24/08/2023
ለክቡር ጠ/ር ዶ. ር አብይ አህመድ
ያስተዛዝበናል!!!
ኢትዮጵያ ብርክስ አባል ሃገራትን በመቀላቀሏ ደስ ብሎናል እንኩዋን ደስ አልዎት::
ነገር ግን በሰጡት እንኩዋን ደስ ያላችሁ መልዕክትዎ ላይ እና በተደጋጋሚ መልኩ በሚሰጡት መግለጫዎች ሁሉ ላይ ኢትዮጵያ ከፍተኛ እድገት ማሳየቱዋን ሲናገሩ ይስተዋላል ::
አዎ እድገት አሳይተናል ለዛዉም በዓለም ደረጃ ::ነገር ግን በፖለቲካ እንጂ በኢኮኖሚ ደረጃ አድጉዋል የተባለው ያስተዛዝበናል::በፖለትካዉም ቢሆን ብዙ አጠያያቂ ነገሮች እንደነበሩ ሆነው ማለት ነው ::
ታዲያ አድጉዋል የተባለው የሀገሩ ሰው ማደጉን ሳያምንበትና በቀን ሶስቴ ከሚበላበት አሁን ሁለቴ ለመብላት በሚቸገርበት, በ2000 ደሞዝ ስኩዋር በኪሎ 20ብር :ጤፍ በኪሎ 30ብር, በቆሎ በኪሎ 10ብር, ቡና በኪሎ 50ብር, ዳቦ በፍሬ 1ብር, ዘይት በሊትር 50ብር.....
ከነበረበት ስኩዋር በኪሎ 100ብር, ጤፍ በኪሎ 100ብር, በቆሎ በኪሎ 50ብር, ቡና በኪሎ 350ብር, ዳቦ በፍሬ 10ብር, ዘይት በሊትር 150ብር..... ያህል ጭማሪ እድገት አሳይቶ ደሞዙ ግን ያው 2000ብር ሆኖ ከመኖርና ካለመኖር ሕይዎት መካከል በጣር ላይ ያለው የመንግስት ሰራተኛውስ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ አድጋለች ሲሉ አያስተዛዝብም?
ኢትዮጵያ ማደጉዋን ኢትዮጵያውያን ካልመሰከሩ ዉቻውያን ብመሰክሩ..... ምን ነበር ሚባለው ተረቱ????
ያስተዛዝበናል!የፖለቲካውን አላልኩም ፖለቲካዉን ለፖለቲከኛው ::
በከተማ ልማት የሚሰሩት ሥራ ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ በኢኮኖምዉም በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ፊትዎን ብያዞሩ መልካም ነው
ያኔ የዓለም ሕዝብ ከምናገርልዎት ይልቅ የሚመሩት የሀገርዎ ሕዝብ ብናገርልዎትና ሥራዎ ቢናገር መልካም ነው የሚል ጥቂት ሃሳብ አለኝ ::
ከመንግስት ሰራተኛ አንዱ አንደበት