08/03/2023
HAPPY MARCH 8 FOR FEMALES
ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድ የዚህ ገፅ ወዳጆች ዛሬም እንደተለመደው ገጠመኜን በማስታወሻየ አሰፈርኩላችሁ….መልካም ንባብ
‹‹ምን አሳየህ !?››
ይህንን ቃ መቼም የማያውቀው፤ያልተናገረችው ሴት ያልሰማው ወንድ የለም ብየ እገምታለሁ፡፡ መገመት ብቻ ሳይሆን በእርግጠኝነት ብናገርም ሀሰት ነው የሚለኝ የለም…..አንዳንዴ የገጠሙኝን ነገሮች በመብዛታቸውና በመመሳሰላቸው በማስታወሻየ ላይ አሰፈርኩት፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ወደ ግቢ በመሄድ ላይ ነበርኩ ከፊትለፊቴ ከሚሄዱት ሦስት ሴቶች መካከል የአንደኛዋ አይዲ(ID) ካርድ ተንጠልጥሏል፡፡ እኔም እንዳይወድቅባት ብየ ኤዲሽን በደንብ አስገቢው አልኩ እኔ ከቅንነት እንዳጠፋባት ብየ እርሷ ግን ‹‹ምን አሳየህ?›› አለች በመገላመጥ አስተያየት እንዴ ምን አይነት ነች በፈጣሪ IDዋን በኋላዋ አድርጋ እርሷ ባይታያት እኔ አይቼ ብነግራት ይህን ያህል ያስገላምጣታል ብየ በይሁንታ አለፍኩት
ሌላ ቀን ተተካ ከላይብረሪ ወደ ዶርም ሳዘግም ከፊትለፊቴ የነበረችው ልጅ መቀመጫዋ ላይ ወረቀት ይታያል ሲያዩት ወረቀቱን አድርጋ ተቀምጣ ቆይታ ስትነሳ አብሮ የተነሳ ይመስላል፡፡ ሌሎች ልጆች አይተው እየሳቁ ያልፋሉ እኔ ግን ስቄ ማለፍ ሳልፈልግ ወረቀቱን አስለቅቂው ብየ ያለበትን ቦታ በምልክት ገለፅኩላት እርሷም ወረቀቱን አስለቀቀች የሚገርመው ግን አስለቅቃ አመሰግናለሁ በማለት ፋንታ ‹‹ምን ስትል ወደዚህ አሳየህ ግን?›› አለች እኔም ያልሰማው መስየ ምን? ስላት ‹‹ምን አሳየህ?›› ደገመችው ደግሞ በግልምጫ እንዴ ምን ነካት? እንደ ሌሎች ስቄ ስላላለፍኩ … ብዙ መመላለስ አልፈለኩም ትቻት መንገዴን ቀጠልኩ ይህም ቀን አለፈ
ሌላኛው ቀን ላይ ሆኜ አንዲት ኮረዳ ከፊት ለፊቴ እየሄደች ነበር ከመቀመጫዋ ላይ አቧራ ይታይባታል እርሷንም አቧራውን እንድታስለቅቀው ነገርኳት መቀመጫዋን በሁለት እጇ አሻሽታ ካስለቀቀች በኋላ ምስጋናው ቢቀር ‹‹ምን አሳየህ?›› ማለቷ ከየት የመጣ ነው? ኧረ እናንተየ …ወይ ባላራገፈችው ምን አይነቷ ነች? በጥቂቱ ብየ እንጅ በዙ ናቸው የአረማመዱንና የአቀማመጡን ነገር ልለፈው ጊዜም አየበቃኝ
ወይ ሴቶች ይህን ነገር ማትተውት ወይ ሽክፍ በሉ አልያ ‹‹ምን አሳየህ?›› የሚለውን ነገር ወዲያ…. እኔም ከእንግዲህ ወዲህ IDዋን መውደቅ አይደለም ሱሪዋ ቢወልቅ ዝም!! መቀመጫዋ ላይ እንኳን ወረቀት ተለጥፎ መሄድ ይቅርና ካካ ብታስነካው ጭጭ!! ሱሪዋ ላይ አይደለም አቧራ ጭቃ ቢኖራትም እልፍ እያልኩ ለመሄድ ወሰንኩ ወይ ሴቶች ጉድለታቸውን በተናገርን ግልምጫ አይ…ስናይ መከራ… ሳናይ ስንቀር ደግሞ ለምን አልታየንም መከራ… የቱ እንደሚሻል እኮ ጨነቀኝ ‹‹ተበጠበጥን›› አለ ጆሊጁስ
የነዚህ ይግረም እንጅ ሌሎች ሴቶች እኮ አስሬ መቀመጫቸውን እየጠረጉ ነው የሚሄዱት ይህንም ‹‹ምን አሳየህ?›› እንዳትሉኝ
ደጅ አዝማች፡፡