28/09/2020
በመጨረሻ ሳቀባቸው!!
ፀሐፊ - ኑረዲን ኢሳ፤ ገጣሚ
አቤል ጳውሎስ ግልፅ መድሎ ፈፅሞበታል ::በመጀመሪያው ዙር የቀነሰበት የ2000 ነጥብ አመክንዮ የውድድሩን መጨረሻ የሚያሳይ ና ይሄንን ውድድር አሁን ካለው ውጤት ውጭ ሊሆን እንደማይችል ያሳየ ብቻ ሳይሆን : ዳኛዎችን ጨምሮ ብዙዎቻችንን ያስደነገጠ ሸፍጥ ነበር ::ያነሳው ትችት መድረክ ላይ አልተወዛወዝክም የሚል ከንቱ ትችት ሲሆን ይሄንን ሁሉም ዘፋኞች እንደሚያደርጉ መስክሯል :: በዚህ መሰረት ግን 2000 ነጥብ ከሁሉም ላይ ሲቆርጥ አልታየም ::
አበበ ብርሃኔ በአይተሽ ሊሰጠው ያሰበው ቁጥር ሁሉ ጠፍቶበት እስኪንተባተብ ድረስ: የቀነሰበት የቁጥር መጠን ስንት ይሁን ከስንት እስከማይታወቅበት ድረስ ቡጭርቅርቅ እስኪል ድረስ ፍርድ ገመደለበት ::ፉና ልጁ በህዝብ ድምፅ የተሻለ አድቫንቴጅ እንዳለው እያወቀ : ቢያንስ ሲስተሙ እስከቆመበት ሰአት ድረስ ያለውን የህዝብ ቁጥር ማካተት እየቻለ ባላዬ አልፎታል ::እነዚህ ነገሮች( በተለይ በአንደኛ ዙር የተፈፀመው) በግልፅ በዮናታን ንብረት የሁለተኛና የሶስተኛ ዙር ፕርፎርማንስ ላይ : ድንጋጤ : አለመረጋጋትና የስነልቦና ጫና አሳድረውበት እንደነገሩ አድርጎ እንዲጨርሰው አስገድደውታል :: በአንፃሩ ለሌሎች ተወዳዳሪዎች ደግሞ የላቀ ተስፋና ከሰማይ የወረደ ኮንፎርት ዞን ፈጥሮላቸዋል ::
በመጨረሻ ግን ሳቀባቸው !!