MELKE DAWIT

MELKE DAWIT Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from MELKE DAWIT, Performance & Event Venue, hawassa, Awassa.

15/05/2023

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች የሲቢኢ ብር አገልግሎትን ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡
=================
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮርፖሬት ኮሙኑኬሽን ዳይሬክተር አቶ አልሰን አሰፋ ዛሬ እንዳስታወቁት ባንኩ ዘመናዊ፤ ለአጠቃቀም ቀላልና ፈጣን የሆነውን የሲቢኢ ብር አገልግሎትን ከነገ ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ተግባራዊ ማድረግ ይጀምራል፡፡

ከሚያዚያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በተጀመረው በዚሁ አገልግሎት መልካም ውጤት መገኘቱን የጠቆሙት አቶ አልሰን፤ በርካታ ደንበኞችም የሲቢኢ ብር የዲጂታል ክፍያ ዘዴን በእጅ ስልኮቻቸው አማካኝነት በመጠቀም የነዳጅ ግብይት በመፈፀም ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የተገኘውን ልምድ መሰረት በማድረግ በአገር አቀፍ ደረጃ ከነገ ጀምሮ ለሚተገበረው ዲጂታል የነዳጅ ግብይት ባንኩ ዝግጅቱን ማጠናቀቁንም ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

ደንበኞች ነዳጅ ለመቅዳት የሲቢኢ ብር መተግበሪያን በእጅ ስልኮቻቸው ላይ ጭነው ወይም *847 # ላይ በመደወል አገልግሎቱን መጠቀም የሚችሉ ሲሆን፤ በተጨማሪም ለዚሁ አገልግሎት ባንኩ ያበለጸገውን ‹‹ነዳጅ›› የተሰኘ የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያን በመጫን ሊጠቀሙ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ሁሉንም መተግበሪያዎች ደንበኞች በነጻ ከአፕ ስቶር እና ፕለይ ስቶር ላይ ማውረድ እና መጫን የሚችሉ መሆኑንም የኮርፖሬት ኮሙኑኬሽን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡

የባንኩ ባለሙያዎችም በሁሉም የነዳጅ ማደያዎች በመገኘት ለደንበኞችና ለነዳጅ ማደያ ሰራተኞች አስፈላጊውን እገዛ ስለሚሰጡ ደንበኞች አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉላቸውም አቶ አልሰን ጠይቀዋል፡፡

15/05/2023
15/05/2023

ነዳጅ ማደያ ሲደርሱ በሲቢኢ ብር በቀላሉ የነዳጅ ክፍያዎን ይፈጽሙ፡፡
የባንኩ ባለሙያዎች ሙያዊ ድጋፍ አብርዎት አለ ፡፡
=================================

በሲቢኢ ብር የነዳጅ ክፍያን መፈጸም ቀላል ነው!
ሲቢኢ ብር ባሉበት ሁሉ አለ!

03/09/2022

የውጪ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ መግባት ለኢትዮጵያ በረከትን ወይስ ክስረትን ያመጣ ይሆን?
****
ኢትዮጵያ ልክ እንደሌሎቹ ከሰሀራ በታች እንደሚገኙ ሀገራት ለረጅም ዘመን በሯን ለውጪ ሀገር ባንኮች ዝግ አድርጋ ቆይታለች። ይሁንና የዓለም የንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል የፋይናንስ ዘርፉን ለውጭ ባንኮች ክፍት እንድታደርግ ከWTOም ሆነ ከዓለም ባንክ ጫና ሲደረግባት ሰንብታለች።

በመጨረሻም ዛሬ፣ ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም. በሯን ለውጪ ባንክ ለመክፈት ታሪካዊ ውሳኔን ወስናለች።

የውጪ ባንኮች በረከት ወይስ ክስረትን ይዘውልን ይመጡ ይኾን?
*****
ይሄንን በተመለከተ በራቸውን ለውጪ ባንኮች ክፍት ያደረጉ ከሰሀራ በታች በሚገኙ ሀገራት ላይ የተደረጉ ብዙ ጥናቶች የሉም። ሀገራት ለውጪ ሀገር ባንኮች በራቸውን መክፈት ይኖርባቸዋል ወይስ አይኖርባቸውም የሚለው ሀሳብም ለክርክር ክፍት ነው።

ሀገራት ለውጪ ባንኮች በራቸውን መክፈት አለባቸው የሚሉ ወገኖች የውጭ ሀገር ባንኮች መግባት:-

➡️ ወደ ሀገር ቤት የካፒታል ፍስሰት እንዲኖር ያደርጋል
➡️የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎች ወደ ሀገር እንዲገቡ ያደርጋል
➡️የተሻሻሉ አስተዳደር፣ የሠራተኛ እና የስልጠና ወደ ሀገር እንዲገባ ያደርጋል
➡️ውድድርን በመፍጠር የባንኮችን አፈጻጸም ያሻሽላል፣ ባንኮች ወጪ ቁጠባ ላይ እንዲሰሩ ያደርጋል
➡️ባንኮች ዘመናዊ የስጋት አስተዳደሮችን እንዲተገብሩ ያደርጋሉ
➡️የስራ እድል ለዜጎች ይፈጥራሉ፣ በብድር ላይ የሚከፈሉ የወለድ ምጣኔ እንዳይበዛ ያደርጋሉ፣ ለቆጣቢዎች የተሻለ ወለድ ይከፍላሉ። በእዚህም ያልተጋነነ ትርፍ ያገኛሉ

ሲሉ ይሞግታሉ።

በአንጻሩ ሀገራት በራቸውን ለውጪ ባንኮች መክፈት የለባቸውም የሚሉ አካላት የሚከተሉትን የመከራከሪያ ነጥቦች ያቀርባሉ...

➡️ወደ ሀገር ውስጥ ከሚያስገቡት ካፒታል ይልቅ ይዘው የሚወጡት ካፒታል ይልቃል (Capital Flight)
➡️ በገቡበት ሀገር የሆነ የኢኮኖሚ ቀውስ ቢፈጠር ዘግተው ገበያውን ለቅቀው ስለሚወጡ ኢኮኖሚ ላይ ተጨማሪ መረበሽን ይፈጥራሉ
➡️ የብድር አቅርቦቶቻቸውና አገልግሎቶቻቸው ሀብታም-ተኮር መሆናቸው ሀብት ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ለሁሉም እንዳይዳረስ ተግዳሮትን ይፈጥራሉ
➡️ትርፋቸውን ከሀገር ሲያስወጡ /Profit Repatriation/ የውጪ ምንዛሪ እጥረቱ ላይ ቤንዚን ያርከፈክፋሉ
➡️ የሀገር ውስጥ ባንኮችን አዳክመው ከገበያ ያስወጣሉ
➡️በእጅ አዙር የምእራባውያን የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈፀሚያ በመሆን ፖለቲካውን ሊረብሹ ይችላሉ

እንዲሁም ሌሎች ነጥቦችን በማንሳት ይከራከራሉ።

ያም ሆነ ይህ ኢትዮጵያ በሯን ለውጭ ሀገራት ከፍታለች። በረከታችን ይበዛ ወንድ የውጪ ባንኮችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሊጠናከርና ጥርስ ሊኖረው ግድ ይላል። ጠንካራ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች ሊወጡ ይገባል። ከእዚህ በተጨማሪ በተበጣጠቀ ካፒታል የሚወዳደሩ 30 የሚደርሱ ባንኮች ሊዋሀዱ (በMerger and Acquisition) እና ጠንክረው ሊጠብቁ ግድ ስለሚላቸው በቅርቡ ብሔራዊ ባንክ የባንኮችን የካፒታል አቅም (Capital Requirement) አይነኬ አድርጎ ይቆልላል ተብሎ ይጠበቃል። ትልልቆቹ አሳዎች ትንንሾቹን መብላታቸው አይቀሬ ይሆናል። ስለሆነም እራሳችንን አጠንክረን ከክስረት ይልቅ በረከትን ለማፈስ መዘጋጀቱ የእኛ ድርሻ ይሆናል።

ይሁንና ኢትዮጵያ በሯን ስለከፈተች ትልልቅ ባንኮች (A class Banks) በቅርቡ ግር ብለው ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ይገባሉ ተብሎ አይታሰብም። ውድድሩ ውስጥ ባንኮች በተትረፈተረፈ ትርፍ /Profit Bonanza/ መራጨታቸው የሚያከትምበት ዘመን እየመጣ ስለሆነ በባንኮቹ የአክሲዮን ድርሻ ያላቸው ባለሀብቶችም የቀነሰ ዲቪደንድ ለመቀበል መዘጋጀት ይኖርባቸዋል።

via Tilahun Girma Ango

28/08/2022

ምርጫውን አቶ ኢሳያስ ጅራ አሸነፉ❗️

⚡️የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት ለመምራት በአብላጫ ድምፅ አቶ ኢሳያስ ጅራ መመረጣቸውን ጉባኤ ይፋ አድርጓል። አቶ ኢሳያስ ጅራ ለሁለተኛ የስራ ዘመን ፌዴሬሽኑን ለመምራት በሀላፊነት ተመርጠዋል።

🦁• •🦁

27/08/2022
08/08/2022

✓✓ KEYNESIAN ECONOMICS

Keynes argued that inadequate overall demand could lead to prolonged periods of high unemployment. An economy’s output of goods and services is the sum of four components: consumption, investment, government purchases, and net exports (the difference between what a country sells to and buys from foreign countries).

Any increase in demand has to come from one of these four components. But during a recession, strong forces often dampen demand as spending goes down.

For example, during economic downturns uncertainty often erodes consumer confidence, causing them to reduce their spending, especially on discretionary purchases like a house or a car.

This reduction in spending by consumers can result in less investment spending by businesses, as firms respond to weakened demand for their products.

This puts the task of increasing output on the shoulders of the government. According to Keynesian economics, state intervention is necessary to moderate the booms and busts in economic activity, otherwise known as the business cycle. T here are three principal tenets in the Keynesian description of how the economy works:

1. Aggregate demand is influenced by many economic decisions—public and private. Private sector decisions can sometimes lead to adverse macroeconomic outcomes, such as reduction in consumer spending during a recession. These market failures sometimes call for active policies by the government, such as a f iscal stimulus package.

2. Changes in aggregate demand, whether anticipated or unanticipated, have their greatest short-run effect on real output and employment, not on prices. Keynesians believe that, because prices are somewhat rigid, fluctuations in any component of spending—consumption, investment, or government expenditures—cause output to change.

3. Prices, and especially wages, respond slowly to changes in supply and demand, resulting in periodic shortages and surpluses, especially of labor.

You can now follow Grand Economics Society on Instagram with the link below

https://instagram.com/grand_economics_society?utm_medium




እንኳን ደስ አለን 3ተኛ ዙር የውሃ ሙለት ተጠናቋል
31/07/2022

እንኳን ደስ አለን 3ተኛ ዙር የውሃ ሙለት ተጠናቋል

29/07/2022

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 27 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር አተረፈ።
Commercial Bank of Ethiopia
• የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2014 (2021/22) በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ በአዲሱ የዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ የ
መሰብሰቢያ አዳራሽ በማካሄድ ላይ ነው፡፡
=================================================================
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2014 (2021/22) በጀት ዓመት 154.9 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ የተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ ጠቅላላ የተቀማጭ ገንዘቡን 890.1 ቢሊዮን ብር ማድረሱን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ አስታውቀዋል፡፡
የ2014 (2021/22) በጀት ዓመት የሥራ እቅድ አፈጻጸም ግምገማውን በማካሄድ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአጠቃላይ ከእቅድ በላይ ወይም ተቀራራቢ አፈጻጸም ያስመዘገበበት ዓመት መሆኑን የባንኩ ፐሬዚዳንት ካቀረቡት ሪፖርት ለመረዳት ተችሏል፡፡
ባንኩ በበጀት ዓመቱ 27 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ትርፍ ያገኘ ሲሆን ይህም ከእቅዱ 16.3 በመቶ፣ ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ደግሞ የ43 ነጥብ 9 በመቶ ብልጫ እንደሚያሳይ አቶ አቤ ገልጸዋል።
ባንኩ 179.2 ቢሊዮን ብር ብድር ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች መስጠቱን ያስረዱት አቶ አቤ፣ 120.6 ቢሊዮን ብርም ከተሰጡ ብድሮች መሰብሰብ መቻሉን አስረድተዋል፡፡
የውጭ ምንዛሪ ግኝትን በተመለከተ ከተለያዩ ዘርፎች 2.6 ቢሊዮን ዶላር የተገኘ ሲሆን፣ በመንግስት ትኩረት ለተሰጣቸው ለተለያዩ የገቢ እቃዎች እና ለሌሎችም 7.7 ቢሊዮን ዶላር ባንኩ መክፈሉንም ነው አቶ አቤ የገለጹት፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ሀብት 1.2 ትሪሊዮን ብር መድረሱንም አቶ አቤ ካቀረቡት ሪፖርት ለመረዳት ተችሏል፡፡
የባንኩን አገልግሎት ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለማዳረስ በሚደረገው ጥረት በበጀት ዓመቱ 124 አዳዲስ ቅርንጫፎች የተከፈቱ ሲሆን፣ የባንኩ አጠቃላይ የቅርንጫፍ ብዛትም 1824 ደርሷል፡፡

24/07/2022

THE OPPORTUNITY SET: CONSUMPTION, PRODUCTION,
AND INVESTMENT CHOICE
So far, we have examined the trade-offs that economic actors (e.g., consumers, companies,
investors) are willing to make. In this section, we recognize that circumstances almost always
impose constraints on the trade-offs that these actors are able to make. In other words, we
need to explore how to model the constraints on behavior that are imposed by the fact that
we live in a world of scarcity: There is simply not enough of everything to satisfy the needs and
desires of everyone at a given time. Consumers must generally purchase goods and services
with their limited incomes and at given market prices. Companies, too, must divide their
limited input resources in order to produce different products. Investors are not able to choose
both high returns and low risk simultaneously. Choices must be made, and here we examine
how to represent the set of choices from which to choose.

የሚነዝር ስሜት 💚💛❤በፍቅርና በትብብር ሮጠው፣ ከነጠላ ስኬት ይልቅ የቡድን ውጤትን አስቀድመው በፈጠሩት ተዓምር ሀዘናችን ተሰርዞ በፈገግታ ታጅበናል። የሀገር ኩራታችንን ስለመለሳችሁልን ፈጣሪ...
24/07/2022

የሚነዝር ስሜት 💚💛❤

በፍቅርና በትብብር ሮጠው፣ ከነጠላ ስኬት ይልቅ የቡድን ውጤትን አስቀድመው በፈጠሩት ተዓምር ሀዘናችን ተሰርዞ በፈገግታ ታጅበናል። የሀገር ኩራታችንን ስለመለሳችሁልን ፈጣሪ አብዝቶ ይባርካችሁ፣ ክበሩልን!!

መቸም የዘንድሮው ውድድር ሴቶች የነገሱበት ነው... በጀግናዋ ደራርቱ ቱሉ እየተመሩ፣ ከአራቱ ወርቅ ሦስቱን ያሳኩት ሴት አትሌቶቻችን ናቸው። by mesafint
💚💛❤

እንኳን ደስ አለን
24/07/2022

እንኳን ደስ አለን

23/07/2022

Address

Hawassa
Awassa
MD6423

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MELKE DAWIT posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share


Other Performance & Event Venues in Awassa

Show All