Teferi event and promotion

  • Home
  • Teferi event and promotion

Teferi event and promotion የሀሰት መረጃዎችን በማምከን እውነተኛ መረጃዎችን ለሕብረተ?

(መስቀሉ በእኛ ሕይወት) በመስቀሉ ድነናል {ኤፌ.1፥7፤1ኛ.ጴጥ.1፥19}በመስቀሉ ክርስቶስ ወደ ራሱ አቅርቦናል፤ በሰማያት ወደ አባቱ አቅርቦናል {ዮሐ.12፥32 ፣ኤፌ.2፥13፣ መጽ.ኪዳን}በ...
28/09/2023

(መስቀሉ በእኛ ሕይወት)

በመስቀሉ ድነናል {ኤፌ.1፥7፤1ኛ.ጴጥ.1፥19}
በመስቀሉ ክርስቶስ ወደ ራሱ አቅርቦናል፤ በሰማያት ወደ አባቱ አቅርቦናል {ዮሐ.12፥32 ፣ኤፌ.2፥13፣ መጽ.ኪዳን}

በመስቀሉ ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀናል ሰላምን አግኝተናል {ሮሜ.5፥2፣1ቆሮ.1፥31፣ዕብ.10፥10}

በመስቀሉ ለዘለዓለም ፍጹማን ሆነናል {ዕብ.10፥14}

በመስቀሉ የዕዳ ደብዳቤያችን ተደምስሷል{ቈላ.2፥14}

በመስቀሉ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለመግባት ሞገስ አግኝተናል፣ {ዕብ.10፥19}

በመስቀሉ ላይ በፈሰሰው ደም ከበደላችን ሁሉ ታጥበናል {ራዕ.12፥11}

በመስቀሉ ቤዛነት እንመካለን {ገላ.6፥14}

(የተዋህዶ ልጆች የመስቀሉ ፍቅር ይደርብን አሜን )

📷  Visit Wolaita - ኑ ወላይታን ይጎብኙ።
27/11/2022

📷 Visit Wolaita - ኑ ወላይታን ይጎብኙ።

777ሀምበሪቾ ተራራ - ከምባታ ጠምባሮሀምበሪቾ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በከምባታ ጠምባሮ ዞን የሚገኝ አስደናቂ ተራራ ነው። ተራራው ከባህር ጠለል በላይ በ3058 ሜትር ከፍታ...
23/10/2022

777
ሀምበሪቾ ተራራ - ከምባታ ጠምባሮ

ሀምበሪቾ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በከምባታ ጠምባሮ ዞን የሚገኝ አስደናቂ ተራራ ነው። ተራራው ከባህር ጠለል በላይ በ3058 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን ወደ ተራራው ጫፍ የሚያደርሱ 777 ደረጃዎች በቅርቡ ተሰርተውበታል።

የደረጃዎች ብዛትና ስያሜ 777 የሆነው የከምባታ ብሔረሰብ ከ7 ቁጥር ጋር ካለው ትውፊታዊ ትስስር በመነሳት ነው። በ777 ያሉት ሦስቱ ሰባቶች የመጀመሪያ ሰባት የከምባታ ሰባቱን ነገዶች(ጎሳዎች)፣ ሁለተኛው ሰባት በሀምበሪቾ የሚገኙ ሰባቱን ተራራዎች፣ ሦስተኛው ሰባት ከተራራው የሚነሱ ሰባቱን ወንዞች ይወክላሉ።

The youth and sports office of the region has announced that the voluntary service of the youth during the summer months...
19/09/2022

The youth and sports office of the region has announced that the voluntary service of the youth during the summer months is in quality and better performance according to the planned leadership plan.


September 09/2015

Hawassa

The management members of the Youth and Sports Bureau have thoroughly reviewed the report showing the status of the voluntary service of the youth during the summer months.

In 13 different areas of voluntary service, the management evaluated the activities of the sector offices, zones and special districts of the region in terms of their plans.

In accordance with the 1.49 billion birr plan set to save the cost of this voluntary service from the government and the society, the management observed that the cost was avoided in a certain way by carrying out charity work costing 1.17 billion birr.

On the other hand, it is planned to do 5 million 892 thousand 184 voluntary works that will benefit the society, and the report states that the current work process has exceeded the plan.

Volunteer youths have been able to deploy one million 824 thousand 804 youths in the good work in an organized way to involve youths in an organized way so that they can use their time, energy and knowledge for the peace, security, development and prosperity of the society and for universal change.

Tesfaye Blatu, Head of the Regional Youth and Sports Bureau, said during the evaluation that organized leadership, integrated support and monitoring, the adoption of a consistent evaluation system, the participation of stakeholders and the focus of the work played a positive role in achieving better results.

The implementation process of the task was evaluated by the technical and technical committee in terms of strengths and weaknesses.

The implementation process of the task was evaluated by the technical committee in terms of strengths and weaknesses.

It was also stated that after the voluntary work summation program of the summer months at the level of zones and special districts until September 15/2015, a general summation program will be held at the regional level.

In the remaining periods, the management has set a direction for the completion of the summer voluntary service program and the winter voluntary service launching program.

14/09/2022
ወላይታ የሊቃ ትምህርት ቤት ፍሬዎች  | እነዚህ ከዚህ በታች የምትመለከቷቸው በ2014 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ7 ዓመታት ህክምና ትምህርታቸውን ...
14/09/2022

ወላይታ
የሊቃ ትምህርት ቤት ፍሬዎች

| እነዚህ ከዚህ በታች የምትመለከቷቸው በ2014 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ7 ዓመታት ህክምና ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ እና ለመመረቅ የቀናት እድሜ የቀራቸው ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ አብሮ ያደጉና በአንድ ትምህርት ቤት የተማሩ ከ20 በላይ የሚሆኑ የቀድሞ የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ፍሬዎች ናቸው።

የወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ከዚህ ቀደምም ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በርካታ ምሁራንን በማስመረቅ ይታወቃል።

Wolaytta Worqqaa mayzzana!!
ሠላም ለኢትዮጵያ ይሁን!!
ምንጭ ጌጡ ተመስገን

የጸጥታው ም/ቤት ሳምንት ባለሞላ ጊዜ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመወያየት የጠራው ስብሰባ ለሁለተኛ ጊዜ ውድቅ ሆነመስከረም 3/2015  የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ሳምንት ባለሞላ ጊዜ...
13/09/2022

የጸጥታው ም/ቤት ሳምንት ባለሞላ ጊዜ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመወያየት የጠራው ስብሰባ ለሁለተኛ ጊዜ ውድቅ ሆነ

መስከረም 3/2015 የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ሳምንት ባለሞላ ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለመወያየት የጠራው ስብሰባ ለሁለተኛ ጊዜ ውድቅ መሆኑን በተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ገለጹ፡፡

አምባሳደር ታዬ ከኢኤምኤስ ጋር ባደረጉት ቆይታ የጸጥታ ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ላይ ሊያደርገው ስላሰበው ስብሰባና ተያያዥ ጉዳዮች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ግልጽ ስብሰባ እንዲደረግ በተለይ አንዳንድ አውሮፓዊያን ሀገራት ለወቅቱ የጸጥታው ምክር ቤት ሰብሳቢ (ፈረንሳይ) ጥያቄ ባቀረቡት መሰረት ስብሰባው ሊካሄድ መታሰቡን አምባሳደር ታዬ ገልጸዋል፡፡

በሌላም በኩል አፍሪካዊያን እና ሌሎች ሀገራት ደግሞ የኢትዮጵያን ጉዳይ የአሰራር ሂደትን ተከትሎ ማጣራት እንጂ በቀጥታ መደበኛ ስብሰባ ማድረግ አያስፈልግም የሚል አቋም መያዛቸውን አስረድተዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች መስማማት ባለመቻላቸው ጳጉሜ 3 ቀን 2014 እንዲሁም መስከረም 2 ቀን 2015 ዓ.ም ሊደረግ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው ስብሰባ አለመሳካቱን ነው አምባሳደር ታዬ የጠቆሙት፡፡

ምክር ቤቱ ከኅዳር 2012 ዓ.ም ጀምሮ የሕዳሴ ግድብን ሳይጨምር በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለ12 ጊዜ ያህል ስብሰባ መጥራቱን እና ሁለት ጊዜ መግለጫ ማውጣቱን ያስታወሱት አምባሳደር ታዬ ኢትዮጵያ የጸጥታው ምክር ቤት አጀንዳ አይደለችም ብለዋል፡፡

ከራሳቸው ፍላጎት በመነሳት የኢትዮጵያ ደመኛ የሆነን ኃይል እንደማደጎ ልጅ የሚቆጥሩ አንዳንድ ሀገራት ደመኛው ሀይል ባለቀሰ ቁጥር ፋይል ይዘው ወደ ጸጥታው ምክር ቤት ስለሚሮጡ ነው የኢትዮጵያ ጉዳይ በጸጥታው ምክር ቤት የሚታየው እንጂ የኢትዮጵያ ጉዳይ በምክር ቤቱ ሊታይ የሚገባው ሆኖ አይደለም ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ በጸጥታው ምክር እስካሁን በተደረጉ ስብሰባዎች ሁለት ጊዜ መግለጫ ከማውጣት በስተቀር በኢትዮጵያ ላይ የተላለፈ ውሳኔ እንደሌለም አስረድተዋል፡፡
ኢትዮጵያም ‘የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ የውስጥ ጉዳያችን እንጂ የጸጥታው ምክር ቤት አጀንዳ ባለመሆኑ በራሳችን እንፈታዋለን’ የሚል አቋም ይዛ መዝለቋም አምባሳደሩ አስምረውበታል፡፡

በተባበሩት መንግስታት በአቅራቢያ ወይም በተዛማጅነት መርህ መሰረት ሀገራት ችግር ሲገጥማቸው ጉዳያቸው ወደ መንግስታቱ ድርጅት ከመምጣቱ በፊት በክፍለ አህጉር ድርጅቶች እንዲታይ ይደረጋል፡፡

በዚሁ አሰራር መሰረት ኢትዮጵያ የገጠማት የውስጥ ጉዳይ ወደ ጸጥታው ምክር ቤት ከመሄዱ በፊት በመጀመሪያ መታየት ያለበት በአፍሪካ ህብረት መሆኑን አምሳደር ታዬ አብራርተዋል፡፡

በተባበሩት መንግስታት እና በአፍሪካ ህብረት መካከል ያለው ግንኙነት መቃኘት ያለበትም በዚሁ መልኩ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ምንጭ ዋልታ

ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆኑ  የባሕርዳር ከነማ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆነው ተሾሙ፡፡ አሰልጣኙ ፊፋ ለቴክኒክ ባለሙያ...
13/09/2022

ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆኑ

የባሕርዳር ከነማ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆነው ተሾሙ፡፡

አሰልጣኙ ፊፋ ለቴክኒክ ባለሙያነት ያቀረባቸውን መመዘኛዎች በማለፍ እንደ ሁኔታው በሚታደስ የሁለት ዓመት ኮንትራት የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ መሆናቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ኢንስትራክተር አብርሃም በአፍሪካ ከፍተኛ ኢንስትራክተርነት ፣ በአፍሪካ ዋንጫ እና መሰል ትላልቅ ውድድሮች በቴክኒክ ጥናት ቡድን አባልነት እና አሰልጣኝ በመሆን አገልግለዋል፡፡

በተጨማሪም አሰልጣኙ በእስያ እና የመን እግር ኳስ ላይ ያላቸው የስራ ልምድ ለቦታው ተመራጭ ያደረጋቸው መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

11/09/2022

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

መስከረም 1 ቀን 2015 (ኢዜአ) የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለመላው ኢትዮጵያውያን የአዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም መጪው አዲስ ዘመንለ ኢትዮጵያውያን ሰላም፣ መቻቻል፣ መከባበርና መፈቃቀድ የሰፈነበት እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያብሔራዊ ደኅንነት እና ጥቅም እንዲረጋገጥም ሁሉም ተባብሮ እና ተደማምጦ የሚሰራበት እንዲሆንም አሳስበዋል።

‹‹መላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ከዘመን ዘመን አሸጋገራችሁ፤ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤናና የስኬት እንዲሆን በራሴ እንዲሁም በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች ስም መግለጽ እወዳለሁ›› ብለዋል፡፡

በተለይ የኢትዮጵያን ህልውና ለማረጋገጥ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በግዳጅ ላይ የምትገኙ የጀግናው የመከላከያ ሠራዊት እና የጥምር ጦሩ አባላት መላው ሕዝብ የሰላም አየር እንዲተነፍስ የሕይወት ዋጋ ጭምር እየከፈላችሁ በመሆኑ ክብር ይገባችኋል ብለዋል፡፡

ውድ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አዲሱ ዓመት ለሰላም በምትከፍሉት መስዋዕትነት በአዳዲስ የድል
ብሥራቶች የሚታጀብ እንደሚሆን በልበ ሙሉነት እገልጻለሁም ነው ያሉት፡፡

የተቋሙ አባላትም የሥጋት ቀጣና በሆኑ አውደውጊያዎች ጭምር በመሠማራት መረጃ በመሰብሰብ፣በመተንተንና ለሚፈለገው አላማ እንዲውል በማድረግ ሀገራዊ ግዳጃቸውን እየተወጡ በመሆኑ አክብሮቴና የአዲሱ ዘመን መልካም ምኞቴ በያሉበት ይድረሳቸው ብለዋል፡፡

በመልዕክታቸው ኢትዮጵያ ሰላምን አበክራ ትሻለች፤የሰላሙ መንገድ ዛሬም ክፍት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ይህን ባለመቀበል ጦርነትን የቀሰቀሱ አካላት ዛሬም የሰላምን ዋጋ ተረድተው በአዲስ ዓመት በአዲስ መንገድ እንዲጓዙ ኢትዮጵያ ጥሪ ታቀርባለች ያሉት አቶ ተመስገን፤ በሀገር ህልውና የተቃጣውን ጥቃት ጀግናው የመከላከያ ሠራዊትና የጥምር ጦሩ በብቃት መመከታቸውን ወደፊትም ይህ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትም በተጠናቀቀው ዓመት ባከናወናቸው የሪፎርም ሥራዎች ዘመኑን የሚዋጁ ቴክኖሎጂዎች በመታጠቁና የላቀ ብቃት ያለው የሰው ኃይል አቅም በመገንባቱኢትዮጵያ ፈተናዎችን በአሸናፊነትና በጽናት እንድትሻገር ብርቱ ጉልበት ሆኗል፤ በእርግጥም ኢትዮጵያ ታሸንፋለች ብለዋል፡፡

መረጃዎቻችንን በዩቲዩብ፡- https://www.youtube.com/channel/UCSjaw-eGJSkvcXHyTpQyT1Q
በቴሌግራም፡- https://t.me/EthiopianNewsA
በድረገጽ፡- https://www.ena.et/
በትዊተር፡- https://twitter.com/ethiopiannewsa?lang=en
በአፋን ኦሮሞ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/TajaajilaOduuItoophiyaa/ አድራሻዎቻችን ያገኟቸዋል።የኢዜአ ዜናዎችን በአጭር የስልክ መልዕክት ለማግኘት፡- 9111

09/09/2022

በካፍ ኮንፌዴሬሽን የቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታ የቡሩንዲው ቡማሙሩን የገጠመው ፋሲል ከነማ 3-0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

""""""ኢየሱስ ያድናል🙏አጋጣሚውን ተጠቅማችሁ በድፍረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስን አታውቅም ኢየሱስን አሰብክም የሚል የሞኝ ከበሮ አትደልቁ! ይህንን እንድል ያደ...
14/08/2022

""""""ኢየሱስ ያድናል🙏

አጋጣሚውን ተጠቅማችሁ በድፍረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስን አታውቅም ኢየሱስን አሰብክም የሚል የሞኝ ከበሮ አትደልቁ! ይህንን እንድል ያደረገኝ በአንዲት ግለሰብ ሰበብ ብዙ ሚሊዮን ተከታይ ያላትን ቤተክርስቲያንን ብዙ ሲሉ ስላየው፣ዝም ማለት አልፈለኩም።ምክንያቱም ያደኩበት ነው።


“ኢየሱስ ጌታ ነው” የሚለው ሰበር ዜናዋ ሊሆን አይችልም!

የዛሬ 2000 ዓመት ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወለድ እጅመንሻ ይዛ ለተገኘች፡

ኢየሱስ ክርስቶስን በሕፃንነቱ ሲሰደድ ለተቀበለች፡

ኢየሱስ ባረገ በዓመቱ በጃንደረባዋ በኩል በስሙ ለተጠመቀች፡

ከማንም በፊት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ያላትን እምነት በንጉሥዋ በኢዛና በኩል በይፋ ለገለጠች፡

በዓለም ጥንታዊዉን በእጅ የተጻፈ የኢየሱስ ወንጌል በአባ ገሪማ ገዳም ለያዘች፡

በዓመት ከ1825 ጊዜ በላይ የኢየሱስ ወንጌል እንዲነበብ ሥርዓት ለሠራች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፡-

“ኢየሱስ ጌታ ነው” የሚለው ሰበር ዜናዋ ሊሆን አይችልም፡፡
👉ደንቆሮ የሰማ ዕለት ያብዳል ሆኖ ነው እንጂ ነገሩ፡፡

መሳይ መኮንን

12/08/2022
12/08/2022

መልካምነት የድንቅ ሰዎች መገለጫ ነው።

ለወገን ደራሽነት፣ አጋዥነት፣ አበርታችነት የንፁ ልቦች ስጦታ ነው።

የሰውነትህ ሙሉነት በጓደኛህ ደስታ ስትደሰት ነው፤ ለቤተሰብህ እድገት በምታደርገው ጥረት ነው፤ ለወገንህ በምታበረክተው አበርክቶት ነው።

ለእራስ ብቻ መሮጥ የትም አያደርስም። ትርፍህ ሰው ነው። ምንም ብትሰራ የሚጠቀመው ሰው ነው፤ ያንተም ተጠቃሚነት ከሰው ይነሳል።

ብትደክም፣ ብትለፋ አገልጋይነትህ ለወገንህ ነው። ምንም እንኳን ለእራስህ ጥቅም ብትለፋ የምትጠቀመው በሰጠሀው አገልግሎት ልክ ነው።

አዎ! በመልካምነት ተመላለስ፣ በቅንነት ስራ፤ ጣፋጩን ስጦታህንም ተቀበል። በንፉግነትህ ከምታገኘው ገንዘብ በአገልጋይነትህ፣ በመስጠትህ የምታገኘውን ደስታ እጅጉን የተሻለ ነውና እርሱን ምረጥ።
ውብ ቀን ይሁንላችሁ

04/08/2022

በብሄር መከፋፈል ዋነኛ የዕድገት ጠንቅ ነው ኢትዮጵያዊነት ይበልጣል !

የደስታችን ሚስጢር የሆነችውን ይህችን ውብ ኢትዮጵያዊት ስሟን ከፍ አለማድረግ፣ ንፉግነት ነው። ሙያ በባለሙያ ሲያዝ፣ ድል ይዥጎደጎዳል። እናመሰግናለን። ገለቶማ። የቅንየለይ። ንቃር ናመሰግነ።...
24/07/2022

የደስታችን ሚስጢር የሆነችውን ይህችን ውብ ኢትዮጵያዊት ስሟን ከፍ አለማድረግ፣ ንፉግነት ነው። ሙያ በባለሙያ ሲያዝ፣ ድል ይዥጎደጎዳል። እናመሰግናለን። ገለቶማ። የቅንየለይ። ንቃር ናመሰግነ።

ፋሲል የኔአለም

Address


Telephone

+251911094652

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Teferi event and promotion posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Teferi event and promotion:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Event Planning Service?

Share