Sami love

Sami love Jesus is my powerful name
https://www.youtube.com/-cg7fm

  Afla
23/04/2024

Afla

15/04/2024

Grace of God
11/04/2024

Grace of God

Grace of god
09/04/2024

Grace of god

❤            ❤=========================== https://www.youtube.com/✍️ ዮሐንስ 8 (John)31፤ ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ፡— እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በ...
31/03/2024



===========================
https://www.youtube.com/

✍️ ዮሐንስ 8 (John)
31፤ ኢየሱስም ያመኑትን አይሁድ፡— እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤
32፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል፡ አላቸው።

✍️ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦
" እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም #ስለ #እኔ #የሚመሰክሩ #ናቸው፤"
(የዮሐንስ ወንጌል 5: 39)

✍️ 2 ቆሮንቶስ 3
14፤ ነገር ግን አሳባቸው ደነዘዘ። ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያ መጋረጃ ሳይወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራልና፤ #በክርስቶስ #ብቻ #የተሻረ #ነውና።
15፤ ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ጊዜ ሁሉ ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል፤
16፤ #ወደ #ጌታ #ግን #ዘወር #ባለ #ጊዜ ሁሉ መጋረጃው ይወሰዳል።

✍️ ብሉይ ኪዳን የአዲስ ኪዳን ጥላ ነውና ወደ አካሉ ወደ ክርስቶስ ካልተተረጎመ ልብን እና አሳብን እንደሚያደነዝዝ ሐዋርያው ጳውሎስ ተናግሯል።

📌ታቦት ምንድን ነው??
==============
ታቦት የሚለው ቃል #ቴብህህ ከሚለው ከዕብራይስጥ ቃል ጋር የሚመሳሰል ሲሆን ትርጉሙም በውስጡ አንዳች ነገር የሚይዝ እንደሳጥን ያለ ማደሪያ ማለት ነው።
በታቦቱ ውስጥም ሶስት ነገሮች ማለትም መና ያለበት የወርቅ መሶብ፣የለመለመችው የአሮን በትር እና የቃልኪዳኑን ጽላት የያዘ ነው።

📌የታቦት አሰራርና አዲስ ኪዳናዊ ትርጉሙ፦
===================
ዘጸአት 25:10-12,
ዘጸአት 37:1-9

✍️ዘጸአት 25
10፤ ከግራር እንጨትም ታቦትን ይሥሩ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን።
11፤ በውስጥና በውጭም በጥሩ ወርቅ ለብጠው፤ በእርሱም ላይ በዙሪያው የወርቅ አክሊል አድርግለት።
12፤ አራት የወርቅ ቀለበቶችም አድርግለት፥ እነርሱንም በአራቱ እግሮቹ ላይ አኑር፤ በአንድ ወገን ሁለት ቀለበቶች፥ በሌላው ወገን ሁለት ቀለበቶች ይሁኑ።
13፤ መሎጊያዎችንም ከግራር እንጨት ሥራ፥ በወርቅም ለብጣቸው።

✍️ ታቦት ከግራር እንጨት የተሰራ ሳጥን ማለት ሲሆን
ይህ #የብሉይ #ኪዳን ታቦት እግዚአብሔር እራሱ ዲዛይኑን አውጥቶ እንዴት መሥራት እንዳለበት ለሙሴ በመናገር እንዲሰራ ያዘዋል፡፡ ዘፀ25፡8-
#ታቦቱ:- ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣
:-ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል፣
:-ቁመቱ አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ነው።
፦ የሚሸከሙትም አራት ሌዋውያን
ናቸው።
ውስጡ እና ውጩ በጥሩ ወርቅ ተለብጧል።
እንዲሁም ታቦቱን የሚከድን የስርየት መክደኛ አለ በስርየት መክደኛው ላይም ሁለት የክብር ኪሩቤሎች ከተቀጠቀጠ ወርቅ ተሰርተው ፊት ለፊት ይቀመጣሉ እግዚአብሔር በሁለቱ ኪሩቤሎች መካከል ተቀምጦ ሙሴን ያነጋግራልና ሕዝቡንም ይገናኝ ነበር።
ይህ የብሉይ ኪዳን ታቦት ለእውነተኛው (አማናዊ) ታቦት ለኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ እና ጥላ ነበር።

📌 1) ታቦቱ በውስጥም በውጭም በወርቅ የተለበጠ ነው ወርቅ በመጽሐፍ ቅዱስ መለኮትነትን የሚገልጥ ሲሆን
ኢየሱስ ክርስቶስ #ፍጹም #አምላክ መሆኑን የሚገልጥ ነው።
📌 2) ታቦቱ የሚሰራው ከግራር እንጨት ነው። የግራር እንጨት ለየት የሚያደረገው ባህሪው የሚነቅዝ አለመሆኑ ነው ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ #ፍጹም #ሰው መሆኑን እና ቢገድሉትም ሞቶ ያልቀረውን ሰውነቱን ያሳያል።

✍️ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው (ከሃጢአት በቀር) አምላክነት ሰውነትን ሳያጠፋ ሰውነትም አምላክነትን ሳይውጥ በአንድ አካል ትላንትና ዛሬም ለዘላለምም የሚኖር አማናዊው(እውነተኛው) ታቦታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ነው። ዮሐ 1:14, ቆላ 1:15 ቆላ 2:9 ዕብ 1:3 , ዕብ 13:8........

📌 የብሉይ ኪዳኑ ታቦት ስለክርስቶስ ምሳሌ እና ጥላ ሆኖ አገልግሎ በነብዩ በኤርምያስ ዘመን ፍጻሜ አግኝቶ አልፏል፦
ኤርምያስ 3
16፤.. በዚያ ዘመን፡— የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት፡ ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም፤ ልብ አያደርጉትም፥ አያስቡትምም፥ አይሹትምም፥ ከእንግዲህ ወዲህም አይደረግም።

🤔🤔🤔,አሁን ታቦት የሚባል ነገር ቢኖር እንኳ ከመጽሐፍ ቅዱሱ እውነተኛ ታቦት ጋር የታሪክም የቅርጽም የብዛትም አንድነት እና ግንኙነት እንደሌለው ልብ ልንል ይገባል!!

👉 #ቅርጽ፦
-----------
የብሉይ ኪዳን ታቦት በቅርጹ ትልቅ ሳጥን ሲሆን የስርየት መክደኛ ያለው እና ሁለት መሸከሚያ መሎጊያዎች አሉት።ዘጸ 25:14-15 እኛ ሀገር ውስጥ ያለት ታቦት ተብሎ የሚጠራው ግን አራት ማዕዘን የሆነ ከእንጨት የተሰራ ጠፍጣፋ ጣውላ ነው።

👉 #ብዛትን በተመለከተ፦
--------------------
እግዚአብሔር እንዲሰራ ያዘዘው እና ሙሴም ከግራር እንጨት የሰራው በብዛት አንድ ብቻ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። በእኛ ሀገር ያለው ግን ቁጥሩ በጣም ብዙ ሲሆን በመላ ሀገሪቱ በተለያየ ቦታ እና በተለያየ ስም ተቀርጾ በየ ደብሩ ይገኛል።

📌 በነብዩ በኤርምያስ አፍ እግዚአብሔር ጣኦት እንደሆነ ይናገራልና ፦
--------------------------
#እግዚአብሔር #ግን #እውነተኛ #አምላክ #ነው

📖 ኤርምያስ 10
3፤ የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል።
4፤ በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል።
5፤ እንደ ተቀረጸ ዓምድ ናቸው፡ እነርሱም አይናገሩም፤ መራመድም አይቻላቸውምን ይሸከሙአቸዋል። ክፉ መሥራትም አይቻላቸውምና፥ ደግሞም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉምና አትፍሩአቸው።
6፤ አቤቱ፥ እንደ አንተ ያለ የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው።
7፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ፥ በአሕዛብ ጥበበኞች ሁሉ መካከል በመንግሥታቸውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለሌለ፥ አንተን መፍራት ይገባልና አንተን የማይፈራ ማን ነው?
8፤ በአንድ ጊዜ ሰንፈዋል፥ ደንቍረውማል፤ ጣዖታት የሚያስተምሩት የእንጨት ነገር ብቻ ነው።
9፤ የሠራተኛና የአንጥረኛ እጅ ሥራ የሆነ ከተርሴስ ጥፍጥፍ ብር ከአፌዝም ወርቅ ይመጣል፤ ልብሳቸውም ሰማያዊና ቀይ ግምጃ ነው፥ ሁሉም የብልሃተኞች ሥራ ናቸው።
10፤ እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘላለም ንጉሥ ነው፤ ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን አይችሉም።
11፤ እናንተም፡— ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ እነዚህ አማልክት ከምድር ላይ ከሰማይም በታች ይጠፋሉ፡ ትሉአቸዋላችሁ።
12፤ ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው።

✍️ ኢሳይያስ 34 (Isaiah)
16፤ በእግዚአብሔር መጽሐፍ ፈልጉ አንብቡም፤ አፌ አዝዞአልና፥

✍️ 1 ዮሐንስ 5 (1 John)
21፤ ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።

✍️ ይሁዳ 1 (Jude)
17፤ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤

✍️ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

  this
30/03/2024

this

Grace family 2310 on youtube የ መፃፍ ቂዱስ ጥያቄ እና ማልስ #ዳዊት
19/03/2024

Grace family 2310 on youtube
የ መፃፍ ቂዱስ ጥያቄ እና ማልስ
#ዳዊት

06/03/2024

Dawit fasil minster

02/03/2024

ወድም ዳዊት ፋሲል

21/02/2024

ወንድም #ዳዊት ፋሲል

06/02/2024
29/01/2024

06/01/2024

18/12/2023

04/11/2023

02/11/2023

Grace family

Address

Metu
Jimma

Telephone

+251935586057

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sami love posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share


Other Party Entertainment Services in Jimma

Show All