27/05/2022
ሰላም ውድ የዚህ ፔጅ ተከታታዮች ከዚህ በፊት ይህንን ፔጅ ከፍቼ ግን በጊዜ ማጣት ምክንያት ብዙም አልገፋሁበትም ነበረ። አሁን ግን ባለችኝ ጊዜ በጨኪ ላይ የሚደረገውን ከተማዋን የሚያቀጭጭ እንዲሁም ነፃነታችንን ማንነታችንን የሚሳጣንን ስራ ለማክሸፍ የአቅሜን እሞክራለሁ በዚህ ደግሞ ሁላችሁም በጨኪና አከባቢዋ ያላችሁ ማህበረሰብ በሰላማዊ መንገድ ታግለን የሚገባንና ለጥያቄያችን መልስ እንድገኝ የሁላችንም አንድነት ትብብር ያስፈልጋል።
*/የጨኪ ከተማ እንደሚታወቀው የኦሮሚኛ ተናጋሪ ኦሮሞዎች በብዛት የሚኖሩባት ከጥንት ጀምሮ በኦሮሞ ህግና ስርአት የሚተዳደሩ ሰዎች የሚኖሩባት ትልልቅ አባቶችን አስታራቂ በኦሮሞ ስርአት (ሴራ ኦሮሞ) በሽምግልና ህዝብን ከህዝብ በማቀራረብና ችግር ፈቺ የሆኑ ሠዎችን ያፈራች ከተማ ናት። ለምሳሌ እነ ዑርጌ ለታ:በቀለ ገብሬ:አባ ደሱ:መምሬ ጭፍራ:አቶዲባባ:ተፈራ ባልቻ:ጉደታ ተሰማ:ግርማ ዑርጌን:ሹሚ ጨመሬ:አድማሡ በየና; ቄስ ተሾመ ሸዋንግዛውን....የመሳሰሉ ሰዎችን ያፈራች ከተማ ነች ።እንዲሁም ጨኪ ከተማ ብዙ ምሁራንንና ብዙ ግንባር ቀደምና ለሀገራችን እንዲሁም ለአለም ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረጉ ያሉ ወጣቶችን ያፈራች ከተማ ናት።ለምሳሌ ፕሮፌሰር መንግስቱ ዑርጌ /ሀረማያ ዩንቨርስቲ presedant.ተስፋዬ ግርማ ዑርጌ በአሜሪካ ትልቅ ስራ እየሠራ የሚገኝ እነገዙ ደገፋ በዳኝነት:ሰለሞን ዲባባ በጋዘጠኝነት ሙያ ከሚያገለግሉ ወጣቶች.. ........ያፈራች ከተማ ነች።ይሁን እንጂ ከተማዋ የሚገባትን ያህል ትኩረት ባለማግኘቷና በብዙ ምክንያቶች እድ,ገቷ ተገቷል።ከነዚህም ውስጥ የማንነት ጥያቄ ነው።ከላይ እንደገለፅኩት ጨኪ 90%ኦሮሞዎችና ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ናቸው።እንዲሁ ቋንቋ ባህል ወግ ልምዳቸው ኦሮሞ ሆኖ ሳለ ወደአማራ ተከልላ ትገኛለች።ይህ ደግሞ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋ እንዳይማሩና ሰዎች በቋንቋቸው እንዳይዳኙ ህገመንግስታዊና ተፈጥሯዊ መብታቸው እንዳይከበር ያደርጋል።እንዲሁም አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ብዙ ችግሮችን ይፈጥራል።እየፈጠረም ይገኛል።ስለዚህ እኛ መሆን ያለብን ኦሮሚዬያ ክልል ስር ነው።በተጨማሪ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጣችን ራሱ ወደ ኦሮሚያ ክልል የምንጠጋ ነን ማለትም ከደብረብርሀንና ከጫጫ ዳሎታ ሰንቦና ሸኖ ለጨኪ ቅርበት አላቸው።ስለዚህ በደብረብርሀን ክፍለከተማ ስር ለመመደብየሚደረገውንና በአማራክልል ስር የማድረግ እንቅስቃሴዎችን እቃወማለሁ። የጨኪወጣቶች ና ማህበረሰብ በሙሉ ይህንን አጀንዳ በሰላማዊ መንገድ መብታችንን ማንነታችንን ለማስከበር አንድ ሆነን መታገል ይኖርብናል።ሀሳብ አስተያየት ላይክና ሼር በማድረግ ለሌሎች አድርጉ።ጨኪ ኦሮሚያ ክልል ስር መሆን አለባ..,