ ስክሪኖች ላይ አዘጋጅታችሁ ብትለጥፉት ቀለሙ ትክክል ላይመጣ ይችላል።
እነዚህን ሑለት ዓይነት ሞዴሎች የት ቦታ መጠቀም እንዳለባችሁ መለየት ጠቃሚ ነው።
አር ዋይ ቢ ሬድ የሎ ብሉ

ይህ የቀለም ሞዴል ምናልባት ሕጻናት ሳለን ትምህርት ቤት ቀለማትን በጣታችን ስንቀላቅል የተማርነው ነው።
ዛሬ ላይ ባሕላዊ የቀለም ንድፈ ሐሳብ በመባል የሚጠራና በአርቲስቶች እና ዲዛይነሮች አሁን ድረስ አገልግሎት ላይ በመዋል ቅቦችን ለመቀላቀል እና የቀለም አማራጭ ትሪዎችን ለመፍጠር የሚያገለግል ነው። የመጀመሪያ መደብ ቀለማቱም ቀይ ብጫ እና ሰማያዊ ናቸው።
ይህ የመቀነስ ቀለም መቀየጫ ሞዴል ነው። ይህም ማለት በነጭ ሸራ ወይም ወረቀት ላይ ትጀምሩና በመቀጠል በወረቀቱ ወይም ሸራው መልሶ የሚተፋውን የሚንጸባረቀውን ብርሃን ለመቀነስ ቀለም የመጨመር ሂደት ነው።
አስታውሱ ነጭ የሌሎች ቀለማት ውኅድ ቀለም ነው።

የቀለም ዊል ንድፈ ሐሳብ
በ1666 ሰር አይዛክ ኒውተን የቀለማት ጅረትን በክብ ቀለማት ላይ አስቀምጦት ነበር። አሁን ላይ ይህንን ክብ ቀለማት የቀለማት ዊል እንለዋለን። ይህም 12 መሠረታዊ ቀለማት አሉት።
የሚሠራውም ከሦስት የመጀመሪያ መደብ ቀለማት፣ ሦስት ሑለተኛ መደብ ቀለማት እና ስድስት ሦስተኛ መደብ ቀለማትን በግራዲየንት ዊል ለመረዳት ቀላል በሆነ መንገድ በማስቀመጥ አንዱ ከሌላው ጋር ያለውን ዝምድን ያሳያል።
ዛሬ ላይ ሦስት የቀለም ዊሎች አሉ። ለእያንዳንዱ የቀለም ሞዴል አንድ አንድ ይኖራቸዋል ማለት ነው። ነገር ግን በቀለም ዊሉ ላይ ያለው በቀለማት መሀከል ያለው ዝምድና ምንም ዓይነት የቀለም ዊል ብትጠቀሙ ተመሳሳይ ነው።
አርቲስቶችና ዲዛይነሮች የቀለማትን ዊል ማናቸውንም በቀለም የሚሠሩ ፕሮጀክቶችን ሲያዘጋጁ ይመርጧቸዋል። ቀለማት አንዳቸው ከሌሎች ጋር ያላቸውን ዝምድና ለመረዳት የቀለም ዊልን በአግባቡ መረዳት ይፈልጋል።
አንደኛ ሑለተኛ እና ሦስተኛ መደብ ቀለማት
የቀለም ዊል በአንደኛ ሑለተኛና ሦስተኛ ቀለማት የተደራጀ ነው።
አንደኛ መደብ ቀለማት የቀለም ዊል ሦስቱ ዋና መገንቢያ ክፍሎች ናቸው። ቀለማቱ ሌሎች የቀለማት ውኁዶችን በማቀላቀል የማይፈጠሩ ናቸው።
ቀይ
አረንጓዴ
ሰማያዊ
ሑለተኛ መደብ ቀለማት ሑለት የመጀመሪያ መደብ ቀለማትን በእኩል መጠን በማቀላቀል የሚገኙ ናቸው።
ቀይ + ሰማያዊ = ማጄንታ
አረንጓዴ + ቀይ = ብጫ
ሰማያዊ + አረንጓዴ = ሲያን
ሦስተኛ መደብ ቀለማት ሑለተኛ መደብን እና አንደኛ መደብ ቀለማትን በመቀላቀል አዲስ የቀለም ውኁድን መፍጠር ያስችላል።
አረንጓዴ + ብጫ = ቻርተርዩዝ
አረንጓዴ + ሲያን = ስፕሪንግ ግሪን
ሰማያዊ + ሲያን = አዙሪ
ሰማያዊ + ማጄንታ = ሮዝ
ቀይ + ብጫ = ብርቱካናማ
ለቀለም ንድፈ ሐሳብ ማወቅ ምን ይጠቅማል? ለምትሉ የዓለምን ቀለማት በሙሉ በአግባቡ ለመጠቀም ሁሉንም ዓይነት የቀለም አማራጮች መጠቀም ለመቻልና ይህንንም የተለያዩ የቀለም ውኁዶች እንዴት እንደሚፈጠሩ ለማወቅ ነው። ይህንን ሳይረዱ መሥራት ሆነ የተሠራውን ነገር በአግባቡ መረዳት ስለማይቻል ነው።
የቀለም ዊልን በደንብ ከሰለጠናችሁ በኋላ ቀጣዩን ደረጃ ደግሞ ስለ ሁ፣ ቫልዩ እክሮማ ማወቅ ይሆናል።
እርሱን ደግሞ በክፍል ሑለት እንመለስበታለን።

Address

Lideta Sub City, Near Saint Lideta Church
Addis Ababa
1110

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yekin Menged Media and Communication plc posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yekin Menged Media and Communication plc:

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Event Planning Service?

Share


You may also like