Ethos Entertainment and Events

Ethos Entertainment and Events Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethos Entertainment and Events, Event Planner, Addis Ababa.

Jump on the dance floor with Mesay Tefera and Tarkege along side with Alazar, Hirut & Abel its all yours and your friend...
26/01/2022

Jump on the dance floor with Mesay Tefera and Tarkege along side with Alazar, Hirut & Abel its all yours and your friends night which we call it the Amazing Wednesday .
Behind the Music Guramyle Band got you covered and all the entertainment is set by One Luxx Addis.

Early Arrival recommend
RSVP +251911679540
+251948665620
+251 91 9454709
+251 92 280 0206


🌻"ብዙነሽ በቀለ /ብዙዬ"🌻 (1928-1982 ዓ.ም)🎼ጭንቅ ጥብብ፣ችላ አትበለኝ፣የናት ውለታዋ፣ የፍቅሬ ነበልባል፣ የሚያስለቅስ ፍቅር፣ የምሰረቅ ቢሆን፣ ይወደኝ አይወደኝ አላውቅም፣ ደብዳቤ ...
26/06/2020

🌻"ብዙነሽ በቀለ /ብዙዬ"🌻 (1928-1982 ዓ.ም)
🎼ጭንቅ ጥብብ፣ችላ አትበለኝ፣የናት ውለታዋ፣ የፍቅሬ ነበልባል፣ የሚያስለቅስ ፍቅር፣ የምሰረቅ ቢሆን፣ ይወደኝ አይወደኝ አላውቅም፣ ደብዳቤ ላክብኝ፣ ድንገት ሳላስበው፣ፍቅሬ ደህና ሁን፣ ፍቅር ሀብት እኮ ነው፣
ለምን ጊዜም የማልረሳሽ፣ ለሚወዱህ ቀርቶ፣ ለሰው ቢናገሩት፣ ሌላ አሰበ ወይ፣አዲስ ፍቅር ይዞኛል፣ እርግብግብ አለብኝ ዓይኔ አይረሴ ከሆኑ ስራዎቿመካከል መጥቀስ ይቻላል‼።
📝ብዙነሽ በቀለ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ ደምቃ እና አዳምቃ ያለፈች ብርቅዬ ከያኒት ነበረች። ዘፈኖቿን ልዩ በሆነ የመድረክ አቀራረቧ እና ግርማ ሞገሷ ትቆጣጠራለች። የሙዚቃ ምትሃት እላይዋ ላይ የሚታይበት ፍፁም የምትወደድ ከያኒት ነበረች።
ብዙነሽ በቀለ የተወለደችው በ1928 ዓ.ም ሐረር ከተማ ውስጥ ሸዋ በር ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ነው።
-የአንደኛ ደረጃ ትምህርቷንም እዚያው ሐረር ከተማ እየተከታተለች ባለችበት ጊዜ ሙዚቃ ጠራቻት። እናም ህዳር 1 ቀን 1949 ዓ.ም በቀድሞው ክቡር ዘበኛ ጠቅላይ መምሪያ በድምጻዊነትና በተወዛዋዥነት ተቀጠረች።.ገና ብዙ ባልተቆጠረው ዕድሜዋ በክብር ዘበኛ ጠቅላይ መመሪያ የሬዲዮ ጣቢያ እንደቀጠራት ይነገራል፡፡ የዚያን ጊዜ የሥራ ድርሻዋም ድምፃዊነት ነበር፡፡ በተለይ በየሳምንቱ ሐሙስ ሐሙስ በጃንሜዳ ይታይ በነበረው የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ድምፃዊቷ ፋና ወጊነቷን ያሰመሰከረችበት ጥበባዊ ጉዞዋ ነበር፡፡ የክብር ዘበኛ ጠቅላይ መምሪያ የሬዲዮ ጣቢያ በጊዜው በኢትዮጵያ ሙዚቃ ዕድገት ለብዙ ድምፃዊያን መሰረት የጣለና ለድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ ደግሞ ግንባታንም ያሳመረ ነበር፡፡
ብዙነሽ ክቡር ዘበኛን እንደተቀለቀለች የሙዚቃ ክፍሉ እጅግ ተጠናከረ። በተለይ ጥላሁን ገሠሠ፣ ብዙነሽ በቀለ እና መሐሙድ አህመድ በድምፃዊነታቸው ተአምረኛ ሆነው ብቅ ብቅ አሉ። አያሌዎችን ምትሃታዊ በሆነ ድምጻቸው ማረኩ።
-በብዙነሽ በቀለ የሙዚቃ ህይወት ውስጥ ሁሌም የሚጠቀሱ ሰዎች አሉ። እነዚህ ሰዎች ግጥምና ዜማ የሚሰጧት፣ የሚያስጠኗት እና የሚያቀነባብሩላት ናቸው። ገዛኸኝ ደስታ፣ ሰለሞን ተሰማ፣ ሳህሌ ደጋጎ፣ ሰይፉ ኃይለማርያም እና ተዘራ ኃይለሚካኤል በብዙነሽ ታላቅነት ውስጥ አሻራቸው በጉልህ የሚታይ ከያኒዎች ናቸው።
-ብዙነሽ በቀለ እና ጓደኞቿ በኢትዮጵያ ውስጥ ከገጠር እስከ ከተማ በእግር፣ በከብት እና በመኪና እየተጓጓዙ ህዝባቸውን ሲያስደስቱ ሲያስተምሩ የኖሩ ናቸው። ብዙዬ ዜጎቿ ሲጎዱባት በመዝፈንና እርዳታ በማሰባሰብ የምትታወቅም ነች። በ1966 ዓ.ም በድርቅ ለተጎዱ ኢትዮጵያዊያን በሙያዋ ዘፍና ገንዘብና እርዳታ አሰባስባለች።
ከዚህም አልፋ በልዩ ልዩ ሀገሮች እየተዘዋወረች የኢትዮጵያን ባህልና ሙዚቃ አስተዋውቃች። ፍልቅልቅ እና ማራኪ ገጽታዋን በሙዚቃዎቿ እያዋዛች ትውልድን ስታስደስት ኖራለች።
-በ1969 ዓ.ም በናይጄሪያ ዋና ከተማ ሌጎስ ውስጥ ተደርጎ በነበረው የመላው ዓለም ጥቁር ህዝቦችና የአፍሪካ የኪነትና የባህል ክብረ በዓል ላይ ተካፍላ ከፍተኛ ተደናቂ ሆናለች። ለዚህም ብቃቷ ተሸላሚ ነበረች።
የብዙነሽ በቀለ ሙዚቃዎች ኢትዮጵያን መውደድ፣ እናትን መውደድ፣ እና ፍቅርን ራሱን መውደድን ያንፀባርቃሉ። ሙዚቃዎቿ አያሌ ናቸው። ግን ገና ተሰባስበው ጥናትና ምርምር አልተደረገባቸውም። ይህችን የምታክል የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንግስት ታሪኳ አልተፃፈላትም። ዮሴፍ ቤተ-ክርስቲያን የሚገኘው የቀብር ቦታዋም ተገቢውን ክብር አላገኘም። እናም የሀገርና የህዝብ ባለውለተኛዋን ድንቅዬ ድምፃዊት ዘላለማዊ ለማድርግ ከሁላችንም ብዙ ይጠበቅብናል።ብዙነሽ በቀለ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ እንደ ተአምር የሚቆጠር አስተዋፅኦ አድርጋ ሰኔ 19 ቀን 1982 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። ድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ በዘመኗ የሚስተካከላት እንስት ድምጻዊ አልነበረም፡፡ የመድረክ አያያዟና እንቅሰቃሴዋን የሚያስሰታውሱ ሁሉ ኮኮብነቷን ይመሰክሩላታል፡፡ብዙነሽ በቀለ ከሙዚቃ ህይወቷ በሞት እሰከተለየችበት ጊዜ ድረስ ለሙያዋ ቀዳሚና አክባሪ፣ ለሙያ ባልደረቦችዋና ለሀገሯ ህዝብ ፍቅር ያላት ምርጥ የጥበብ ሰው ነበረች፡፡*የድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ ዘመን አይሽሬ ሥራዎች ዛሬም በጣፋጭ ትዝታ ይደመጣል፡፡ ከአብራኳ ከወጡ ልጆቿም የራሷን የሙያ ፈለግ ተከትላ የወጣች ሥሟን የምታስጠራ ድምፃዊት ልጇን ተክታልናለች፡፡
*ነፍስ ይማር
ምንጭ:-ጥበቡ በለጠ;ሸገር 102.1; ከተለያዩ

©የጠላሽ ይጠላ ሃገሬ

ጀንበሬ በላይ ፣ ወጋየሁ ንጋቱ ፣ አስናቀች ወርቁ ፣ አበበ ባልቻ እና አባባ ተስፋዬ ምስል ከ Teborne Beyene ገፅ
05/09/2019

ጀንበሬ በላይ ፣ ወጋየሁ ንጋቱ ፣ አስናቀች ወርቁ ፣ አበበ ባልቻ እና አባባ ተስፋዬ
ምስል ከ Teborne Beyene ገፅ

ባለቅኔ እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ)ጎጃም ያረሠውን ለጎንደር ካልሸጠጎንደር ያረሠውን ጉራጌ ካልሸጠየሸዋ አባት ልጁን ለትግሬ ካልሠጠየሐረር ነጋዴ ወለጋ ካልሸጠፍቅር ወዴት ወዴት፤ ወዴት ዘመም ዘመም...
25/12/2018

ባለቅኔ እጅጋየሁ ሽባባው(ጂጂ)

ጎጃም ያረሠውን ለጎንደር ካልሸጠ
ጎንደር ያረሠውን ጉራጌ ካልሸጠ
የሸዋ አባት ልጁን ለትግሬ ካልሠጠ
የሐረር ነጋዴ ወለጋ ካልሸጠ
ፍቅር ወዴት ወዴት፤ ወዴት ዘመም ዘመም
ሃገርም አለችኝ ሃገር የኔ ህመም
ዘሩ እንዳይበጠስ መቋጠሪያው ደሙ
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው ቀለሙ...
:
:
እኔን የራበኝ
ፍቅር ነው የራበኝ
ፍቅር ነው የራበኝ
ፍቅር ነው የራበኝ

ያልተዘመረላት - አስቴር አወቀ !በየመድረኩ እየተጠራሩ ሲሸላለሙ በብዛት ስሟ ሲነሳ አላያትም -ምናልባት በስጋዋ ስታልፍ ልናወድሳት እና ልንዘምርላት ይሆን ???በነጠላ ዜማዎች ደረጃ አድናቆት...
08/12/2018

ያልተዘመረላት - አስቴር አወቀ !

በየመድረኩ እየተጠራሩ ሲሸላለሙ በብዛት ስሟ ሲነሳ አላያትም -ምናልባት በስጋዋ ስታልፍ ልናወድሳት እና ልንዘምርላት ይሆን ???

በነጠላ ዜማዎች ደረጃ አድናቆት የሚጎርፍላቸው የዘመኑ ሙዚቃውያን ያህል "ያልተዘመረላት" በአመታት ውስጥ ዜማዎቿ እና ግጥሞቿ የሚገዝፉ እና ዘመን ተሻጋሪዎች : ፍቅር በሌለበት እንኳ ፍቅር የያዘው ሰው አይነት ስሜት የምታጭር -የዘመናት ቁንጮ - አስቴር አወቀ !

እደግመዋለሁ...
በየመድረኩ እየተጠራሩ ሲሸላለሙ በብዛት ስሟ ሲነሳ አላያትም -ምናልባት በስጋዋ ስታልፍ ልናወድሳት እና ልንዘምርላት ይሆን ???

Š Zami zem

ሳህሌ ደጋጎ-----ክቡር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ ከተጫወታቸው ሙዚቃዎች ውስጥ “ስቆ መኖር”፣ “እውነት ማሪኝ”፣ የሚሉትን ግጥሞች፣ “ዋይ ዋይ ሲሉ”፣ “ውሸት ለመናገር”፣ “ልብሽን ለአፈርሰው”፣...
05/12/2018

ሳህሌ ደጋጎ
-----
ክቡር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ ከተጫወታቸው ሙዚቃዎች ውስጥ “ስቆ መኖር”፣ “እውነት ማሪኝ”፣ የሚሉትን ግጥሞች፣ “ዋይ ዋይ ሲሉ”፣ “ውሸት ለመናገር”፣ “ልብሽን ለአፈርሰው”፣ “ኮቱሜ”፣ የሚሉትን ዘፈኖች ግጥምና ዜማዎች የደረሰው ሌ /ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ ነው፡፡
-
ከዚህም ሌላ ለድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ “አይወጣኝም ክፉ ነገር” በሚል የዘፈነችውና በብዙኀን ዘንድ ተወዳጅነት ያለውን (“ወደመጣሁበት ምድር፣ እስክመለስባት በክብር፣ ሰውን ከማስደሰት በቀር፣ አይወጣኝም ክፉ ነገር፣ ሙዚቃውን ያቀናበረው ሌ /ኮሎኔል ሣህሌ ነው።
-
ሌ /ኮሎኔል ሣህሌ “ፍላጎቴ”፣ “ምን ነበር”፣ “ምንድነው ትዝታህ”፣ ... የተሰኙትን የብዙነሽ በቀለን ዘፈኖች ያቀናበረ ሲሆን፣ “ከንቱ ሥጋ” የሚለውንና ሌሎችንም ዘፈኖችዋን ግጥም ደርሶላታል። “አታሳየኝ ጭንቁን”፣ “የፍቅር ወጋገን”፣ “ቃልኪዳን”፣ “በብር አይጋዛም”፣ “ፍቅርህ ቀሰቀሰኝ”፣ የተሰኙትን ዜማና ግጥሞች ያዘጋጀው ሣህሌ ደጋጎ ነው፡፡
-
“ሰው ከተሰማራ” በተሰኘው ዘፈኗ ለምትታወቀው ለድምፃዊት መንበረ በየነ ደግሞ “እንዴት ከረማችሁ” የሚለውን ዘፈን ግጥም የደረሰው ሌ /ኮ /ል ሣህሌ ነበር።
“የቆራጡ መሪ ፍሬው ጎመራ” የተሰኘውንና ለቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም ላቀነቀነችው ለድምፃዊት ውብሻው ስለሺ ደግሞ “ይህ ነው ጌትነት”፣ “የምድር ፈተና” የተሰኙትንና በ 1966 ዓ /ም የታተሙትን ዘፈኖችዋን ያቀናበረላት ሌ /ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ ነበር።
-
በዕድሜ ዘመን የኪነ ጥበብ አገልግሎት የክብር ሜዳሊያ እና የ 20 ሺህ ብር ተሸላሚ የሆነው ሣህሌ ደጋጎ፤ የ 30፣ የ 20 እና የ 10 ዓመት የረዥም ዘመን አገልግሎት የወርቅ፣ የብርና የነኀስ እንደዚሁም የተዋጊ ወታደርነት የደረት ዓርማ ኒሻን ተሸለሚም ነበር።

ፀሐፊ ፡ታጁዲን አሊይ

አሁን ......ለማ ገ/ህይወትን አየሰማሁ ነው።  ስርቅርቁ ዜማቸው ቢቀርባችሁ ግጥማቸውን እንካችሁ!ኮራ ያለ ዳሌ ሰበር ያለ አንጀት፣ጠፈፍ ያለ ከንፈር ያልወደቀ ጡት፣ሰብስቦ ሰጥቷታል ሁሉን ...
03/12/2018

አሁን ......ለማ ገ/ህይወትን አየሰማሁ ነው።
ስርቅርቁ ዜማቸው ቢቀርባችሁ ግጥማቸውን እንካችሁ!

ኮራ ያለ ዳሌ ሰበር ያለ አንጀት፣
ጠፈፍ ያለ ከንፈር ያልወደቀ ጡት፣
ሰብስቦ ሰጥቷታል ሁሉን ላንድ ሴት፣
እንዴት ያምላክ ፍጡር በእሷ ራብ ልሙት።
***
የገደል ዝንጀሮ ወጣበል ከሳሩ፣
ጠይም የወደደ ገናነው አሳሩ።
***
ፍቅሬ ትዝታዬ በጣሙን ውድ ነሽ፣
ፍቅርሽ ዋጋ አያውቅም ብርቱካን አልማዝ ነሽ።
***
እንደዚህ እንደዚህማ ከሆነ ነገሩ፣
ልብሽና ልቤ ዘብ ይተዳደሩ።
***
እያሉ ጋሽ ለማ ገ/ህይወት በመሰንቆ ታጅበው ይስረቀረቃሉ።
መቼም ዛሬ ላይ በህይወት ቢኖሩ....
".........ባንዘልቅ እንኳን አብረን እንደር" ብሎ የዘፈነውን
ምንኛ ይታዘቡት ነበር??
#ብትችሉ የጋሽ ለማ ገ/ህይወትን ዘፈኖች ፈልጉና ስሙ።

ŠAbebaw Fiseha

አስናቀች በክራር ራሷን አጅባ በምታንጎራጉራቸው ዘፈኖች የምታተኩረው ተቀጣጥሎ ያልተፋፋመ ወይንም የሰከነ ፍቅር ላይ ነው። ለአብነት ‘እንደ ኢየሩሳሌምን’ና ‘እሱ ርቆ ሄዶ’ን መመልከት ነው። ...
02/12/2018

አስናቀች በክራር ራሷን አጅባ በምታንጎራጉራቸው ዘፈኖች የምታተኩረው ተቀጣጥሎ ያልተፋፋመ ወይንም የሰከነ ፍቅር ላይ ነው። ለአብነት ‘እንደ ኢየሩሳሌምን’ና ‘እሱ ርቆ ሄዶ’ን መመልከት ነው። የፍቅር ጉዞዋ በዘፈኖቿ ውስጥም ይታያል። የምታፈቅራቸው ሰዎች አያዛልቋትም፤ የሰው ሰው ሊሆኑ ይችላሉ ወይንም ስሜታቸው አብሯት አይፈካም። ለዚህም ነው ፍቅረኞቿን “ይፋ የማይወጣ ሰው”፣ “ፍቅር የማይገባው አጉል ሰው” እያለች የምትጠራቸው። አስናቀች ለወደደችው ፍቅሯን ከመግለጽ አትቆጠብም፣ ከመለማመጥም አትመለስም። አንዴ ፍቅሩ ከሰከነ ግን እርግፍ አድርጋ ትተዋለች። ሕይወቷም ዘፈኖቿም ምስክሮች ናቸው።
“መሞከር ይሻላል ሁሉንም መሞከር፣
ይፈጠር ይሆናል አንድ ደህና ነገር።”

መንገደኛው ልቤ 1966 ዓ. ም.

'©አንድምታ መፅሄት የአርቲስቷን ታሪክ ሠፋ አድርጎ አቅርቦታል በዚህ link ማግኘት ትችላላችሁ
https://andemta.com/2017/03/01/%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%8A%93%E1%89%80%E1%89%BD-%E1%8B%88%E1%88%AD%E1%89%81/

አርቲስት ተሾመ አሰግድተሾመ አሰግድ በ1942 ዓ.ም ነው በድሮዋ ወለጋ ጠቅላይ ግዛት ተወለደ ። ገና የአምስት ወር ልጅ እያለ የአይኑን ብርሃን ያጣው ተሾመ እናት ሆነው ያሳደጉት በዝምድና ቋ...
01/12/2018

አርቲስት ተሾመ አሰግድ
ተሾመ አሰግድ በ1942 ዓ.ም ነው በድሮዋ ወለጋ ጠቅላይ ግዛት ተወለደ ። ገና የአምስት ወር ልጅ እያለ የአይኑን ብርሃን ያጣው ተሾመ እናት ሆነው ያሳደጉት በዝምድና ቋጠሮ አክስት በወል ግን እናቱ የሆኑት ወይዘሮ አማካለች ይመር ናቸው። ስድስት ወንድ እና ስምንት ሴት በተወለደበት ቤተሰብ ውስጥ ተሾመ ለአቶ አሰግድ ይመር አራተኛው ልጅ ነው። ምንም እንኳን በአክስቱ ወ/ሮ አማከለች ጥረት፣ የመንደሩን ልጆች የኔም ናቸው ብሎ በሚያሳድገው ጎረቤት ክብካቤ ቢያድግም ተሾመ ራስን መቻል ይሉትን ጥበብ፣ በገዛ እግር መቆም ይሉትን ብልሃት ገና ብላቴና ሳለ ነው የሚያውቀው። በደምቢዶሎ ቡና በረንዳ ከትላልቆቹ ነጋዴዎች ጆንያ ሾልኮ የሚፈስ ቡና እየለቀመ በመሸጥ ትምህርት ቤት ሲሄድ የሚያጌጥበትን ሸራ ጫማ መግዛት ችሎ ነበር። ተሰጥኦ የሚሉት መክሊት ገና በጠዋቱ እድል ፈንታውን ያሰመረለት ተሾመ በመንደሩ ሰርግ ቤቶች አይታጣም ነበር።
“የኔን የህይወት መስመር እግዚአብሔር በመልካም ሲያበጅልኝ ነው የኖረው” ብሎ የሚያምነው ተሾመ አሰግድ፤ ሚስተር ራሰል ከሚባሉ ኦሮሚኛን አቀላጥፈው ከሚናገሩ ካናዳዊ የወንጌል መምህር ጋር የተገናኘባትን ጀምበር የዛሬ ማንነቴ መሰረት የተጣለባት ነች ይላል። እኚህ ሰው ተሾመን ገና በስድስት ዓመቱ መንገድ አግኝተውት ይህ ህፃን ትምህርት ማግኘት አለበት ብለው ጂፕ መኪናቸው ውስጥ አስገብተው ይዘውት ተፈተለኩ። አዲስ ነገርን የመከተል የልጅነት ጉጉት የኋሊት ወደቤተሰቦቹ ጎትቶ ያላስቀረው ተሾመም ሚስተር ራሰልን በፈቃደኝነት ተከተላቸው።
በሃገሩ ወግ ባህል ወደ ሰውነቱ ይዘልቅ የጀመረው የጥበብ እርሾ ከፈርንጁ ዘመናዊ የሙዚቃ ዕውቀት ጋር ተዋህዶ የወደፊት የሙያ እንጀራው ይጋገር ዘንድ ተሾመ ገና በልጅነቱ ከታች በእግር እየተረገጠ ከሚሰራው የድሮ ፒያኖ ጋር ተዋወቀ። ይህ የሆነው የሚስተር ራሰል ባለቤት ቤቷ ይህንን የሙዚቃ መሳሪያ ትጫወት ስለነበር ነው። ፒያኖውን ስትጫወት እስሩዋ ሆኖ በአርምሞ ያዳምጣት የነበረው ይህ ልጅ እሱዋ ዘወር ስትል ተደብቆ የልጅ ጣቶቹን ፒያኖው ቁልፎች ላይ ያሩዋሩጣቸው ጀመር። ገና በአስራ ሶስት ዓመቱ ጥሩ ሙዚቃ መጫወት የመቻሉ ሚስጥር ቁዋጠሮ እንዲህ ባሉ የትላንት ወዲያ ታሪኮቹ ውስጥ ነው የሚገኙት።
ቁምጣ፣ ጥበቆና ሸሚዝ ተገዝቶለት በትምህርት ቤት ገበታ ሊቀመጥ የቻለው ተሾመ ማየት ለሚችሉት ብዙ ቦታዎችን ለአይነ ስውራን ደግሞ ጥቂት ቦታዎችን አሰናድቶ ያስተምር በነበረው የአሜሪካን ሚሽን ትምህርት ቤት ውስጥ ነበር። እናም እስከ አስር ዓመት እድሜው ድረስ እዚያው ተማረ።
አንድ ቀን በአጋጣሚ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ተሾመ የሚማርበትን ትምህርት ቤት ለመጎብኘት ደምቢዶሎ ይሄዳሉ። ህፃናቱን እየዞሩ እያናገሩ ነበርና ለታዳጊው ተሾመም ጥያቄዎችን አቀረቡለት። በኦሮምኛ ነበር ያናገሩት። “ኦሮምኛ ትችላለህ?” የሚለውን ጥያቄ አስቀድመው “እኛ ማን ነን?” ብለው ጠየቁት። እሱም ምን ልጅ ቢሆን ወቅቱ የሚፈልገውን ቁዋንቁዋ ያውቅ ነበርና “የኢትዮጵያ ብርሃን ግርማዊ ጃንሆይ” አላቸው። “ምን እንድናደረግልህ ትፈልጋለህ?” ጠየቁት። በወቅቱ ከፍተኛ የመሰለውን ነገር እንዲፈፅሙለት ነገራቸው። ንጉስ ነበሩና አልክብዳቸውም። ሸራ ጫማው ተገዛለት።የሚማርበት ትምህርት ቤት ተማሪዎቹን ይዞ ይጉዋዝበት የገንዘብ አቅም ስላለነበረው ጥያቄውን ለቀዳማዊ ሃይለስላሴ አቅርቦ ከስምንት ተማሪዎች ገሚሶቹ ወደ ባኮ ሲሄዱ ገሚሶቹ ደግሞ ወደ ሰበታ ተሸኙ። ተሾመ ለሶስት ዓመታት ባኮ ቢመቀመጥም ለጆሮ ህክምና ስዊድን ደርሶ ከመጣ በሁዋላ ወደ ሰበታ ተዛወረ።
በወቅቱ አጠራር “መርሃ ዕውራን” ተብሎ በሚታወቀው ትምህርት ቤት ዛሬ በካናዳ ከሚኖረው አብዱቄ ከፈኔ እና ከሌሎች ባልንጀሮቹ ጋር ሙዚቃን በቅጡ መለማመድ ጀመረ። የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተርን ጨምሮ እነ ፕሮፍሰር አሸናፊ ከበደ፣ ተስፋዬ ለማ፣ ዓለማየሁ ፋንታ እና መላኩ ገላውን የመሰሉ ሰዎች ተሾመን በማበረታቱ እና የሙያ ፈር በማስያዙ ረገድ በኩል ጉልህ ሚና ተጫውተዋል።
እናም ገና በወጣትነቱ ፍሬውን ማየት ማሳየት ጀመረ። ከስድስት የሰበታ አይነ ስውራን ትምህርት ቤት ጉዋደኞቹ ጋር ሆኖ “ሬንቦው” የተባለ ቡድን አቁዋቁመው ለረዥም ጊዜ ሰርተዋል። “ይህች አጋጣሚ” የተሰኘው የጥላሁን ገሰሰ ዜማ አስቀድሞ ተሾመ አሰግድ ገና በለግላጋነቱ ሊጫወተው የነበረ ዜማ ነው። በአሁኑ ሰዓት ዊስኮነሰን የሚኖረው የህግ ባለሙያ ዶክተር በቀለ ሃይለየሱስ የደረሰው ይህ ስራ በመጀመሪያ ሊቀነቀን የነበረው በተሾመ አሰግድ ቢሆንም የፊሊፕስ ኩባንያ ባለቤት በተፅዕኖ ዜማው ለጥላሁን ገሰሰ እንዲሰጥ ቢያደርጉም ጥላሁን የተሾመን ያማረ አጨዋወት አይቶ የገበያው መሪ ባለሃብት የወሰኑትን መቀልበሱ ባይቻለው እንባውን አፍስሶ ከሙዚቃ ሽያጩ ያገኘውን ሙሉ ገቢ በወቅቱ እሱን ላጀቡት ለእነ ተሾመ አሰግድ – ለሬንቦ ባንድ ስጥቱዋል።
ተሾመ “ውጋጋን” በተባለው የኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ማህበር የሙዚቃ ቡድን ውስጥም አገልግሉዋል። ተሾመ ከውጭ የትምህርት ቆይታው በሁዋላ ሙያዊ አበርክቶውን ከለገሰባቸው ተቁዋማት መካከል የዓይነ ስውራን ማህበር አንዱ ሲሆን አመራር በመስጠትም ሙያዊና ወገናዊ ሃላፊነቱን ተወጥቱዋል።
ተሾመ እንደአብዛኛው የወቅቱ ወጣት በእድገት በህበረት ዘመቻ ተሰልፎ ነበር። ያንን የወቅቱን ግዴታ ከተወጣም በሁዋላ ነበር ጀርመን አገር ሄዶ የፒያኖ ቅኝት እና ፒያኖ አሰራር ትምህርቱን የተከታተለው። አሁን ኬምኔትስ ተብላ በምትጠራው፤ በቀዝቃዛው ጦርነት የበርሊን ግንብ ዘመን ካርልማረክሽታት ትባል በነበረችው ከተማ በብሎንደን ሴነትሩም ወይም የዓይነ ስውራን ትምህርት ማዕከል ነበር እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1980 ዓ.ም ወደ ከፍትኛ ትምህርት ምዕራፍ የተቀላቀለው። የጀርመንኛ ቁቃንቁዋን ያጠናበትን ስድስት ወር ጨምሮ በአጠቃላይ ለሁለት ዓመት ከመንፈቅ ነበር ተሾመ ትምህርቱን በጀርመን ሃገር ተከታትሎ በዲፕሎም የተመረቀው።
ተሾመ ትምህርቱን በብቃት ጨርሶ ሃገሩን ለማገልገል ወደ ኢትዮጵያ በመንፈሰ ሙሉነት ተመልሶ በቅድሚያ ወደ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ነበር ያቀናው። ተቁዋሙ ግን በልምድ ከሌላ መምህር የተማሩትንና በዘልማድ የሚሰሩትን ዓይናማ ሰው በፒያኖ ቃኚነት ቀጥሮ እያሰራ በጀርመን ሃገር ትምህርት ቤት ገብቶ ሙያውን በብቃት ቀስሞ የመጣውን ተሾመ አሰግድን አልፈልግህም አለው። ለነገሩ ይህ የሙዚቃ ትምህርት ቤት እንደ ፐሮፌሰር አሸናፊ ከበደ አይነት በእኩልነት የሚያምኑ ሰዎች የነበሩበት መሆኑ ባይታበልም አይነ ስውራን ሙዚቃን መማርም ሆነ ማስተማር አይችሉም በሚል እና እነሱን ተቀብለን ለማስተናገድ በበቂ አልተዘጋጀንም በሚል አስባብ እስከዘንድሮ አይነ ስውራንን ከሙዚቃ ትምህርት ገበታ ነጥሎ ኖሩዋል።
ተሾመ ግን በዚያ መገፋት ተስፋ ሳይቆርጥ የባህል ሚኒሰቴርን እና ቴአትር ቤቶችን በር ደጋግሞ አንኩዋኩዋ። የእነዚህ ተቁዋማት በሮች በዋናነት ለዓይናማዎቹ ብቻ የተከፈቱ ነበሩና ማንኩዋኩዋቱ ተሰምቶ በሮቹ አልተክፈቱለትም። ተሾመ ግን “አንኩዋኩቻለሁ፤ በሮቹ ግን አለትከፈቱም” ብሎ መቆዘምን፣ ቀያጅ የሆነው የማህረሰቡ አስተሳሰብ የሚፅፍለትን ዕጣ መቀበልን ምርጫው አላደረገም። የማይከፈቱ በሮችን ከማነኩዋኩዋት ይልቅ ሌሎች በሮችን ወደ መሰራት ሄደ። በተለያዩ ባንዶች ውስጥ ማገልገሉን፣ ከእውቅ ሙዚቀኞች ጋር ተባብሮ መስራቱን ቀጠለ። በሁዋላም ጎረቤት ሃገር ጅቡቲን መኖሪያው አደረገ። ለነገሩ ወደዚያም ሄዶ መስራት ዋዛ አልነበረም። ከሃገር እንዳይወጣ በሮችን ሊቆልፉበት የታገሉም ነበሩ። ማመልከቻው በአንድ ባለስልጣን ጠረጴዛ ላይ ልታርፍ በመቻሉዋ ነበር የጅቡቲ ጉዞውም በመጨረሻ የተሳካው።
በጅቡቲ የአምስት ዓመት ቆይታው “የኩባያ ወተት” የተሰኘ ስራው ገንኖ ቢወጣም ተሾመ የተለያየ ሃገር ዜጎችን ለማዝናናት በተለያዩ ቁዋንቁዋዎች ያዜም ነበር። እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ አፋርኛ፣ ሶማልኛ እና ሌሎችም።ተሾመ በሙዚቃ ቅንብር በኩል ከኦርኬስትራ ኢትዮጵያ ጋር ስራዎችን አበርክቱዋል። ከነዚህም ውስጥ ለጥላሁን ገሰሰ ያቀናበራቸው “አልማዝን አይቼ”፣ “ያለቀሰ ሲስቅ” እና “ውቢት ህይወቴ ነሽ” የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው። በተጨማሪም በኦርኬስትራ ኢትዮጵያ ቆይታው የፀሐይ እንዳለን ዜማም አቀናብሩዋል። ይህም ሆኖ ግን ተሾመ ቅንብርን በሙሉ መንፈስ ስራዬ ብሎ የያዘው በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ የራሱን የድምፅ አሻራ ካተመው ከኢትዮ ስታር ባንድ ጋር ሲሰራ እንድሆነ ይናገራል።
ተወዳጁ አርቲስት ቴዎድሮስ ታደሰ ከህዝብ ጋር በሰፊው ያስተዋወቀው ስራው የሉባንጃዬ ካሴቱ እንደሆነ ይታወቃል። ከዚያ ካሴት ውስጥ በዜማም ሆነ በግጥም እንዲሁም በቅንብር የሚገደፍ አንድም ስራ የለም ብንል ማጋነን አይሆንም። እንደ ሉባንጃዬ እና ቀን ሳይመሽ ሳይጨልም በጊዜን የመሳሰሉት ምርጥ ስራዎች የተካተቱበትን ይህንን ሙሉ ስራ ያቀናበረው ተሾመ አሰግድ ነው።በሁዋላም የሂሩት በቀለን ልጅ የመስፍን ኤልያስን እና ጥላሁንን ይተካል በሚል ማሞካሻ ይሞገስ የነበረውን ነገር ግን በልጅነቱ በሞት የተቀጨውን የደሳለኝ ቢሻውን ካሴቶችም አቀናብሩዋል። ኪቦርድ ወይም ሲንተሳይዘር የሚባለውን መሳሪያ በመጫወትም ድምፃውያንን አጅቡዋል።የሙዚቃ መሳሪያዎች ጨዋታ ከተነሳ የተሾመ ችሎታ ሊወሳ ግድ ነው። ተሾመ ክራር፣ መሰንቆ፣ ዋሽንት፣ አኮርዲዮን፣ ፒያኖ- ኪቦርድ የመሳሰሉትን መሳሪያዎች ይጫወታል።
አርቲስት ተሾመ አሰግድ በግልና በጋራ በአጠቃላይ ስድስት አልበሞችን ለህዝብ አበርክቱዋል።
1. “ትዝታ”፡ ከሬንቦው ባንድ ጋር በመሪ ድምፃዊነት ፊሊፕስ ባስቀረፀው ሸክላ 2. “በላሽው”፡ የካሴት ስራ ከሬንቦው ባንድ ጋር
3. “የኩባያ ወተት”፡ ከሮሃ ባንድ ጋር
4. “ደርባባዬ”፡ ከሮሃ ባንድ ጋር
5. በቡድን ከኬኔዴ መንገሻ እና ራሄል ዮሐንስ ጋር
6. በቡድን ከነበዛወርቅ አስፋው፣ ኤሊያስ ተባባልና ማርታ አሻጋሪ ጋር
ተሾመ በተናጥል ተወዳጅ ከሆኑለት እና ዛሬ ድረስ ወጣቶችን እያነቃቁ ከሚገኙት ዜማዎች መካከል “የኔ አካል የኔው ነሽ”፣ “አገሬ ነገር የዛው ሙዳይ”፣ “እንዲያው ዘራፌዋ”፣ “ያዘልቃል ያልሽው ፈጣን መኪና” እና ሌሎችም ተጠቃሾች ናቸው።
ተሾመ አሰግድ በግሪክ፣ ጣልያን፣ ጀርመን፣ ሆላንድ፣ ስዊድን፣ ጅቡቲ፣ ካናዳ እና እንግሊዝ ሃገራት የሚኖሩ አድናቂዎቹን በሙዚቃ ስራዎቹ የደረሰ ሲሆን፤ በሰሜን አሜሪካ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባቸው ከተሞች ሁሉ ማለት በሚባል ደረጃ ተፈጥሮ በለገሰችውና በዘመናት ልምድና ችሎታው ሲያገለግለን ኖሩዋል።

ŠHiwot mekonnen

ፎቶ © ከTedy Afro ገፅ

***** እሳቱ ተሰማ *****ከክብር ዘበኛ ሁለተኛ ኦርኬስትራ የመጀመሪያዎቹ ድምፃውያን አንዱ ነው። ለክብር ዘበኛ የሙዚቃ ክፍል ልዩ ፍቅርና አድናቆት የነበረው እሳቱ ጥላሁን ገሠሠን ወደ ክ...
01/12/2018

***** እሳቱ ተሰማ *****

ከክብር ዘበኛ ሁለተኛ ኦርኬስትራ የመጀመሪያዎቹ ድምፃውያን አንዱ ነው። ለክብር ዘበኛ የሙዚቃ ክፍል ልዩ ፍቅርና አድናቆት የነበረው እሳቱ ጥላሁን ገሠሠን ወደ ክብር ዘበኛ በማምጣት ታላቅ ሚና የተጫወተ ለየት ያለና ማራኪ ድምፅ የነበረው ከዘመኑ ምርጥ ድምፃውያን አንዱ ነበር።
ከተጫወታቸው በርካታ ዜማዎች በጥቂቱ...

* ችቦ አይሞላም ወገቧ
* አበባዬ ነሽ
* ትናንት ዛሬ አይደለም
* የልጅነት ፍቅር
* አይ ጠባይ
* አጋጠመኝ ዛሬ.....ጥቂቶቹ ናቸው።

ŠSamybaber Yosef

ከአልጋው ላይ ስንዝር የምታራርቀውእንደ ባህር አረም ቅስሟ የደመቀውእንደ ቀትር እባብ ሽንጧ የረቀቀውእንደ እየሩሳሌም አንጀቷ የራቀውስትተኛ ክናዳ ስንዝር የምትርቀውስታንተርስ ክንዷን የምታስጨ...
30/11/2018

ከአልጋው ላይ ስንዝር የምታራርቀው
እንደ ባህር አረም ቅስሟ የደመቀው
እንደ ቀትር እባብ ሽንጧ የረቀቀው
እንደ እየሩሳሌም አንጀቷ የራቀው
ስትተኛ ክናዳ ስንዝር የምትርቀው
ስታንተርስ ክንዷን የምታስጨንቀው
ስትስም ከመሬት የምትደባልቀው
ትንፋሿ እንዳ`ረቄ ሃሞት የሚከተው
ከንፈሯ እንዳ`ራስ ልጅ የሚርበተበተው
እጥር ምጥን ያለች የልጅ እመቤት
ስንቱ ገሠገሠ ሊወዳት ከቤት
አጥንቴ ረገፈ ስሠናበታት
አትለማም አትሠማም እኔ እዚ ስሞት
ኦሆ ነይ…ኦሆ ነይ…

ክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰአርቲስት ብዙነሽ በቀለአርቲስት ሻለቃ ጽጌ ፈለቀከግራ ወደ ቀኝ !
26/11/2018

ክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ
አርቲስት ብዙነሽ በቀለ
አርቲስት ሻለቃ ጽጌ ፈለቀ
ከግራ ወደ ቀኝ !

ስደት ና ኪነ ጥበብ_______________ከቀኝ ወደ  ግራ1_ሻበል በላይነህ2_ታማኝ በየነ3_ጌታቸው አብዲ4_ኤልያስ ተባባል5፣_አያሌው መስፍን6_አሊ  ታንኅ(የታንኅ ሙዚቃቤት ባለቤት)በጣም ...
26/11/2018

ስደት ና ኪነ ጥበብ
_______________

ከቀኝ ወደ ግራ

1_ሻበል በላይነህ
2_ታማኝ በየነ
3_ጌታቸው አብዲ
4_ኤልያስ ተባባል
5፣_አያሌው መስፍን
6_አሊ ታንኅ(የታንኅ ሙዚቃቤት ባለቤት)

በጣም የሚገርመው በዚህ ፎቶ ግራፍ ላይ የሚታዩት የኪነጥበብ ባለሞያዎች አሳታሚውን ጨምሮ ሁሉም ስደት ላይ ናቸው።

Š Teborne Beyene

ክራር አናጋሪው ካሳ ተሠማ©Mekonnen Sisay
26/11/2018

ክራር አናጋሪው ካሳ ተሠማ
ŠMekonnen Sisay

እዮብ መኮንን1፩፦የሙዚቃ አልበሙ (ዳሌሽ ባቴሽ የሌለበት)     2፪፦ህይወቱ»ቀኙ ሲሰጥ ግራው የማያይ  3፫፦ሞቱ»አለም አጭር መሆኗን ያሳየበት           ማን እንደ ቃል, ነቅቻለው,ነገ...
26/11/2018

እዮብ መኮንን

1፩፦የሙዚቃ አልበሙ (ዳሌሽ ባቴሽ የሌለበት)
2፪፦ህይወቱ»ቀኙ ሲሰጥ ግራው የማያይ
3፫፦ሞቱ»አለም አጭር መሆኗን ያሳየበት
ማን እንደ ቃል, ነቅቻለው,ነገን ላየው, የቋንቋ ፈላስፋ, ደብዝዘሽ.................
እዮባ ስራህ ለነብስ ጠበቃ ይሁንህ

© ዲጄ ሚኪ ጎጆ

Address

Addis Ababa
2906

Telephone

+251 90 108 4444

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethos Entertainment and Events posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category