Neew Ict and Event Organizer/ ነው አይሲቲና ኢቨንት ኦርጋናይዘር

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Neew Ict and Event Organizer/ ነው አይሲቲና ኢቨንት ኦርጋናይዘር

Neew Ict and Event Organizer/ ነው አይሲቲና ኢቨንት ኦርጋናይዘር Specializing within the creation of outstanding events for personal and company, we design, arrange,

አስቸኳይ  ክፍት የስራ መደብ ማስታወቂያ!!መካኒሳ አካባቢ የሚገኘዉ ጋሹና ኮፊ ሾፕ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የስራ መደቦች ላይ ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ስለሚፈልግ አመልካቾች ከታች በተ...
02/05/2024

አስቸኳይ ክፍት የስራ መደብ ማስታወቂያ!!

መካኒሳ አካባቢ የሚገኘዉ ጋሹና ኮፊ ሾፕ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የስራ መደቦች ላይ ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ስለሚፈልግ አመልካቾች ከታች በተገለፀዉ መስፈርት መሰረት የምታሟሉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣ ጀምሮ በአምስት ቀናት ዉስጥ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች 0912802694፤ 0911685777 ወይም 0911678053 ላይ ከማለዳ 2፡00 ሰዓት እስከ ምሽት 12፡00 ሰዓት በመደወል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን የቅጥረ ቃለ መጠይቅ ቦታዉ ከካራ ኮተቤ ወደ የካ አባዶ በሚወስደዉ መንገድ ላይ ከኦዞን ትምህርት ቤት በሰተቀኝ በኩል በሚገኘዉ የጋሹና ቡና ማቀነባበሪያ እና ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፤
1. የስራ መደቡ መጠሪያ፡ የፈጣን ምግቦች አዘጋጅ (ሃላፊ)
የትምህርት ዝግጅት፤ በምግብ ዝግጅት ከአንድ አመት በላይ የሰለጠነ እና ሰርተፍኬት ያለዉ
የስራ ልምድ፤ ሶስት አመት እና በተመሳሳይ ሙያ የሰራ
ተፈላጊ ፆታ፤ ወንድ/ሴት
ብዛት፤ አንድ
የወር ደሞዝ፤ በስምምነት

2. የስራ መደቡ መጠሪያ፤ የምግብ ዝግጀት ባለሙያ
የትምህርት ዝግጅት፤ አንድ አመት በምግብ አዘገጃጀት ሙያ የሰለጠነ
የስራ ልምድ፤ ከአንድ አመት በላይ በታዋቂ ምግብ ቤቶች በሃገር ባህል እና በዉጭ ሃገር ፈጣን ምግብ አዘጋጅነት የሰራ/ች
ተፈላጊ ፆታ፤ ሴት/ወንድ
ብዛት፤ ሁለት
የወር ደሞዝ፤ በስምምነት
3. የስራ መደቡ መጠሪያ፡ የተለያዩ የፍራፍሬ ጭማቂ አዘጋጅ
የትምህርት ዝግጅት፡ በምግብ ዝግጅት ሙያ ከስድስት ወር በላይ የሰለጠነ ወይም በቀድሞዉ 12ኛ ወይም 10ኛ ክፍል ያጠናቀቀ
የስራ ልምድ፡ ከሁለት አመት በላይ በተመሳሳይ ሙያ የስራ ልምድ ያለዉ
ፆታ፡ ሴት/ወንድ
ብዛት፡ ሁለት
የወር ደሞዝ፡ በስምምነትየስራ

4. መደቡ መጠሪያ፡ ባሪስታ
የትምህርት ዝግጅት፡ በቀድሞዉ 12ኛ ወይም 10 ያጠናቀቀ
የስራ ልምድ፡ ልዩ ልዩ ትኩስ መጠጦች አዘገጃጀት ከሁለት አመት በላይ ልምድ ያለዉ
ተፈላጊ ፆታ፡ ወንድ/ሴት
ብዛት፡ ሁለት
የወር ደሞዝ፡ በስምምነት

5. የስራ መደቡ መጠሪያ፡ አስተናጋጅ (ለቤት ዉስጥ እና ለዉጭ አገልግሎት)
የትምህርት ዝግጅት፡ 10ኛ ክፈል ወይም 12ኛ ክፍል ትምህረት ያጠናቀቀ
የስራ ልምድ፤ አንድ አመት በመስተንግዶ ስራ ልምድ ያለዉ/ያላት
ፆታ፤ ሴት/ወንድ
ብዛት፤ ሶስት
የወር ደሞዝ፤ በስምምነት

6. የስራ መደቡ መጠሪያ፡ የዕለት ሸያጭ ገንዘብ ተቀባይ
የትምህርት ዝግጅት፤ 10ኛ ወይም 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ፤ መሰረታዊ ኮምፒዩተር እና የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን አጠቃቀም እዉቀት ያለዉ
የስራ ልምድ፤ ሁለት አመት እና ከዚያ በላይ በተመሳሳይ ስራ ዘርፍ የሰራ
ፆታ፤ ሴት/ወንድ
ብዛት፤ ሁለት
የወር ደሞዝ፤ በስምምነት

7. የስራ መደቡ መጠሪያ፡ የፅዳት ሰራተኛ
የትምህርት ዝግጅት፤ 8ኛ ክፍል እና ከዚያ በላይ
የስራ ልምድ፤ አንድ አመት
ፆታ፤ ሴት
ብዛት፤ ሁለት
የወር ደሞዝ፤ በስምምነት
8. የስራ መደቡ መጠሪያ፤ የባር እና ምግብ ዝግጅት ፅዳት
የትምህርት ዝግጅት፤ 8ኛ ክፍል እና ከዚያ በላይ
ልምድ፤ አንድ አመት
ፆታ፤ ወንደ/ሴት
ብዛት፤ ሁለት
የወር ደሞዝ፤ በስምምነት

አንድ ሰው - ለአንድ ወገን!!...እባክዎ!..አንድ የጎዳና ሰው የበዓል ምሳውን ይሸፍኑልን?እኛ ስማችን ከዚህ በታች የተጠቀሰ ጋዜጠኞችና በጎ አድራጊዎች  ሶሻል ሚድያን በመጠቀም ለመጪው የፋ...
23/04/2024

አንድ ሰው - ለአንድ ወገን!!...

እባክዎ!..አንድ የጎዳና ሰው የበዓል ምሳውን ይሸፍኑልን?

እኛ ስማችን ከዚህ በታች የተጠቀሰ ጋዜጠኞችና በጎ አድራጊዎች ሶሻል ሚድያን በመጠቀም ለመጪው የፋሲካ በዓል አስታዋሽ የለሾቹን የጎዳና ተዳዳሪ ወገኖች ምሳ በማብላት በዓሉን አብረን ለማሳለፍ አቅደናል። እርስዎም ከጎናችን ይሁኑ!..ከቻሉ አብረውን ያሳልፉ?..ቢያንስ የአንድ ሰው የምሳ ወጪ በመሸፈን አጋርነትዎን ይግለፁልን?!

መርሐግብሩን ለማዘጋጀት ያቀድነው በተለያዩ ምክንያቶች ጎዳና ለወጡ ወገኖች ቢያንስ አለኝታነታችንን ለመግለፅ እና በዓሉን ደስ ብሏቸው እንዲያሳልፉ በማሰብ ነው።

ከእርስዎ የምንፈልገው እገዛ ቢያንስ አንድ ሰው በመመገብ ዓላማችንን ደግፈው ከጎናችን እንዲቆሙ ነው።

የአንድ ሰው ምገባ ወጪ ግምት 500 ብር ነው። አቅምዎ ከፈቀደ ሁለትም ሶስትም ...ወገኖችን በመመገብ ከበረከቱ መቋደስ ይችላሉ።

📌 የ 1 ሰው ምሳ ወጪ ለመሸፈን .................500 ብር

📌 የ 3 ሰዎችን...ለምትሸፍኑ...1500 ብር

📌 የ 6 ሰዎችን ...ለምትሸፍኑ.... 3000 ብር

📌 የ 10 ሰዎችን.... ለምትሸፍኑ......5000 ብር

📌 የ15 ሰዎችን ...ለመሸፈን...7500 ብር

📌 የ20 ሰዎችን ....ለመሸፈን...10000 ብር

***
✅ የምገባውን ዝርዝር መርሐግብር በቀጣይ የምናሳውቅ ይሆናል።

📌 አሁን መላክ ጀምሩ?!...

✅ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስላሴ ቅርንጫፍ
ሒሳብ ቁጥር

1000620235818...(ቴዎድሮስ፣ፍሬው እና አለምነሽ)

***ለተጨማሪ መረጃ አስተባባሪዎች

1.ቴዎድሮስ ካሳ(+251 98 900 0089)
2.ፍሬው አበበ (+251911617935)
3..አለምነሽ ኩምሳ (+25191 164 5458)
4.ቤቴልሄም ለገሰ (+251911335511)
5.ቆንጂት ሁሴን (+251911408541)

✅ ሲያስገቡ ደረሰኙን መላክ አይዘንጉ!!

💕 ማኀበራዊ ሚድያን ለበጎ ተግባር በመጠቀም ለውጥ እናመጣለን!!

እናመሰግንዎታለን!! 🙏

የኦቲዝም እውነታወች፡ • ሰማያዊ ቀለም ብዙውን ጊዜ የኦቲዝም ግንዛቤን ለማመልከት ያገለግላል።• ኦቲዝም ወንዶችም ሴቶችም  ላይ ሊከሰት ይችላል።• ታዋቂው ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን ኦት...
22/04/2024

የኦቲዝም እውነታወች፡
• ሰማያዊ ቀለም ብዙውን ጊዜ የኦቲዝም ግንዛቤን ለማመልከት ያገለግላል።
• ኦቲዝም ወንዶችም ሴቶችም ላይ ሊከሰት ይችላል።
• ታዋቂው ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን ኦትስቲክ እንደነበሩ ይታመናል።
• አብዛኞቹ ወላጆች በመጀመሪያ በልጆቻቸው ላይ የኦቲዝም ምልክቶች እንዳለ የሚያውቁት በ2 ዓመት እድሜ ላይ ነው።
• ኤፕሪል 2 የአለም የኦቲዝም ግንዛቤ ቀን ተብሎ ይከበራል።
• የንግግር ቴራፒ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የስራ ቴራፒ ኦቲዝም ያለባቸውን ግለሰቦች ለመርዳት በብዛት ጥቅም ላይ ይውላሉ።
• ኦቲዝም የአእምሮ ጤና መታወክ አይደለም።
• በአማካይ ከ54 ህጻናት 1 ህጻን በኦቲዝም የመያዝ እድል እንዳለው ይነገራል።
• ክትባት ኦቲዝምን አያመጣም።
• ኦቲዝም በሁሉም ዘር፣ ጎሣ እና ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ሁነት ውስጥ ያሉ ሰወችን ይነካል።
• ASD የሚለው ምህጻረ ቃል ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር ማለት ነው።

ስለኦቲዝም ያለንን ግንዛቤ አስፍተን ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት የየበኩላችንን ጥረት እናድርግ። እሩቅ ሳንሄድ በአካባቢያችን ላሉ ድጋፋችንን፣ እገዛችንን ከሚሹ ሰወች ጎን እንቁም።

መረዳዳት፣ መተሳሰባችንን እናጠነክር፣ በበጎነትና በርህራሄ የታጀበ፣ ለሁሉም የሚሰራ ጠንካራ ማህበረሰብን እንፈጥር ዘንድ እግዛብሄር ይርዳን።

ኩላሊትዎን ለማከም! 1. በቂ ውሃ ይጠጡኩላሊታችንን ጨምሮ ለአጠቃላይ ሰውነታችን ጤንነት አስፋለጊ የሆነውን በቀን ስምንት ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ።2. አልኮል እና ሲጋራ ማቆምአልኮል እና ሲጋራ ከ...
30/03/2024

ኩላሊትዎን ለማከም!


1. በቂ ውሃ ይጠጡ
ኩላሊታችንን ጨምሮ ለአጠቃላይ ሰውነታችን ጤንነት አስፋለጊ የሆነውን በቀን ስምንት ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ።

2. አልኮል እና ሲጋራ ማቆም
አልኮል እና ሲጋራ ከኩላሊት ጋር ዐይና እና ናጫ ናቸው። በመሆኑም ሁለቱን መለያየት አስፈላጊ ነው። የሚወስዱትን አልኮል መጠን ይቀንሱ፤ ሲጋራ ማጤስም ያቁሙ።

3. ከእጸዋት ከተቀመሙ ነገሮች ይጠንቀቁ
ለጤና እና ለሌሎች የተለያዩ ነገሮች በቅርብ ሰዎች ወይም ባለሙያ ነን በሚሉ ሰዎች ምክር ከተለያዩ ነገሮች የተቀመሙ ነገሮችን ከመጠጣታችን በፊት ቆም ብለን ማሰብ ይኖርብናል።
በተለይም ክብደት ለመቀነስ እና ለተመሳሳይ ጠቀሜታ በቤት ውስጥ እና በሌላም ቦታ የሚዘጋጁ መጠናቸው እና ይዘታቸው የማይታወቁ የእጸዋት ውጤቶችን መውሰድ ችግር ሊያስከትል ይችላል።

4. መድኃኒቶችን ያለአግባብ አይውሰዱ
ከሐኪም ካልታዘዘ በስተቀር መፍትሔ ነው ስለተባለ ወይም ሌሎችን ስላሻለ የትኛውንም ዓይነት መድኃኒት መውሰድ አይገባም።
በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ህመሞችን ለማስታገስ አዘውትረን የምንወስዳቸው መድኃኒቶች እፎይታን የሰጡን በሚመስለንም ለጉዳት ሊዳርጉን ይችላሉ።

5. ምርመራ ያድርጉ
በተቻለ አቅም ከስንት ጊዜ አንድ ጊዜ ኩላሊትን ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም የአካል ክፍሎቻችንን ጤንነት በምርመራ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
በዚህ ጊዜ በተለያዩ ምክንያቶች እያቆጠቆጡ ያሉ ከባድ የጤና ችግሮችን ሥር ሳይሰዱ ለማቅ ስለሚቻል በጊዜ በመታከም ለመዳን ዕድል ይፈጠራል።

6. የደም ግፊትዎን ይቆጣጠሩ
በአሁኑ ወቅት በዓለማችን እየተስፋፉ ካሉት ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች መካከል አንዱ የሆነው ከፍተኛ የደም ግፊት አንዱ ነው።
የደም ግፊት አንዱ የጤና እክል ሆኖ ሳለ መቆጣጠር ካልቻልን ሌሎች የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል።
ስለዚህም ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች የደም ግፊታቸው የጨመረ መሆኑን በሚረዱበት ጊዜ፣ ችላ ሳይሉ በቁም ነገር ሊከታተሉት ይገባል።
ከፍተኛ የደም ግፊት የምልክት አልባ የኩላሊት ችግር የመጀመሪያ ምልክት እንደሆነ ባለሙያዎች ስለሚገልጹ፣ የደም ግፊትን በመቆጣጠር የኩላሊትን ጤና መጠበቅ ይቻላል።
BBC

የዘንድሮ የፋሲካው የኤግዚብሽን ፕሮግራም ቅናሽ እንደሆነ ተገለፀ"ሠላም" የፋሲካ የንግድ ትርዒት ባዛርና ፌስቲቫል ከሚያዝያ 5 እስከ 26 በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እነደሚከናወን ተጠቆ...
30/03/2024

የዘንድሮ የፋሲካው የኤግዚብሽን ፕሮግራም ቅናሽ እንደሆነ ተገለፀ

"ሠላም" የፋሲካ የንግድ ትርዒት ባዛርና ፌስቲቫል ከሚያዝያ 5 እስከ 26 በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እነደሚከናወን ተጠቆመ ።

በአንጋፋው ሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ አማካኝነት በሚከናውነው "ሠላም" የፋሲካ ንግድ ትርዒት ፣ ባዛርና ፌስቲቫል ላይ በየቀኑ በአማካይ 15 ሺ የሚደርሱ ጎብኚዎች ይኖራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅና ከ500-600 የሚደርሱ አምራች ፣ አከፋፋዮችና ነጋዴዎች እንደሚሳተፉ የሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘውገ ጀማነህ ገልጸዋል።

ለ33ኛ ጊዜ በሚዘጋጀው የፋሲካ ንግድ ትርዒት ፣ ባዛርና ፌስቲቫል አዲስ የስራ ፈጣሪዎች እና አቅማቸው አነስተኛ ለሆኑ የንግድ እና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ልዩ ድጋፍ በማድረግ ለማሳተፍ መታቀዱን አቶ ዘውገ ተናግረዋል ።

በኤክስፖው ላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ምርት እና አገልግሎቶች፣ የባንከ እና የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች፣ የሪል እስቴት አልሚዎችና የኢንሹራንስ ሽያጭ አከናዋኞች፣ የምግብና መጠጥ አገልግሎት አቅራቢዎች: የቤትና የቢሮ እቃዎች እና የፈርኒቸር አምራችና አስመጪዎች እንዲሁም ሌሎች ድርጅቶች እንደሚሳተፉ የተገለፀ ሲሆን ፣ ይህን ምርታቸውን ለማስተዋወቅ ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች በአቅማቸው ድንኳን ፣ ቡዝ ተከላና ሌሎች አገልግሎቶችን አጠቃልሎ በብር 50 ሺ ብር በአነስተኛ ዋጋ ተከራይተው ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ማስተዋወቅና መሸጥ እንዲችሉ እድል መፍጠሩን ተጠቁሟል ።

በተጨማሪም ዝግጅቱ የሀገራችንን ብሎም የአዲስ አበባ ከተማን አለም አቀፋዊ ገፅታ በተለይም የአፍሪካ መዲናነት ደረጃን ታሣቢ በማድረግ በጥንቃቄ የታቀደ እና የሚተገበር ትርዒት ነው ተብሏል፡፡

ሴንቸሪ ፕሮሞሽንና ኤቨንትስ ባለፉት 25 ዓመታት ከመንግስት ፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ፣ ከንግድ ም/ቤቶች ፣ ከማህበራት ፣ ዩኒየኖች እንዲሁም የግል ድርጅቶች ጋር በአጠቃላይ ከ 75 የሚበልጡ ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ዝግጅቶችን ለማዘጋጀት መቻሉን አቶ ዘውገ ተናግረዋል ።

ከፍተኛ ሙቀት ፅንስን የማጨናገፍ እድሉ እየጨመረ ነው ተባለ___________________ከፍተኛ ሙቀት  የነፍሰጡሮች በሆዳቸው ያለን ጽንስ ለሞት የመዳረጉ ወይም የመጨናገፍ ዕድሉ በሁለት እጥ...
22/03/2024

ከፍተኛ ሙቀት ፅንስን የማጨናገፍ እድሉ እየጨመረ ነው ተባለ
___________________
ከፍተኛ ሙቀት የነፍሰጡሮች በሆዳቸው ያለን ጽንስ ለሞት የመዳረጉ ወይም የመጨናገፍ ዕድሉ በሁለት እጥፍ እንደሚጨምር በህንድ የተደረገ ጥናት አመላከተ።

ጥናቱ ከፍተኛ ሙቀት እናቶች ላይ የሚያመጣው ተጽዕኖ ከዚህ ቀደም ከታሰበው እጅግ ከፍ ያለ እንደሆነ አሳይቷል።

አጥኚዎቹ ከፍተኛ ሙቀት የሚመዘገብበት የበጋ ወቅትም ሴቶች ላይ ተጽዕኖ እንዳለው ይገልጻሉ።
በጥናታቸውም ነፍሰጡር እናቶች ላይ ብቻ የሚያተኩር አማካሪ እንዲቋቋምም ምክረ ሀሳበ አቅርበዋል።
በህንድ በሚገኘው ራማቻንድራ የከፍተኛ ትምህርት እና ምርምር ተቋም አማካኝነት የተሰራው ጥናት ከአውሮፓውያኑ 2017 ጀምሮ 800 ሴቶችን አሳታፊ አድርጓል።
ከተሳታፊዎች ግማሽ የሚሆኑት ለከፍተኛ ሙቀት ተጋልጠው እንደ ግብርና፣ ጡብ ምርት እና የጨው ማውጣት ስራ ላይ የተሰማሩ ናቸው።

19/03/2024

አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ከክፍል እንዳይወጡ እያደረጉ ነው
____________________

ሰሞኑን የተሰራጨውን የፅሀይ ጨረር መረጃን ተከትሎ አንዴንድ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ከክፍል እንዳይወጡ እያደረጉ መሆኑን ሰበር ዜና ያገኘችው መረጃ አመላክቷለ ።

ሰሞኑን በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች እየተስተዋለ ያለው የፅሀይ ግለት ብዙዎችን እያነጋገረ ያለ ሲሆን ፣ አንዳንድ ትምህርት ቤቶችም ተማሪዎቹ በፅሀይ ግለቱ እንዳይጎዱ በማሰብ ከክፍል መውጣትን ከልክለዋል።

የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲና የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነና ጨረርም ከፀሀይ ሙቀት ጋር ግንኙነት እንደሌለው አስታውቀዋል ።

በረመዳን ፆም በስሁር ጊዜ ላይ የማይመከሩ ምግቦች____________________የስብ መጠናቸው ከፍ ያለ ምግቦችና የውሃ ጥም የሚያስከትሉ ትኩስ መጠጦችን ከመውሰድ መቆጠብ ጾሙን በብርታት ለ...
15/03/2024

በረመዳን ፆም በስሁር ጊዜ ላይ የማይመከሩ ምግቦች
____________________

የስብ መጠናቸው ከፍ ያለ ምግቦችና የውሃ ጥም የሚያስከትሉ ትኩስ መጠጦችን ከመውሰድ መቆጠብ ጾሙን በብርታት ለመጨረስ ያግዛል ተብሏል።

ጾም ለሰው ልጆች ያለው መንፈሳዊ ብሎም አለማዊ በረከት በተደጋጋሚ ተጠቅሷል።

የተለያዩ ጥናቶች ጾም ሰውነታችን መርዛማ የሆኑ ነገሮችን በተፈጥሯዊ መንገድ እንዲያስወግድ
እንደሚረዳ አመላክተዋል።

እናም በረመዳን ወር በስሁር ወቅት የምግብ ጠረጼዛችን ላይ የሚቀርቡ ምግቦችና መጠጦች ጥንቃቄ ሊደረግባቸው እንደሚገባ ነው ባለሙያዎች የሚመክሩት።

በረመዳን የጾም ወቅት በስሁር (ቁርስ) ከተመገብናቸው ሰውነታችን ይጎዳሉ የተባሉ የምግብ አይነቶች ቀጥለው ቀርበዋል፦

1. የተጠበሱና ቅባታማ ምግቦች

አይብ፣ ቅቤ፣ የተጠባበሱ እና ቅባታማ ምግቦች በስሁር ወቅት አይመከሩም፤ ምንም እንኳን ጣፋጭ ቢሆኑም የምግብ መፈጨት ሂደት በማስተጓጎል ሰውነትን ያደክማሉ። ስብ ለሰውነታችን ወሳኝ ቢሆንም የምንጠቀመው መጠን መብዛትና የስብ አይነቱም ጤናማ አለመሆን በረመዳን ጾም ክብደት ለመጨመር ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ። የልብ ቃር እና ሌሎች እክሎችም በእነዚህ ምግቦች ምክንያት ተከስቶ ጾሙን ሊያውክ ይችላል ነው የሚሉት የህክምና ባለሙያዎች።

2. ስኳር የበዛባቸው ጣፋጭ ምግቦች

ኬክ፣ ፓስቲ፣ ስኳር የበዛባቸው የተጠባበሱ ምግቦች ወዲያውኑ የመጥገብ ስሜት እንዲሰማን ቢያደርጉም የካርቦሃይድሬት መጠናቸው አነስተኛ በመሆኑ ለረጅም ስአት ያለድካም ለመቆየት አያስችሉም።

3. ጨዋማ ምግቦች

በሰውነታችን ውስጥ ያለ የሶዲየም መጠን አለመመጣጠን የውሃ ጥምን ያስከትላል። በመሆኑም በስሁር ወቅት ጨው የበዛባቸውንና የውሃ ጥም የሚያስከትሉ ምግቦችን አለመውሰድ ተገቢ ነው።

4. የካፌይን ይዘት ያላቸው መጠጦች

ቡና፣ አረንጓዴ ሻይ እና ሌሎች ከፍተኛ የካፌይን ይዘት ያላቸውን ትኩስ መጠጦች በስሁር ወቅት መጠጣት የውሃ ጥም ከማስከተሉ ባሻገር እንቅልፍ ማጣትንም ያመጣል። በመሆኑም የካፌይን ይዘታቸው ከፍ ያሉ ትኩስ መጠጦችን በስሁር ወቅት መጠጣት አይመከረም ተብሏል።

* * *
ምንጭ :- አል አይን

14/03/2024
አዲሱ ጫት!____________________-  ተማሪዎች በትራማዶል ሱስ ተለክፈዋል! -  “ከድንገተኛ ሞት እስከ ቀጣይነት ያላቸው የጤና እክሎች ያስከትላል“     (ዶ/ር መስፍን በኃይሉ) ...
14/03/2024

አዲሱ ጫት!
____________________

- ተማሪዎች በትራማዶል ሱስ ተለክፈዋል!

- “ከድንገተኛ ሞት እስከ ቀጣይነት ያላቸው የጤና እክሎች ያስከትላል“

(ዶ/ር መስፍን በኃይሉ)
____________________

ትራማዶል የሚባለው የህመም ማጥፊያ መድሐኒት ያለ አግባብ በወጣቶች ኪስ ተዘውትሯል። ከስምንተኛ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በዚህ መድሐኒት ሱስ ተለክፈዋል። መድሐኒቱ ያለ በቂ ምክንያትና ተዘውትሮ ሲወሰድ ወደ ሱስነት ይሸጋገራል።

አንድ የገጠመኝ ተማሪ በቀን 26 ትራማዶል ክኒን መውሰድ ደረጃ የደረሰ ነበር። በቀን 26 ማለት ለመውሰድ ቀርቶ ለመቁጠር የሚታክት ነው። ሱስ የማያደርገው የለምና እያደረገ ቆይቷል። ከዚህ ደረጃ የደረሰው በአንድ ቀን አልነበረም። በቀን አንድ ተጀምሮ ቀስ በቀስ መላመድ ስላለው የሚፈለገውን የሱስ ቃና ስለማያስገኝ መጠኑን እንዲጨምር በሱስ ትዕዛዝ ሁለት፣ አራት፣ ስድስት፣.....እያለ ሀያ ስድስት ክኒን ላይ ደርሷል።

የትራማዶል ሱስ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ የሚገኝ አደገኛ የስነ አእምሮ ችግር ነው። ከመድሐኒት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የስነ አእምሮ ችግር የማይነካው ማዕዘን የለም። የግለሰብ፣ የቤተሰብና የማህበረሰብ ጤና፤ ኢኮኖሚና ማህበራዊ መስተጋብሮችን አደጋ ላይ ይጥላል።

ሳይንቲስቶች የደቀ ቁ ፕላስቲኮች በደም ማስተላለፊያ ቱቦ ውስጥ ማግኘታቸው ግርምትን እየፈጠረባቸው ይገኛልይህም የሆነው ሰዎች በየቀኑ የሚጥሏቸው ፕላስቲኮች አካባቢያችን ላይ ተፅእኖ እያመጡ በ...
07/03/2024

ሳይንቲስቶች የደቀ ቁ ፕላስቲኮች በደም ማስተላለፊያ ቱቦ ውስጥ ማግኘታቸው ግርምትን እየፈጠረባቸው ይገኛል

ይህም የሆነው ሰዎች በየቀኑ የሚጥሏቸው ፕላስቲኮች አካባቢያችን ላይ ተፅእኖ እያመጡ በመሆኑ ነው።

በካምፓኒያ ሊዩጂ ቫንቪቴሊ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ራፋኤል ማርፌላ ጥናታቸውን ተከትሎ እንደተናገሩት ከሆነ ይህ ከ5 ሚሊሜትር በታች ደቆ የሚታየው ፕላስቲክ ምናልባትም ለ ልብ ችግር ሁነኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል ነው ያሉት።

እነዚህ ጥቃቅን ፕላስቲኮች በትንፋሽ፣ በቆዳ በኩል አልያም ከምግብ ጋር ሊገባ ይችላል ሲሉ መላ ምታቸውን አስቀምጠዋል ሲል ኤን ቢሲ ዘግቧል።

ዱባይ ተራ ህንፃ ስር ተደበቀው የከረሙ መዳህኒቶች ተያዙ____________________የ20ሚሊዮን ብር የዋጋ ግምት ያለው በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ የተለያዩ መዳህኒቶች በቁጥ...
07/03/2024

ዱባይ ተራ ህንፃ ስር ተደበቀው የከረሙ መዳህኒቶች ተያዙ
____________________

የ20ሚሊዮን ብር የዋጋ ግምት ያለው በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ የተለያዩ መዳህኒቶች በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ፖሊስ መዳህኒት የማከፋፈል ሆነ የመሸጥ ፍቃድ የለውም ያለው ተጠርጣሪ የህገ - ወጥ መዳህኒቶቹን አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ዱባይ ተራ ህንፃ የታችኛው ክፍል ደብቆት ከርሟል ብሏል።

ግለሰቡ፥ የካቲት 10 ቀን 2016 ዓ/ም መዳህኒቶቹን ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀርባ ወዳለው የግል መኖሪያ ቤት በመውሰድ በዚያ አከማችቶ መያዙ ተነግሯል ።

ትራማዶል የተሰኘው ኪኒን ለድንገተኛ ሞት ይዳርጋል ተባለ____________________በወጣቶች ዘንድ ሱስ ወደመሆን ደረጃ ደርሷል____________________ ትራማዶልን ከሐኪም ፈቃድ ው...
05/03/2024

ትራማዶል የተሰኘው ኪኒን ለድንገተኛ ሞት ይዳርጋል ተባለ
____________________

በወጣቶች ዘንድ ሱስ ወደመሆን ደረጃ ደርሷል
____________________

ትራማዶልን ከሐኪም ፈቃድ ውጪ በአንድ ጊዜ አብዝቶ መውሰድ ከድንገተኛ ሞት እስከ ቀጣይነት ያላቸው የጤና ዕክሎች እንደሚያጋልጥ ተጠቆመ፡፡

ትራማዶል የተሰኘው ጊዜያዊ የህመም ማስታገሻ ተገቢ ባልሆነ መንገድ እየተዘወተረና ሱስ እየሆነ የወጣቶችን ጤና እያመሳቀለ መሆኑን በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር መስፍን በኃይሉ ገልጸዋል፡፡

በአብዛኛው ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በትራማዶል ሱስ እንደሚጠመዱ ጠቅሰው ፣ ያለ በቂ ምክንያት ተዘውትሮ ሲወሰድ ወደ ሱስነት እንደሚሸጋገር አስረድተዋል፡፡

" የትራማዶል ሱስ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ ያለ አደገኛ የሥነ-አዕምሮ ችግር ነው "ያሉት ባለሙያው ፣ " ከድንገተኛ ሞት እስከ ቀጣይነት ያላቸው የጤና እክሎች ያስከትላል " ብለዋል ።

በአንድ ጊዜ በብዛት ከተወሰደም ለሞት ይዳርጋል ማለታቸውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ መረጃ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም መዳህኒቱ ለአንጎል ንዝረት፣ ለኩላሊት መድከም (መባባስ)፣ ለጡንቻ መቅለጥ እና ለከፋ የሥነ-ልቦና ችግር ይዳርጋል ብለዋል ።

አንዳንድ ወጣቶች ኪኒኑን በመውሰድ ሱሳቸውን ማብረድ ሲሳናቸው በመርፌ መውሰድ እንደሚጀምሩና ይህ ሁኔታም ለስትሮክ እንደሚያጋልጥ ጠቁመዋል፡፡

* * *
ምንጭ:- አአዮ የጤና ሳይንሰ ኮሌጅ

03/03/2024

ሐኪሞች ዶክተር መባል የለባቸውም! በዚህ የሚስማማ አለ?
___________________

የህክምና ባለሙያዎች ዶክተር መባል የለባቸውም።

ምክንያቱም ዶክተር የሚባለው በየትኛውም የትምህርት ዘርፍ ሶስተኛ ዲግሪ ለያዙ የሚሰጥ ማዕረግ ነው። PHD የሚባለው ማለት ነው።

ስለዚህ ሀኪሞች ፊዚሻን(Physicians)፣ ሰርጂን(surgeon)፣ የጥርስ ሀኪም(dentist)፣ የአይን ሐኪም(Optometreists)፣ የማህፀንና ጽንስ ስፔሻሊስት(Gynecologyists)፣ የካንሰር ስፔሻሊስት(Oncologist)...ወዘተ ነው መባል ያለባቸው እንጂ ዶክተር መባል የለባቸውም የብለው የሚከራከሩ ብዙ ናቸው። እርስዎስ ምን ይላሉ? ሀኪሞች አስተያየት ቢሰጡበት ደስ ይለኛል ።

* * * *
ጥላሁን አክሊሉ

ብዙ ያልተነገረለት ቀይ ስር____________________በኢትዮጵያ የደም ግፊት ያላባቸው ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። ይህ ተላላፊ ያልሆነው የጤና ችግር ከወጣት አስከ አ...
29/02/2024

ብዙ ያልተነገረለት ቀይ ስር
____________________

በኢትዮጵያ የደም ግፊት ያላባቸው ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። ይህ ተላላፊ ያልሆነው የጤና ችግር ከወጣት አስከ አዋቂዎች ላይ እየተከሰተ ሲሆን፣ ኣሳሳቢነቱ ከፍተኛ ሆኗል።

የአኗኗር ዘይቤ፣ አመጋገብ፣ እንቅስቃሴ አለማድረግ እና ሌሎችም ለደም ግፊት ምክንያት ከሚባሉት ዋነኞቹ ሲሆኑ፣ ጤናማ አኗኗር በመከተል እራስን ከደም ግፊት ለመጠበቅ እና መቆጣጠር እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ከእነዚህም መካከል የአመጋገብ ሥርዓትን በማስተካከል እና ጤናማ በማድረግ ደግም ግፊትን በሚፈለገው መጠን ውስጥ ማድረግ ይቻላል። ለዚህም ከሚመከሩት የምግብ አይነቶች መካከል አንዱ ቀይ ሥር ነው።

አንዳንዶች ቀይ ሥር እንዲሁ ለቀለሙ እንጂ የሚሰጠው የምግብነት ጠቀሜታ ይህን ያህል ነው ሲሉ ቆይተዋል። ባለሙያዎች ግን ቀይ ሥር ለሰውነት ከሚሰጠው ብርታት እና ጥንካሬ ባሻገር የደም ግፊትን በመቀነስ በኩልም ጠሜታ አለው ይላሉ።

ቀይ ሥር የደም ግፊትን ዝቅ ከማድረግ እና እድሜ እየገፋ ሲሄድ የእእምሮ ጤናን ከመጠበቅ በተጨማሪ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች አሉት።

የዚህን አትክልት ለየት ያለ ጠቀሜታን በተመለከተ የሥነ ምግብ እና የጤና ባለሙያዎች መረጃዎችን እያጋሩ ሲሆን፣ በዕለት ከዕለት ምግባችን ውስጥም ቀይ ሥርን እንድናካትት እየመከሩ ነው።

27/02/2024

በግል የህክምና ተቋማት ብልሹ አሰራርና የገንዘብ ብዝበዛ ላይ ክትትል አድርጎ የሚያጋልጥ የጋዜጠኞች ቡድን እየተዋቀረ ነው።

የአፍሪካዊያን የሙዚቃ እና ምግብ ፌስቲቫል በድምቀት ተካሄደAfro food and music fest ትናንት ምሽት የካቲት 16/2016 ዓም በአዲስ አበባ ቫይብስ ሆቴል እና ስፓ ተካሄደ።በዝግጅ...
26/02/2024

የአፍሪካዊያን የሙዚቃ እና ምግብ ፌስቲቫል በድምቀት ተካሄደ

Afro food and music fest ትናንት ምሽት የካቲት 16/2016 ዓም በአዲስ አበባ ቫይብስ ሆቴል እና ስፓ ተካሄደ።

በዝግጅቱ ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ እንግዶች የታደሙበት ሲሆን የምስራቅ አፍሪካ Nyama & Kuku Choma ምግቦች የምዕራብ አፍሪካ Salone Kitching (Acheke Potatoe & Cassava Leaves) Grill fish, peper soup, Nigeria-foo foo & Egusi South African Braai፣ የኢትዮጵያ ምግቦች ክትፎ፣ ጥብስ፣ ቁርጥ እና የሸክላ ጥብስ በፌስቲቫሉ ላይ ቀርበው እንግዶቹ አጣጥመውታል።

የአፍሪካ ሀገራት ሙዚቃ እና የባህል ፋሽን ሾው በፕሮግራሙ ላይ የቀረበ ሲሆን ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ታዳሚያን የባህል ልውውጥ አድርጓል።

ፕሮግራሙ የተከናወነበት ቫይብስ ሆቴል እና ስፓ በአዲስ አበባ መገናኛ አከባቢ ሲገኝ ምቹ እና ፅድት ያሉ የመኝታ ክፍሎች፣ የማሳጅ፣ ስፓ እንዲሁም የወንዶች እና ሴቶች የውበት ሳሎን አካቶ የያዘ ሆቴል እንደሆንም ተመልክተናል።

https://yt2fb.in/v/rtnXw_MUVSs
25/02/2024

https://yt2fb.in/v/rtnXw_MUVSs

ከሀምሳ ብር ተነስተው ባለ 4 ኮከብ ሆቴል የገነቡት ባለሀብት ታሪክ። በጋዜጠኛ ኤደን ገ/ህይወት!

የሐኪሞች ማህበር የግል የጤና ተቋማትን ወቀሳ____________________ታካሚዎች በግል የጤና ተቋማት ዋጋ መወደድ ላይ  ቅሬታ እያነሱ  መሆኑን የኢትዮጵያ  የሐኪሞች ማህበር አስታወቀ ።...
24/02/2024

የሐኪሞች ማህበር የግል የጤና ተቋማትን ወቀሳ
____________________

ታካሚዎች በግል የጤና ተቋማት ዋጋ መወደድ ላይ ቅሬታ እያነሱ መሆኑን የኢትዮጵያ የሐኪሞች ማህበር አስታወቀ ።

ማህበሩ በየጊዜው ከህብረተሰቡ በርካታ ቅሬታዎች የሚቀበል ሲሆን፣ ከቅሬታዎች ቀዳሚ የሆነው እና በርካታ ታካሚዎች እየተማረሩበት ያለው ጉዳይ የግል የህክምና ተቋማት የዋጋ መወደድ መሆኑን ገልጿል ።

የማህበሩ ፕሬዝዳን አቶ ተግባር ይግዛው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት እለት ከእለት በርካታ ቅሬታዎችን እንደሚያስተናግዱ ገልጸዋል ። ከእነዚህም መካከል የመድኃኒት ዋጋ መወደድ፣ የህክምና ተቋማት የገንዘብ ክፍያ ከአግባብ በላይ መሆን ፣ እንዲሁም ስነምግባር ጥሰት እንደሚገኙበትም ተጠቁሟል።

አክለውም ማህበሩ በቅርቡ በሚያካሄደዉ በ60ኛ ዓመታዊ ጉባኤው የመድኃኒት መወደድ ፣ የስነምግባር ጥሰት፣ እና ሌሎች የቀረቡ ቅሬታዎችን በተመለከተ ውይይት እንደሚደረግባቸው ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል፡፡

ታካሚዎች በተመጠጣኝ ዋጋ ህክምና ማግኘት የሚችሉበትን ፣ በስነምግባር እና አገልግሎት በተመለከተ መልካም አገልግሎት መሰጠት እንደሚኖርበት እና ሌሎች የተነሱ ቅሬታዎችን በተመለከ የመፍትሄ ውይይቶች እንደሚደረጉ ይጠበቃል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

****

ዳጉ_ጆርናል

19/02/2024

የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭትን ለመቆጣጠር አስገዳጅ መመሪያ በትምህርት ቤቶች ሊተገበር ነው
____________________

የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭትን ለመቆጣጠር አስገዳጅ መመሪያ በትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚደረግ በጤና ሚኒስቴር የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ጽህፈት ቤት መሪ ስራ አስፈጻሚ ፈቃዱ ያደታ አስታውቋል።

ኤችአይቪ/ኤድስ በሀገር አቀፍ ደረጃ የስርጭት መጠኑ ከ1 በመቶ በታች መሆኑን የጤና ሚኒስቴር የገለፀ ሲሆን በተለያዩ ክልሎች ያለው ስርጭት እንደሚለያይና በተለይም በጋምቤላ 4 ነጥብ 5፣ በአዲስ አበባ 3 ነጥብ 4፣ በሐረሪ እና በድሬዳዋ ደግሞ 3 በመቶ መሆኑን ተጠቁሟል።

እንደ ሀገር ስርጭቱ ዝቅ ያለ ቢሆንም በአንዳንድ አካባቢዎችና የህብረተሰብ ክፍሎች ስርጭቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑንና በተለይም በወጣት ሴቶች፣ ሴተኛ አዳሪዎች፣ የአደንዛዥ እጽ ተጠቃሚዎች፣ ረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች፣ የህግ ታራሚዎችና በጎዳና ላይ ንግድ የሚተዳደሩ ሴቶች በይበልጥ ለቫይረሱ ተጋላጭ እንደሆኑም ተመላክቷል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ አዲስ የመያዝ ምጣኔም ሆነ በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ቢሆንም በተለይ በወጣቶች ላይ የመያዝ ምጣኔው እንደታሰበው እየቀነሰ ባለመሆኑ ቫይረሱን ለመቆጣጠር በትምህርት ቤቶች ላይ በትኩረት ለመስራት አስገዳጅ መመሪያ ለመተግበር ጤና ሚኒስቴር ጥረት እያደረገ መሆኑን ተጠቁሟል።

ስለ መመሪያው ይዘት የሚኒስቴሩ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ጽህፈት ቤት መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ፈቃዱ ያደታ ዝርዝር ማብራሪያ #ያልሰጡ ሲሆን መመሪያው ስለኤችአይቪ ግንዛቤ ለመፍጠር እንዲሁም ሌሎች የመከላከል እና የመቆጣጠር ዘዴዎችን ትኩረት ሰጥቶ ለመተግበር ወሳኝ እንደሆነ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ጠቃሚ መረጃ
19/02/2024

ጠቃሚ መረጃ

11/02/2024

ተደጋጋሚ ሽንትን የመምጣት ችግርን ለመቀነስ የሚረዱ አንዳንድ የጤና ምክሮች:-
____________________

_ ከመተኛትዎ በፊት ፈሳሽ መውሰድን ይገድቡ፡- ከመተኛትዎ ከሁለት ሰአት በፊት ከፍተኛ መጠን ያለው ፈሳሽ ከመጠጣት ይቆጠቡ። ይህም በምሽት ጊዜ የመሽናት ፍላጎትን ለመቀነስ ይረዳል።

_የሚወስዱትን የካፌይን እና የአልኮል መጠንን ይቀንሱ፡- ካፌይንም ሆነ አልኮል እንደ ዳይሪቲክስ ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉ፤ ይህም የሽንት ምርትን ይጨምራል። እነዚህን ንጥረ ነገሮች መውሰድዎን መገደብ ሽንት በተደጋጋሚ መሽናትን ለመቀነስ ይረዳል።

_ የሽንት ፊኛን መቆጣትን መቆጣጠር፡- የተወሰኑ ምግቦች እና መጠጦች ማለትም እንደ:- ሲትረስ ፍሩት፣ ቅመም የበዛባቸው ምግቦች፣ ካርቦን ያላቸው መጠጦች እና ሰው ሰራሽ ማጣፈጫዎች ፊኛችን እንዲቆጣና እና የሽንት በተደጋጋሚ መምጣትን ሊያባብሱ ይችላሉ። እነዚህን ቀስቃሽ ነገሮች ለመለየት እና ለማስወገድ ይሞክሩ።

_ ጤናማ ክብደት ይኑርዎት፡- ከመጠን በላይ ክብደት በፊኛ ላይ ጫና ስለሚፈጥር ተደጋጋሚ የሽንት መምጣትን ያስከትላል። ክብደት መቀነስ ትንሽም ቢሆን የሽንት ፊኛ ቁጥጥርን ለማሻሻል ይረዳል።

_ የዳሌ ጡንቻዎችን ማጠንከር፡- የ ኪግል ስፓርት (Kegel Exercise) የሽንት ፊኛን እና የሽንት ቱቦን የሚደግፉ ጡንቻዎችን ለማጠናከር ይረዳል። ይህም የፊኛ ቁጥጥርን ያሻሽላል በተጨማሪም አዘውትሮ የሽንት መምጣትን ይቀንሳል።

_ ብዙ ውሃ መጠጣት፡- ተቃራኒ ቢመስልም ውሃን ማቆየት ወይም ውሃ መጠጣት ለፊኛ ጤንነት ጠቃሚ ነው። ብዙ ውሃ መጠጣት ሽንትን በማሟሟትና መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ለማስወገድ ይረዳል። ይህም ማቃጠልን እና ቶሎ ቶሎ የመሽናት ፍላጎትን ይቀንሳል። በቀን ስምንት ብርጭቆ ውሃ ለመጠጣት ያቅዱ።

_ ፋይበር የበዛበት አመጋገብ ይመገቡ:- ፋይበር የምግብ መፍጫ ስርዓታችን በተቃና ሁኔታ እንዲንቀሳቀስ ይረዳል፤ ይህም የሆድ ድርቀትን ይከላከላል። የሆድ ድርቀት ፊኛ ላይ ጫና ስለሚፈጥር ተደጋጋሚ የሽንት መሽናትን ሊያባብስ ይችላል።

_ ስኳር የበዛባቸው መጠጦችን አይውሰዱ፡- ስኳር የበዛባቸው መጠጦች ፊኛን ሊያስቆጡና የሽንት በተደጋጋሚ መምጣትን ሊያባብሱ ይችላሉ። በምትኩ ውሃ፣ ያልጣፈጠ ሻይ ወይም ጥቁር ቡና መውስድን ይምረጡ።

▪️ ፊኛዎን ሙሉ በሙሉ ባዶ ያድርጉት፡- በሚሸኑበት ጊዜ ፊኛዎን ሙሉ በሙሉ ባዶ ማድረግዎን ያረጋግጡ። ይህ ብዙም ሳይቆይ እንደገና ሽንት ለመሽናት የመሄድ ፍላጎትን ለመቀነስ ይረዳል።

▪️ ደርበው ፊኛዎን ባዶ ማድረግ፡- ሽንት ከሸኑ በኋላ ጥቂት ደቂቃዎችን ይጠብቁ ከዚያም እንደገና ለመሽናት ይሞክሩ። ይህ ፊኛዎን ሙሉ በሙሉ ባዶ ማድረግዎን ለማረጋገጥ ይረዳል።

▪️ የዳሌ አካላዊ ሕክምና፡- ሌሎች የአኗኗር ለውጦችን ከሞከሩ እና በተደጋጋሚ ሽንትዎ እየመጣ የሚያስቸግርዎ ከሆነ፤ የዳሌ አካላዊ ሕክምናን ስለማድረግ ማጤን ያስፈልጋል።

ፊዚካል ቴራፒስት ፊኛዎን እና የሽንት ቱቦዎን የሚደግፉ ጡንቻዎችን ለማጠናከር ልዩ የአካል ብቃት ልምዶችን ወይም እንቅስቃሴዎችን ሊያስተምርዎት ይችላል።

እንደ:- ሕመም፣ በሽንትህ ውስጥ ያለ ደም ወይም ትኩሳት የመሳሰሉ ሌሎች የሕመም ምልክቶች በተደጋጋሚ ሽንት ከመምጣት ጋር የሚያጋጥምዎት ከሆነ፤ ማንኛውንም መሰረታዊ የጤና እክሎች ለማስወገድ ዶክተር ማየት አስፈላጊ ነው።

09/02/2024

በአዲስ አበባ የደም ግፊት በሽታ ስርጭት 22 በመቶ ደረሰ
____________________

የደም ግፊት በሽታ በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ የደም ግፊት ስርጭት 16 በመቶ ሲሆን በአዲስ አበባ ደግሞ 22 በመቶ መሆኑን ቢሮዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡

በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የጤና ማጎልበት እና በሽታ መከላከል ዳይሬክተር አቶ ጌቱ ቢሳ በወንዶች 25 በመቶ በሴቶች ደግሞ 18.8 በመቶ ነ ዉ ብለዋል፡፡

ይህም የሚያሳየው ከ5 ሴቶች 1፤ ከ 4 ወንዶች ደግሞ 1 ሰው የደም ግፊት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
የተቀመጠው ቁጥርም ቀላል የሚባል አለመሆኑን አንስተዋል፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩትም እድሜቸው ከ30 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው ብለዋል፡፡

ለችግሩ መስፋፋት እንደመንስኤ ከሚነሱ ነገሮች ወስጥ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ፣ ከመጠን በላይ ጨው መጠቀም ፣በቂ ያልሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደሚገኙበት አቶ ጌቱ ተናግረዋል ፡፡

የአዲሰ አበባ ጤና ቢሮ በአጠቃላይ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ላይ ትኩረት በመስጠት ሰፊ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ እና ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎችም ተጠናክረው እንደቀጠሉ አስታውቀዋል።

Address

Bole Medehanialem, Oromia Tower
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Neew Ict and Event Organizer/ ነው አይሲቲና ኢቨንት ኦርጋናይዘር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category

Nearby event planning services