Prana Events

Prana Events Prana Events is a full-service event management, marketing and consulting firm based in Addis Ababa,

30/10/2025
30/10/2025
14ኛው የኢትዮ ፖልተሪ ኤክስፖ (ኢትዮፔክስ)፡ 10ኛው የአፍሪካ እንስሳት ዓውደርዕይና ጉባዔ (አሌክ) እንዲሁም 5ኛው የአፒካልቸር ፡አኳካልቸር ኢትዮጵያ ዓለምዓቀፍ የንግድ ትርዒትና ዘንድሮ ...
30/10/2025

14ኛው የኢትዮ ፖልተሪ ኤክስፖ (ኢትዮፔክስ)፡ 10ኛው የአፍሪካ እንስሳት ዓውደርዕይና ጉባዔ (አሌክ) እንዲሁም 5ኛው የአፒካልቸር ፡አኳካልቸር ኢትዮጵያ ዓለምዓቀፍ የንግድ ትርዒትና ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደው የባዮ ኢነርጂ የንግድ ትርዒት ጥራት ያላቸውን የዘርፉ ዋነኛ አንቀሳቃሾች በማሳተፍ ዛሬ ጥቅምት 20፣2018 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ በደማቅ ዝግጅት ተከፍቷል፡

የንግድ ትርዒቱ የግብርና ሚንስትር አማካሪ ዶ/ር አለማየው መኮንን፣ የSNV Country Director Mrs. Julie Graham፣ የኪንግደም ኦፍ ኔዘርላንድ አምባሳደር ፣አምባሳደር ክርስቲን ፓይሪን ባደረጉት ንግግር ዝግጅቱ በይፋ ተጀምሯል።

ከ14 ሀገራት የተውጣጡ ከ 100 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ኩባንያዎች በአወደርዕዩ የተገኙ ሲሆን ከ5ዐዐዐ በላይ ከኢትዮጵያ፣ ከምስራቅ አፍሪካ እና ከሌሎች የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ ጎብኚዎችም በዓውደ-ርዕዩ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም በእንስሳት ሀብት እና ጤና ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ ውይይቶች ይካሄዳሉ።

የፕራና ኤቨንትስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ነብዩ ለማ እንዳሉት ዝግጅቱ የእንስሳት መኖን፣ የእንስሳት ጤናን፣ ዶሮ እርባታን፣ ወተት፣ ስጋ፣ እንቁላል፣ አሳ ሃብት፣ ንብ እርባታን እንዲሁም ባዮ ኢነርጂን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ትኩረቱን አድርጓል። ዓውደ-ርዕዩ በፕራና ኢቨንትስና አጋሮቹ አዘጋጅነት የሚካሄድ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ የቴክኖሎጂና ግብዓት አቅራቢዎችን ከሀገር ውስጥ ባለድርሻ አካላት ጋር ለማገናኘት ያለመ ነው ተብሏል።

ኤግዚቢሽኑ ከዚህ በፊት በነበሩት መርሀ-ግብሮች የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ ልምድና ተሞክሮ በማጋራት፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ እንዲሁም ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት በዘርፉ ዕድገት ላይ አመርቂ ውጤት አስመዝግቧል።

ዓውደ-ርዕዩ ከዛሬ ጥቅምት 20-22፣2025 ዓ.ም ድረስ ለሶስት ቀናት ለተሳታፊዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል።

ለመመዝገብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
Pranaevents.net/EAP

በዶሮ እርባታ፣ በእንስሳት ሃብት እና እሴት ሰንሰለት ላይ፣ ዓሳ ማርባት እና በንብ ማነብ ላይ ያተኮሩ ከ14 ሀገራት የተወጣጡ ከ90 በላይ ዓለምዓቀፍ የቴክኖሎጂ እና የመኖ ግብዓት እና ሌሎች...
30/10/2025

በዶሮ እርባታ፣ በእንስሳት ሃብት እና እሴት ሰንሰለት ላይ፣ ዓሳ ማርባት እና በንብ ማነብ ላይ ያተኮሩ ከ14 ሀገራት የተወጣጡ ከ90 በላይ ዓለምዓቀፍ የቴክኖሎጂ እና የመኖ ግብዓት እና ሌሎች የእሴት ሰንሰለት ምርት አቅራቢዎች እንዲሁም ገናና ሀገር በቀል ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ዛሬ በ ሚሊኒየም አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ ለ ጎብኚዎች ተከፍቷል።

መግቢያ 200 ብር ብቻ።
ለመመዝገብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
pranaevents.net/EAP

16/10/2025
Exciting News We’re excited to elevate our long-standing partnership with Ethiopian Airlines, Africa’s leading carrier, ...
03/10/2025

Exciting News

We’re excited to elevate our long-standing partnership with Ethiopian Airlines, Africa’s leading carrier, to provide exclusive discounted fares for participants attending the upcoming 14th Ethio Poultry Expo and the Africa Livestock Exhibition and Congress.

This collaboration is designed to make travel to our events smoother, more accessible, and more affordable no matter where you're coming from.

These landmark events bring together key players across the poultry and livestock industries for three days of networking, innovation, and opportunity all in the heart of Addis Ababa.

To make your journey easier and more affordable, Ethiopian Airlines is offering discounted travel for all attendees.

🟡 Promo Code: Mat27
🟢 Book here:
https://www.ethiopianairlines.com/events/14th-ethio-poultry-expo

Don’t miss your chance to be part of Africa’s leading platforms for livestock and poultry sector growth. We look forward to welcoming you on board and on site!

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን።
26/09/2025

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን።

10/09/2025

መልካም አዲስ አመት።

Happy Ethiopian New Year

Address

BL_03_646 Street
Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00

Telephone

+251-929-308-364

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Prana Events posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Prana Events:

Share

Category