27/06/2024
መቼ: Friday June 28, Band Starts 9PM
የት፡ Fendika Cultural Center
"ጉንጉን” የሚለውን የስም ስያሜ ለ ቡድኑ ስሰይም የተለያዩ ባህሎችን እና አዳዲስ ጉልበቶች እንዲሁም ችሎታዎች መሰባሰቡን አስተውዬ ነው ::
አሁን የቡድኑ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያውያን ባህልም ባንድ ላይ መሰባሰቡን በማዬቴ ኩሩ ምስክር ነኝ! ዘፋኞች፣ ሙዚቀኞች እና ዳንሰኞች ልዩ ችሎታቸውን በልግስና እና በትህትና በማካፈላቸው በጣም እኮራለሁ! የፈንድቃን ትሩፋት የማስቀጠል እና የኢትዮጵያን ሙዚቃ እና ውዝዋዜ የማክበር እና የማሳደግ ትልቅ ኃላፊነት በትከሻቸው ላይ ነው።
ይህንን ሥራ በስሜታዊነት እና በቁርጠኝነት እየሰሩ እንዲሁም መንገድን እየመሩ ነው። ሁላችንም ከእነሱ መማር እንችላለን! በተለይ መሳይ አበባዬ እና እመቤት ወልደፃዲቅ እንዲሁም ናርዶስ ተስፍው (ውዴ) ይህንን አዲስ ባንድ እያሳደጉ እና አዳዲስ ነገሮችን እየተማሩ የፈንድቃን የእለት ተዕለት ስራ እየተንከባከቡ ነው - ጉንጉንን ወደ ፈንድቃ መድረክ ለማምጣት 24 ሰአት ይሰራሉ::
ኢትዮጵያ እነሱን በማግኘቷ እድለኛ ናት! ፈንድቃ እድለኛ ነው, እኔ እድለኛ ነኝ. በዚህ ሥራ ብቻዬን አይደለሁም። እነዚህ ወጣት መሪዎች የፈንድቃ፣ የባህላችን እና የሀገራችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ናቸው። የተባረኩ ይሁኑ : ይህንን የኢትዮጵያን ባህል ጌጥ ለራስህ መቅመስ ካስፈለጎት ነገ አርብ ምሽት ወደ ፈንድቃ ይምጡ ትኩስ ኃይላቸውን ይወዱታል :
የናንተው , መላኩ
when I offered the name “Gungun” (braided in Amharic) for this new band, I envisioned the braiding and coming together of different cultures, energies, and skills. Now I am a proud witness to the coming together and growth of not only the band but also Ethiopian culture! I am so proud of the singers, musicians and dancers for sharing their extraordinary talents with generosity and humility! On their shoulders rests the big responsibility to carry on Fendika’s legacy, and to celebrate and develope Ethiopian music and dance. They are doing this work with passion and commitment; they are leading the way. We can all learn from them! Mesay Abebaye and Emebet Woldetsdik, or Naredos Tesfawu (Wudi)in particular, are taking care of Fendika’s daily operation while developing this new band and learning new things – they work almost 24 hours a day to bring Gungun to the stage of Fendika! Ethiopia is lucky to have them! Fendika is lucky, and I am lucky. I am not alone in this work. These young leaders are the future of Fendika, our culture, and our country. Stay blessed! If you want to experience this jewel of Ethiopian culture for yourself, come to Fendika on Friday nights (alternate with Ethiocolor). I love their fresh energy, and they will only get better and better with time!
Yours, Melaku