31/10/2022
ክፍል 2
በአካል የልጁን መጎዳት ያዩት Easter እና Erick በተመስገን ብርቱ ጥረት እና ትግል ህክምናውን ለማስጀመር መስማማታቸውን ገለጹለት ይህን ዜናም ተመስገን ለኡሪና ቤተሰቦች አበሰራቸው።
ጭንቀት ውስጥ የነበሩት ትንሽ ቀለል አላቸው የልጃቸውን ፊት ፊት እያዩ አሁን ይድንልን ይሁን በሚመስል መልኩ ፈዘው ይመለከቱትም ነበር ተመስገንም የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ለራሱ ቃል ገባ ፕሮሰሱ ተጀመረ ለአባት መታወቂያ ማውጣት ለህክምና የሚሆን የድጋፍ ደብዳቤዎች በማስጻፍ ሙሉ ሀላፊነትን በመረከብ አሳክሞ እስከመመለስ ድረስ ሁሉም በሰላም ተጠናቀቀ አሁን የሚቀራቸው መጓዝ ብቻ ነው መጓዝዝዝዝዝዝዝ
ጉ...ዞ.....ተጀመረ
በርግጥ በጉዞው ወቅት ለተመስገን ሁሉ ነገር ቀላል አልነበረም ፈተናዎች ብዙ ነበሩ ሰዎቹ የልጁን ፊት በማየት ብቻ አልጋ ለማከራየት አለመፍቀድ፣ምግብ ቤት ለማስገባት ፍቃደኛ አለመሆን ብቻ ብዙ ብዙ ነገር ግን ከጓደኛው ጋር በመመካከር በተጠቀሙት ዘዴ በስተመጨረሻም ለአዳር የሚሆን መኝታ ቤት አግኝተው የሚበላውን ገዝተው ተመግበው አዳራቸውን አርባ ምንጭ በማድረግ በለሊት ጉዞ ወደ ሸገር አደረጉ
ሸገር እንደደረሱ ለኡሪና ለአባቱ ሁሉ ነገር አዲስ ነበር ያው ህክምናው ረዥም ጊዜ ስለሚወስድ ቀን በቀን ለመኝታ ቤት ከመክፈል እና ከወጪው አንጻር ያለው አማራጭ ቤት ተከራይቶ ከለመዱት ማህበረሰብ ውጪ አዲስ ማህበረሰብ ጋር ተቀላቅለው ሁሉን ባህል እንዲላመዱ ማድረግ ነበር እና ይህንንም አድርጎታል ህክምና የሚያደርግበት ሆስፒታልም አቀኑ የተከሰተውን በሙሉ ተመስገን ለዶክተሮቹ አስረዳቸው የፊት ሰርጀሪ እንዲሰራለት ዶክተሮቹ ይነግሯቸዋል በዚህም ተመስገን እና የኡሪ ቤተሰቦች በመነጋገር የፊት ሰርጀሪው እንዲሰራለት ተስማሙ... እንደታሰበው ሰርጀሪው ግን ቀላል አልነበረም ማለትም የፊት ሰርጀሪውን ከአንድም ሶስት ጊዜ አድርጓል በዛን መሃል በየአንዳንዱ ሰርጀሪ ከአንድ ወር እስከ ሁለት ወር የሚፈጅ ጊዜ ቀጠሮ የነበረው ሲሆን ይሄን ሁሉ ጊዜ ያለመታከት ከጎናቸው ላለፉት ከባድ ጊዜያት አንድ ብርቱ ወጣት ነበር ተ...መ....ስ....ገ...ን
በቀነ ገደብ ቀጠሮው ሰርጀሪው ለሶስት ዙር የተሰራለት ሲሆን የመጨረሻው ሰርጀሪ እንደተሰራለት ከትንሽ ቆይታ በኋላ ኡሪ ከልጅነት ጓዶቹ ጋር ለመቦረቅ ለመጫወት ተስፋን ሰንቆ ቤተሰቦቹ ልጃቸው ወደ ቀድሞው የፊቱ ገጽታ እንደሚመለስ አምነው ከህክምናው በኋላ ወደ አከባቢያቸው በዚህ ብርቱ ወጣት አማካኝነት ተመለሱ።
በዚህ ላለፉት ሶስት ዓመታት ያለ መታከት እና ያለ መሰልቸት ከኡሪና ቤተሰቦቹ ጎን የነበረው ተመስገን እንዲህ እያለ ያስታውሳል ከህክምና ጀምሮ የ አውሮፕላን ትኬት ወጪ ፣ የመኪና ትራንስፖርት ወጭ ፣ አልጋ ፣ የምግብ ፣ ታክሲ ከተማ በምሄዱበት ግዜ ለአባትና ልጅ ሙሉ ልብስ እስከነ መቀየሪያቸው ... ወዘተ ወጭዎችን በመቻል ይህ ነው የማይባል እስከ 3000,000 ብር የሚገመት ገንዘብ Easter እና Erick ፈሰስ እንዳደረጉ ይገልጻል።
ነገር ግን በዚህም አላበቃም ኡሪ ከህክምና መልስ ቁስሉ እስኪሽርለት በባክቴሪያ ኢንፌክሽን እንዳይጠቃበት በዞን የሚገኘው ሆስፒታል በማመላለስ የእጥበት ሂደቱን እንዲከታተል ያደረገ ሲሆን ያ ሁሉ ጉዳይ ተጠናቆ ኡሪ ቁስሉ ከሻረለት በኋላ ወደ ትውልድ መንደሩ በመመለስ ከጓደኞቹ እኩል እየቦረቀ ይማር ዘንድ የትምህርት ቁሳቁሱን በሟሟላት ከትምህርት ጽ/ቤት ኋላፊ አቶ አንተነህ ጌታቸው ጋር መንደራቸው ድረስ በመሄድ ለኡሪና ቤተሰቦቹ ቁሶችን አበርክተዋል።
ጽናት፣ትጋት፣ ሰብዓዊነት፣የአንድን ወጣትን ህይወት ከማዳን አልፎ እንደ አዲስ ተስፋን እስከመዝራት የተከፈለ መስዕዋትነት❤❤❤❤...
ኡሪና ቤተሰቦቹ አሁን ላይ ያመሰግኑታል እንደ ቤተሰባቸውም ይቆጥሩታል አሁን ላይ በደስታ እየኖሩ ነው ዕድሜ ለዚህ ብሩህ ታጋይ ወጣት እና ሰብዓዊነት ተሰምቷቸው ከባህር ማዶ ሆነው ለረዱት Easter እና Erick❤❤❤
ጽሁፌን በዚሁ አበቃው ቸር ሰንብቱ