ኪ/ዲ/ወ/ዴ/ተ/ምሁራን ዘርፍ

  • Home
  • ኪ/ዲ/ወ/ዴ/ተ/ምሁራን ዘርፍ

ኪ/ዲ/ወ/ዴ/ተ/ምሁራን ዘርፍ Performance

አዲሱ ዓመት 2012 የወላይታ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ያለ ምንም መንገራገር በሰላማዊ መንገድ የሚመለስበት ዓመት ይሁንልን!
12/09/2019

አዲሱ ዓመት 2012 የወላይታ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ያለ ምንም መንገራገር በሰላማዊ መንገድ የሚመለስበት ዓመት ይሁንልን!

እንኲን ለ2012 ዓ.ም አዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት፣ የመንፈስና የስነ ልቦና ዕድሳት፣ የስኬት፣ የብልጽግና ይሁንልን!!
12/09/2019

እንኲን ለ2012 ዓ.ም አዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት፣ የመንፈስና የስነ ልቦና ዕድሳት፣ የስኬት፣ የብልጽግና ይሁንልን!!

11/09/2019

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ዘርፍ በአፍሪካ የፖለቲካ አማካሪዎች ማኅበር ተሸለሙ

💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖💖

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የአፍሪካ የፖለቲካ አማካሪዎች ማኅበር ሽልማት አበረከተላቸው።

የአፍሪካ የፖለቲካ አማካሪዎች ማኅበር አራተኛ ጉባኤውን “የምርጫ ቅስቀሳ ፋይናንስና ምርጫ በአፍሪካ” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው።

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ኬሂንዳ ባሚግቤታን እንደተናገሩት፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ማሻሻያ አድርገዋል።

በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎችና እስረኞች እንዲፈቱና በውጭ የሚኖሩ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ወደ አገራቸው በነጻነት እንዲመለሱ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ወደ ሀገራቸው ከመጡ በኋላም ከፖለቲከኞቹ ጋር ተቀራርበው መስራታቸውንና ከምሁራን ጋርም የፖለቲካ ከባቢ መፍጠራቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል።

በመሆኑም ማኅበሩ ይህንን ተግባራቸውን ከግምት በማስገባት የአፍሪካ የዓመቱ የዴሞክራሲ ተሸላሚ እንዲሆኑ መወሰኑን ነው የጠቆሙት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያመጧቸውን አዎንታዊ ለውጦች ለማስቀጠል መሥራት እንዳለባቸውም የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ተናግረዋል።

ማኅበሩ ከዚህ ቀደም ለሁለት ናይጄሪያዊ ፖለቲከኞች ተመሳሳይ ሽልማት ሰጥቷል፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ይህንን ሽልማት ሲቀበሉም ሦስተኛ ግለሰብ ናቸው ብለዋል።

ማኅበሩ በአፍሪካ በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የኃሳብ ልውውጥ ልምድ ለማዳበርና በምርጫ ሥርዓት ላይ ያሉ ስልቶችንና ልምዶችን ለመለዋወጥ ይሰራል።

ጎን ለጎንም በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር በማድረግ በአፍሪካ የዴሞክራሲ ሥርዓት እንዲዳብር እየሰራ የሚገኝ ማኅበር ነው።

ምንጭ፦ FBC

10/09/2019
ከቀን 01/13/2011 እስከ ቀን 03/13/2011ዓ.ም ድረስ በኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ከዞኑ ደጋፊ አመራሮችና አጠቃላይ የወረዳዉ አመራሮች ጋር የወረዳዉ ወቅታዊ ፖለቲካ ሁኔታ፣ ፀጥታ ሁኔታ እን...
10/09/2019

ከቀን 01/13/2011 እስከ ቀን 03/13/2011ዓ.ም ድረስ በኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ከዞኑ ደጋፊ አመራሮችና አጠቃላይ የወረዳዉ አመራሮች ጋር የወረዳዉ ወቅታዊ ፖለቲካ ሁኔታ፣ ፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም የክልል አደረጃጀት ጥያቄ በተመለከቱ ጉዳዮች ለተከታታይ ሦስት ቀናት ሰፊ ዉይይት ተደርጎ በስኬት ተጠናቅቊል።

08/09/2019

:- #ሀዋሳ

!🤧😆
------------------------------------------------------------------

ዛሬ ወደ አመሻሽ ከውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደደረሰኝ መረጃ ከሆነ ከሰሞኑ #ደኢህዴን ያዘጋጀውና እየተካሄደ ባለው የ' ' ወደ ህዝቡ የማስረፅ የአሰልጣኞች ስልጠና ላይ ከሲዳማ ዞን ውጭ ካሉ የደቡብ ክልል ዞኖች የመጡ የየዞን ወረዳዎች የድርጅቱ መዋቅር አባላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ:: ሆኖም #ከከፋ እና #ወላይታ ዞን ወረዳዎች የመጡ ተሳታፊዎች "'ሳይንሳዊ ጥናቱ' የዞናችንን ህዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ ጥያቄ የሚመልስ ባለመሆኑ ከወከልነው ህዝብ interest በተቃራኒ አንሰለፍም" በማለት ስብሰባውን እረግጠው ወጥተዋል::

ሆኖም የደኢህዴን ከፍተኛ አመራሮች የህዝብ እንደራሴዎቹን #በወታደር አስፈራርተውና አስገድደው ወደ ስብሰባው ሊያስገቡ እንደሞከሩ ታውቋል:: ይህም ሆኖ የህዝብ እንደራሴዎቹ ወደ ስብሰባው ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በተደረገ በወታደሮች የማሳሰር ሙከራ ወደ ከረረ ፍጥጫ ውስጥ ገብተው እንደነበር ከውስጥ አዋቂ ምንጮች የደረሱ መረጃዎች ገልፀዋል:: በኋላም ከወታደሮች ጋር የተፈጠረው ፍጥጫ ወደ ከፋ ደረጃ ሳይሸጋገር በንግግር ወደ ስምምነት ተደርሶበት ለጊዜው ሊበርድ ችሏል:: ከወታደሮቹና ከድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ስብሰባውን ረግጠው የወጡ የሁለቱ ዞኖች የህዝብ እንደራሴዎች መሀከል በተደረገው ውይይት ወቅት ምን አይነት ስምምነቶች ይደረሱ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም::
Via

07/09/2019
06/09/2019
06/09/2019
05/09/2019
04/09/2019

"በዓለም የምንታወቅበት የአክሱምን ሀወልት የሰሩ ጀግኖች አባቶቻችን ይህንን ያወረሱን ውብ ባህል ጠብቆ ለማቆየትና ለመንከባከብ እንዲሁም ከትውልድ ትውልድ ትውፊቱን ጠብቆ ለማስተላለፍ እንሰራለን። በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ በዓል በአዲስ አበባ ደረጃ ባማረና በደመቀ ሁኔታ ለማስከበር ከዛሬ ጀምሮ የከተማው መስተዳድር አጠናክሮ ይሰራል። አሸንዳ በዓለም ድንቅ የቅርሳቅርስ መዝገብ (UNESCO) ለማስመዝገብ የበኩላችንን ሁሉ እንሰራለን!"

ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ

04/09/2019
04/09/2019

የሳታላይት መረጃ መቀበያ ማዕከል ግንባታ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 29 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቅርቡ ከምታመጥቀው የመረጃ ሳታላይት በተጨማሪ ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎች ማግኘት የሚያስችላትን የመረጃ መቀበያ ማዕከል ግንባታ እያካሄደች ነው።

ኢትዮጵያ ከስምንት ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ ያደረገችበት እና አንድ የመረጃ አገልግሎት የሚሰጥ ሳተላይት ወደ ህዋ ለማምጠቅ ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ መሆኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር ዶክተር ሰለሞን በላይ ተናግረዋል።

ለሳታላይቷ ትዕዛዝ የሚሰጠው እና የሚቆጣጠረው ቴክኖሎጂ ግንባታ እንዲሁም ከዓለም አቀፉ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ህብረትና አውተር ስፔስ ፈቃድ የማግኘቱ ስራ መጠናቀቁንም ይናገራሉ።

የቻይና መንግስትም ሳታላይቷ የምትመጥቅበትን ቦታ መፍቀዱን ያነሱት ዳይሬክተሩ፥ አሁን ላይ የሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ የመግባት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በአንድ ሳታላይት ብቻ አስፈላጊ መረጃዎችን ማግኘት ስለማይቻልም አሁን ላይ መረጃን ከሌሎች ምንጮች የሚቀበል ማዕከል ግንባታ (ሪሲቨር ስቴሽን) እየተከናወነ መሆኑንም አስረድተዋል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ባሳለፍነው ሰኔ ወር ግንባታው የተጀመረው ማዕከል እስከ ታህሳስ ወር ድረስ ስራውን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ማዕከሉ ስራ ሲጀምርም ከአምስት የተለያዩ ሳታላይቶች መረጃዎችን በመቀበል የማደራጀት አቅም ይኖረዋል ነው የተባለው።

ከማዕከሉ ግንባታ ባለፈም የቻይና ብሄራዊ ህዋ ኤጀንሲን ጨምሮ መረጃን ማግኘት በሚቻልበት አግባብ የተለያዩ ስምምነቶች እየተፈጸሙ ስለመሆኑም ዳይሬክተሩ አንስተዋል።

በአፈወርቅ አለሙ

04/09/2019
04/09/2019

ለደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የ2012 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት 40 ቢሊየን ብር እንደሆነ ታውቋል፡፡
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

የበጀት ድልድሉ የቅርብ ዓመታት የፌደሬሽን ምክር ቤት የበጀት ድልድል ቀመርን የተከተለ መሆኑን የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ገልጿል፡፡

በክልሉ በ2011 በጀት ዓመት በውስጥ የተሰበሰበ ገቢ 8 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ብቻ መሆኑን ነው የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታምራት ዲላ የተናገሩት፡፡

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ባካሄደው ጥናት ክልሉ ከአቅም በታች ገቢ እየሰበሰበ እንደሆነ በጥናት ማረጋገጡን የገለጹት ኃላፊው የውስጥ ገቢን በማሳደግ ረገድ ስራዎችን መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

የ2012 በጀት ድልድል ከህዝብ ቁጥር በተጨማሪ የየአካባቢዎቹን ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ፣ አሰፋፈር፣ ከማዕከል ያላቸውን ርቀት ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በዞንና ልዩ ወረዳዎች በጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴዎችን ጨምሮ የየሴክተር መስሪያ ቤት የፋይናንስ ኃላፊዎች በተሳተፉበት በዚህ በያዝነው በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት በቀረበበት መድረክ በየአካባቢው በጀት ለመደልደል የሚሰበሰቡ መረጃዎች በልዩ ጥንቃቄ እየተወሰዱ አይደለም የሚል ጥያቄ ተነስቷል፡፡ በዚህም ድልድሉ ፍትሀዊ አይደለም የሚል ጥያቄ ቀርቧል፡፡

መረጃ የማግኘት፣ የበጀት አደላደል ዘዴ ግንዛቤ ማነስ እና የማስፈጸም አቅም ውስንነት ቢሮው ያጋጠሙት ችግሮች እንደሆኑ ያነሱት አቶ ታምራት ዲላ የኢትዮጵያ ካርታ ስራዎችን ጨምሮ መረጃ በተገቢው መንገድ መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡

የዘንድሮ በጀት ከአምናው አንፃር ሲታይ የ5 ነጥብ 59 ከመቶ ብልጫ እንዳለው ነው የተገለጸው፤ ለዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ጭማሪ ተደርጓል ተብሏል፡፡

ለክልሉ ነዋሪዎች በነፍስ ወከፍ ለአንድ ሰው የአገልግሎት ወጪ 1423 ብር መሆኑን ነው ከክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተገኘው መረጃ የሚያሳየው፡፡

በክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 4ኛ ዓመት ዘጠነኛ መደበኛ ጉባኤ 40 ቢሊየን ብር በጀት ለውይይት ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

(ደሬቴድ)

04/09/2019

ትልቁ ባህር የጠብታ ውሃ ውጤት ነው!

ጠብታ ባህርን የመፍጠር አቅም እንዳለው ሁሉ አንድ ግለሰብ የጠብታን ያህል ሚና ተጫውቶ ባህር መሆን የሚችል ታሪክ የመስራት ታላቅ ጉልበት አለው! ታሪክ ድርሳናቱን ገልጦ እንደሚያስረዳንም በግለሰብ ደረጃ የተቀነቀኑ በጎም ይሁን እኩይ የነበሩ ሀሳቦች እና ድርጊቶች አለም ላይ ታላላቅ ተፅእኖዎችን መፍጠር እንደቻሉ ነው፡፡

አንድ ግለሰብ ሆነው ሚሊዮኖችን ያንቀሳቀሱ፤ሃሳባቸው ገዢ ሆኖ ብዙሀን የተከተላቸው፤ጠብታነታቸው ለባህር መፈጠር ምክንያት የሆነ በርካቶች ናቸው፡፡

ሉተር አንድ ግለሰብ ነበር ! አለም ላይ የፈጠረው ተፅእኖ ግን ዛሬም ድረስ አሻራው አለ ! ህይወት ብሎ የኖረለት ህልም ጥቁርን ከነጭ እኩል ማኖር የቻለ፤ሰው የተባለ ፍጡር በቆዳው ቀለም ሳይበላለጥ የሚኖርበት አለማዊ አውድ እንዲፈጠር በር ከፋች የሆነ ፤ጥቁሮች ለነፃነታቸው ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ አዲስ ጉልበት የሆናቸው፤ ዛሬ ለተፈጠረችው አለም ቅድመ አሻራ አሳራፊ መሆን የቻለ አንድ ግለሰብ ነበር !

የሉተር ተግባር ዛሬ በሰው ልጆች ዘንድ የቆዳ ቀለም እኩል እይታ እንዲኖረው፤ሰው በሰውነቱ እንዲከበር፤ነፃነት በእኩል ለሁሉም እንዲቸር፤ባርነትን የምትጠየፍ አለም እንድትፈጠር አስችሏል፡፡ ሉተር ተፅእኖው ሚሊዮኖችን ማጥለቅለቅ የቻለ፤አንድ ግለሰብ ለውጥ መፍጠር እንደሚችል ማሳያ ተደርጎ የተወሰደ ትንታግ የነፃነት አርበኛ ነው ዛሬም ድረስ፡፡

የጠብታ ባህርን የመፍጠር ጉልበት ማሳያ ሉተር ብቻ አይደለም!
እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር ዲሴምበር 17/2010 ዓ.ም በቱኒዚያዋ ቤን አሩስ ከተማ መሀመድ ቦአዚዚ የተባለ አንድ ግለሰብ ባልተገመተ ሁኔታ ራሱን አደባባይ ላይ በእሳት አንድዶ ገደለ፡፡

የግለሰቡ ድርጊት ራስን ከማቃጠል በላይ ሆኖ አለም በጉያዋ ያስተናገደቻቸው አሳዛኝ እና አስገራሚ የተባሉ ታሪኮች እንዲመዘገቡ አስቻለ፡፡

በአደባባይ የለኮሳት እሳት ከአካላቱ በላይ የምትፋጅ ሆና ቱኒዚያን የአረብ ሀገራት የለውጥ ንቅናቄ መጀመሪያ አድርጎ፤አይደፈሩም የተባሉ ወንበሮችን ነቅንቆ፤የአረብ ፀደይ የተባለው አብዮት አሀዱ ተብሎ አንዲጀመር በር ከፍች እንደሆነ ዛሬም ድረስ ስሙ ይነሳል፡
ያ አንድ ግለሰብ የፈፀመው ድርጊት የኮለኔል ጋዳፊ እና የሙባረክን ወንበር ይገረስሳል ብሎ ማንም አልገመተም ነበር ፡፡
ተግባሩ ግን አዲስ ድባብ የታየባት አለም እንድትፈጠር ያስቻለ፤ሊቢያ የመን እና ሶሪያን ወደ ፍርስራሽነት ቀይሮ፤ሚሊዮኖችን ለስደት እና ለሞት የተዳረጉበት ትራጀዲ በአለም ታሪክ ላይ እንዲመዘገብ ምክንያት ሆኗል፡፡

መሀመድ ቦአዚዚ እና ሉተር ብቻም አይደሉም የጠብታ ጉልበት ማሳያዎች….አለም በጉያዋ ጠብ እያሉ ባህር የሆኑ በርካቶች ነበሯት፡፡

ጋንዲ አንድ ጠብታ ነበር ባህርነቱ ዛሬ አለምን ይመራል…….ማልኮም ኤክስ አንድ ጠብታ ነበር በአሻራው አዲስ የነፃነት ባህር ያላት አለምን ፈጥሯል….ኤዲሰን ጠብታ ነበር በብርሀን ባህር የተሞላች አለም እንድትፈጠር አስችሏል……
አለም ዛሬ ለደረሰችበት ስልጣኔ እና ባህርነት መፈጠር ዋና ምክንያቶች ጠንካራ የሆኑ ጠብታዎች ናቸው፡፡

በርካቶች ለዛሬዋ አለም በንግግራቸው፤በአስተሳሰባቸው፤በዋጋ ከፋይነታቸው፤በፈጠራቸው ያበረከቱት የጠብታነት አስተዋፆ በቀላሉ የሚመዘን አይደለም፡፡

እኛ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ለምንገኝበት ሁኔታም በየዘመኑ ምድራችን ላይ ብቅ ያሉ ጠብታዎች ያሳረፉት አሻራ ጉልህ እንደሆነ አይካድም፡፡ዛሬ ላይ እንደ ሀገር የጀመርነው ለውጥም የጠብታን ጉልበት ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ሆኖ በህብረተሰባችን ዘንድ መስረፅ ከቻለ የምናገኘው ውጤት ቀላል አይደለም፡፡

የኢትዮጵያ ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት አንድ ግለሰብ ያለውን ፋይዳ ከቶ ልንዘነጋው አይገባም፡፡ሁላችም የዛሬ ፍሬ የሆንን ኢትዮጵያውያን ለነገዋ ኢትዮጵያ መፈጠር አስተዋፆ ይኖረናል፡፡

ጠንካራ ህብረተሰብ የጠንካራ ግለሰቦች ድምር ነው!
ሁላችንም ይህን ሀቅ ተረድተን ታላቅ ሀገርን ለመፍጠር በምናደርገው ጥረት ሁሉ በግል ያለብንን ሀላፊነት የተገነዘብን፤ለውጥን ከራሳችን የምንጀምር፤የጠብታነታችንን ጉልበት የተረዳን ልንሆን ይገባል፡፡

እኔ ስለወጥ ኢትዮጵያ ትለወጣለች በሚል እሳቤ መንቀሳቀስ ከቻልን በሰላም፤በአንድነት፤በፍቅር ባህር የተገነባች ሀገር ከመፍጠር ሊያግደን የሚችል አካል የለም፡፡

ከግለሰብ የሚጀምር ለውጥ ብርቱ ጉልበት እንዳለው እና በሁላችንም ዘንድ ያለው አቅም ኢትዮጵያን የማሳደግ እና የመለወጥ ችሎታ እንዳለው በአግባቡ ተረድተን ሁላችንም ሀላፊነታችንን መወጣት ግድ ይለናል፡፡

ከፊታችን የሚመጣው አዲስ አመትም ኢትዮጵያ የተባለችውን ታላቅ ባህር ለመፍጠር ታላቅ ጠብታ የምንሆንበት ሊሆን ይገባል፡፡

04/09/2019

በመላ የአፍሪካ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ አትሌቶች በሴቶች ግማሽ ማራቶን ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን በድል ፈፅመዋል፡፡

ያለምዘርፍ የኋላ ወርቅ፣ ደጊቱ አዝመራው ብር ፣መሰረት በለጠ ነሐስ በማግኘት ድሉን ጠቅልለው ወስደዋል፡፡

በሙሉጌታ ክፍሌ

03/09/2019
02/09/2019
የኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቀን 27/12/2011 ዓ.ም በከፈተዉ የግፋታ በዓል አከባበር ዝግጅት መድረክ ላይ የግፋታ በዓል ዘላቂ ጥ...
02/09/2019

የኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቀን 27/12/2011 ዓ.ም በከፈተዉ የግፋታ በዓል አከባበር ዝግጅት መድረክ ላይ የግፋታ በዓል ዘላቂ ጥበቃና እንክብካቤ በማድረግ ቅርሱን ትዉልድ ተሻጋሪ እናድርግ!! በሚሉና ተያያዥነት ባላቸዉ በርካታ ሀሳቦችን በማንሳት በደማቅ ሁኔታ አክብሮ ዉሏል።

31/08/2019

በሐዋሳና አካባቢዋ ታዉጆ የነበረዉ ኮማንድ ፖስት ቢነሳም ችግር እንደለለ ተገለጸ።

31/08/2019

በሐዋሳና አካቢ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኪ/ዲ/ወ/ዴ/ተ/ምሁራን ዘርፍ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Event Planning Service?

Share