27/02/2023
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ4ኛው ዙር የመጀመሪያ ባች ስልጠና ተጠናቋል።
በስልጠናው የተገለጸው :-
፩) የልማት ባንክ የማምረቻ መሣሪያ በብድር ኪራይ ያቀርባል።
፪) ተበዳሪው ሠርቶ ኪራይ እየከፈለ በመሣሪያው ይጠቀማል። ኪራይ እስከሚጨርስ የመሣሪያው ባለቤት ልማት ባንክ ነው።
፫) ተበዳሪው ብድሩን በኪራይ መልክ ከፍሎ ሲጨርስ መሣሪያው የራሱ ይሆናል።
፬) የኪራይ ግዢ ብድሩን ለማግኘት ከጠቅላላው ካፒታል 20% የሚሆን የሥራ ማስኬጃ ካፒታል ተበዳሪው እንዲያቀርብ ይጠየቃል።
፭) ተበዳሪው ለማሽኑ በልማት ባንክ ስም የመድን ዋስትና እንዲገባ ይጠየቃል።
፮) ተበዳሪው ለመረጠው መሣሪያ ግዢ 3 የዋጋ ማቅረቢያ እንዲያቀርብ ይጠየቃል። ለአገልግሎት ዘርፍ ከሆነ 1 በቂ ነው።
፯) የልማት ባንክ የሚያበድረው ብድር ትንሹ 2 ሚሊየን ብር፣ ትልቁ ደግሞ 60 ሚሊየን ብር ነው።
፰) ብድሩን ከፍሎ የማጠናቀቂያ ጊዜ እጅግ ቢበዛ 7 ዓመት ነው።
፱) ለህብረት ሥራ ማህበራት፣ ለሴቶች፣ ወጣቶችና ለአካል ጉዳተኞች ቅድሚያ ይሰጣል ተብሏል።
፲) የብድር ዓመታዊ ወለድ ከ7% - 11% ይደርሳል። 7% ለግብርና ነው።
፲፩) ለሚሠራው ሥራ መሬት ማግኘት፣ ገበያ መፈለግና እንዴት እንደሚያተርፍ አጥንቶ መሥራትና ሥራውን በትርፋማነት መሥራት/መምራት የተበዳሪው ፋንታ ነው።
፲፪) ለሥራ ማስኬጃ የሚያስፈልገውን 20% ይህም ማለት ከ500 ሺህ ብር እስከ 15 ሚሊየን ብር ማዘጋጀት የተበዳሪው ኃላፊነት ነው።
____________
አሁን እንግዲህ እንዴት እንደሚሠራ ሁሉም በስልጠናው የተገለጸውን ሃሳብ ተጠቅሞ መሥራት አለበት።
1) በቅድሚያ የምትሠማራበትን ዘርፍ ምረጥ። የሥራ ዘርፍ እንዴት ትመርጣለህ? የምትሠማራበትን ዘርፍ ታውቀዋለህ? ሠርተህበታል? ተመሳሳይ ሥራ የሚሠራ ድርጅት ዓይተሃል? ያተርፋል? እንዴት?
2) ተቋሙን ከእነማን ጋር ትመሠርታለህ? ወይንስ ለብቻህ ትሮጣለህ? ለምን? አጋሮችህን/ሸሪኮችህን እንዴት መረጥካቸው? ምን ይዘው ይመጣሉ?
3) የቢዝነስህን ህጋዊ የአደረጃጀት ተቋም መርጠህ ወስንና የንግድ ፈቃድ አውጣ። ህጋዊ የድርጅትህን ዓይነት እንዴት ትመርጣለህ? PLC, S. Co., Coop, Sole Propeitirship, ... የቱ ይሻልሃል? ለምን?
4) የት ቦታ ትሠራለህ? የራስህ ህጋዊ ቦታ አለህ? ወይንስ ትከራያለህ? ከየት? ለምን ያህል ጊዜ? ቢያንስ የ2 ዓመት የኪራይ ውል ባንኩ ይጠይቃል።
5) የድርጅቱን የእለት ተእለት ሥራ ማን ይመራዋል? ማን ይሠራዋል? ገበያ ማን ያፈላልጋል? ማን ጥሬ-ዕቃ ይገዛል? ማን ያመርታል? ማን ይሸጣል? ማን ሂሳብ ይመዘግባል? ማን ሠራተኞችን ይመራል?
6) ተቋሙ በገበያ ላይ ከሌሎች ብልጭ ለማግኘት እንዴት ይወዳደራል? ምን የተለየ ነገር ይዞ ይቀርባል?
7) ትርፍ መቼና እንዴት ይከፋፈላል? ድርጅቱ ቢከስር ምን ታደርጋለህ? ተጨማሪ ካፒታል ማመንጨት ትችላለህ? ወይንስ ምን ታደርጋለህ?
__________
ወዳጄ ልብ በል :-
ገንዘብ ወይም መሣሪያ ብቻ ስኬታማ ቢዝነስ አይፈጥርም። ስኬታማ ቢዝነስ የብዙ ጉዳዮች ቅንብር ውጤት ነው።
በተለይ ግን ከላይ የተቀመጡት 7 ነጥቦች ለስኬታማ ቢዝነስ እጅግ ወሳኝ ናቸውና ከአሁኑ ተዘጋጅበት።
***
👉 የሥራ ማስኬጃ ገንዘብ ለሌላቸው የአክሲዮን ኩባንያ እንዲያቋቁሙ ባንኩ ያግዛል።
👉 አዲስ ሃሳብ ላላቸው ባንኩ የተወሰነ % ባለድርሻ ሆኖ ሃሳቡን ሙሉ በሙሉ ፋይናንስ ያደርጋል።
በሉ ተዘጋጁ!
ከዚህ ሁሉ ሰልጣኝ መካከል፣ የዛሬ 10 ዓመት ወደፊት ሲታይ 1000 ሰው የሚቀጥሩ 10 ትልልቅ ኩባንያዎች ተመሥርተው ከተገኙ ለሀገር ትልቅ ነገር ነው።
ከ https://www.facebook.com/100000511141487/posts/6716212265072412/?mibextid=cr9u03