Ibnu habeshiyi

  • Home
  • Ibnu habeshiyi

Ibnu habeshiyi ኩሉ ሽእን ያታጋያር

25/01/2022
15/01/2022

ያንን ዉብ ያንን ዘንፋላ ጣፋጩን የማር ወለላ

07/08/2021

"አህመድ እና ሰሚራ"....
(ፀሃፊ✍፡ አብዱልጀባር ፋሪስ)

በ... የተዘጋጀ ልብ አንጠልጣይ ታሪክ✍

....

አንድ በጣም ህብረተሰቡ ዘንድ ተወዳጅ የሆነ ሰው ነበር። ስሙ አህመድ ይባላል። አህመድ በጣም ጨዋ እና፤ ከሰው ጋር በቀላሉ ይግባባል። ታድያ ሰው ይወደዋል፤ እሱም ለሰው ጥሩ አሳቢ ነው። አህመድ እንኳን ለወዳጆቹ ክፋ ለሚሆኑበት እንኳን ጥሩና ቅን አሳቢ ነው።

አህመድ ሰላት የሚሰግደው በአቅራቢያው በሚገኝ መስጅድ ነው። ሁሌም ከመስጅድ አይጠፋም። 5ትወቅት ሰላት መገኛው መስጅድ ነው። በመስጅዱ በሚገኘው ጀመዓ ውስጥም የጎላ ተሳትፎ አለው። አህመድ ከፀባዩ ሲበዛ #ዝምተኛ ነው። እርሱ ዘንድ ወሬ ካልጀመሩ እንጂ በቀላሉ አይከፈትም። ዝምተኛ ሰው ይፈራሉ ይሉ፤ በጣም ይፈሩት፤ ያከብሩት፤ ይወዱት ነበር።

የዲን እውቀቱ ይህን ያህል ሚባል አይደለም። ግን በሚያውቀው በእያንዳንዱ ነገር ይተገብራል። (እኛ ብዙ ሃዲሶችን እናውቃለን። ስንቱን ተግብረናል!?) ዛሬ አህመድ ሳምንቱን ሙሉ በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው የጁምዓ ቀን ነው። ጁምዓ ቀን ፏ ማለት በጣም ይወዳል። ነጭ ጀለብያ፤ ነጭ የጀለብያ ሱሪ፤ ቀይ ጥምጣም፤ ማራኪ መዓዛ ያለው ሽቶ.. ብቻ ከሚባለው በላይ ጁምዓ እለት መዋብ ይወዳል። ሻወር ገብቶ ተውቦ የጁምዓ ሰላት የሚሰግድበት ሙሰላ ላይ ሽቶውን ነስንሶ በዚያ በሚያምር ግርማ ሞገሱ ወደ መስጅድ ለመጓዝ ከቤት ወጥቶ ጉዞ ጀምሯል። ይሄኔ አይኑ አንዳች እንግዳ ነገር ላይ ያርፋል። በጣም ደነገጠ!! አይኑን ለመስበር ሞከረ፣ ግን አልቻለም። አንዴ ቀና ብሎ አያት በጣም ደስ የሚል ስሜት ተሰማው። አንዲት ውብ ጂልባቢስት በመንገዱ ዳር በሚገኝ ሱቅ ላይ እቃ ትነግዳለች። አህመድ ከዚህ በፊት ያላያት፤ አንድም ቀን አይኑ ቀና ብሎ አያውቅም። ዛሬ አላህ ቀድሮ ተገጣጠሙ። ብቻ አይኑን ነቅሎ ጉዞውን ቀጠለ።

ጁምዓ ሰላት የመጀመርያው ሰፍ ላይ ተቀመጠ። ኢማሙን በጉጉት ይጠባበቅ ገባ። እስከዛ ድረስ ግን ጁምዓ እለት ሱረቱል ካህፍን ለምን አልቀራም ልትሉ ትችላላችሁ። አዎ ሱረቱል ካህፍን ጁምዓ እለት እንድናነብ ረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም አስተምረውናል። የቀራ ሰው ከአላህ የሆነ ጥበቃ ሳምንቱን ሙሉ ይኖረዋል። ይህንን አህመድ ጠንቅቆ ያውቃል። በመሆኑም የፈጅር ሰላትን ሰግዶ ነበር ሱረቱል ካህፍን አንብቦ የጨረሰው። ታድያ ኢማሙ እስኪከሰት ድረስ ዚክር ማድረጉን ተያያዘው። በመሃል የቅድሟ ቆንጅዬ ልጅ በዓይኑ እልፍ ትላለች። ዚክሩን አቁሞ ስለሷ ትንሽ ካሰበ በኋላ ድጋሚ ከገባው ሌላ አለም ይነቃል። ወደ ዚክሩም ይመለሳል።

ከቆይታ በኋላ ስለ ልጅቷ ሃሳቡን ይጀምራል። "ማን ናት? እስከዛሬ እንዴት አላየኋትም?? ስሟ ማን ይሆን? አግብታ ይሆን እንዴ? ለነገሩ እኔ ምን አገባኝ!!" ትንሽ ይቆይና...

"ምናልባት አላህ የፃፈልኝ ሃላሌ ብትሆንሳ!? ማን ያውቃል? ብቻ አላህ መልካሙን ይግጠመኝ" ብሎ ከህሊናው ጋር ሙጉት ውስጥ ሳለ ኢማሙ ለኹጥባው፤ እፊት ለፊታቸው የሚገኘው ማይክራፎንን በረጅሙ እፍፍፍፍፍፍፍፍፍ በማለት ሰውን ለማንቃት ሞከሩ። ይሄኔ አህመድ ከገባበት ጭልጥ ያለ ሃሳብ.....

ክፍል ሁለት ይቀጥላል....

ፎርዋርድ በማድረግ ለወዳጅዎ ያጋሩ!!

14/03/2021

hiii

Address


Telephone

+251912069942

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ibnu habeshiyi posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ibnu habeshiyi:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Event Planning Service?

Share