07/08/2024
👇🏾👇🏾👇🏾
https://yt.psee.ly/6ahfup
🔊🔊🔊+++በገና+++🔊🔊🔊
"በገና" የበገና ቀጥተኛ ትርጉሙ መዝሙር ሲሆን.
በገና፡- በገነ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን ማለትም ደረደረ መታ፡ነዘረ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም በገና ማለት ድርደራ፣ ምስጋና፣ መዝሙር... ማለት ነው።መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ መሠረት በማድረግ ይተረጎማል፡፡ ለምሳሌ፦
"አቤቱ አምላኬ በበገና አመሰግናለሁ" መዝ.42/43:4
"ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት" መዝ.48:5
"እግዚኣብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት አሥር አውታር ባለው በበገና ዘምሩለት" መዝ.32/33:2
በገነኛው ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ በገናን ሲተረጉም መዝሙር፣ምስጋና... በማለት ሲገልጽ እናገኘዋለንና።
በገና የሚያገለግለው ለመንፈሳዊ ትሩፋት ማለትም ለምስጋናና ለልመና ብቻ ነው፡፡በመሆኑም ተመርጦ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ይውላል።
ከዚህ በተጨማሪም እንደ አስፈላጊነቱ ለማኅበራዊ እሴት፣ ለሃገር ክብር፣ ለሉዓላዊነት...በገና ይደረደራል፡፡ ለዚህ ጥሩ ማስረጃችን በአፄቴዎድሮስ ጊዜ የተደረደረውና እስከ አሁን ድረስ የበገና መማርያ የሆነው የበገና አገልግሎት ነው።ከዚህ ውጭ በገና ለዓለማዊ ፍላጐት ማስፈጸሚያ ማለትም፡- ለዳንስና ለዳንኪራ ለዘፈንና ለጭፈራ ለዝናና ለጉራ ለቀልድና ለፉከራ... ወዘተ ፈጽሞ አገልግሎት አይሰጥም፡፡
የበገና ዜማ ልብን የሚነካ፤ ከፈጣሪ ጋር ለመገናኘት እራስንም ለማግኘት ጥቅም ላይ የሚዉል ምስጋና ማቅረብያ የዜማ መሳርያ ነዉ። የሰዉን ልጅ ስሜት የመግዛት ከፍተኛ ሃይል እንዳለዉ የሚነገርለት የበገና ድርድር በተለይ በጾም ወራት በብዛት
ይደመጣል።በብዛት ተባለ እንጂ ዓመት እስከ ዓመት የሚመሰገንበት ነው።
በገና በገዳማዉያንም ዘንድ የተወደደና የተከበረ ሲሆን። ግን ኋላ ኋላ የመጥፋት አዝማምያ ገጥሞት እንደነበርና አሁን ደግሞ ዳግም ለትንሳኤ በቅቶአል በገና። «በአገራችን አጼ ቴዎድሮስ በገና በመደርደራቸዉም ይታወቃሉ፤ዕቴጌ ጣይቱ እንዲሁ በገና ደርዳሪ ናቸው» በጾም ወቅትም ወደራስ የመመለሻም ግዜ ስለሆነ በገና በሰፊው ይደመጣል።
በበገና
እግዚአብሔር፦ ይመሰገንበታል፣ ይቀደስበታል፣ ይለመንበታል... "
ሕሙማን፦ ይፍወሱበታል፡፡
ሕዙናን፡- ይጽናኑበታል፡፡
አማኞች፡- ይመከሩበታል፡፡
የሀገር ክብር ይገለጽበታል።
የዚህ ታሪካዊና ጥንታዊ የዜማ መሣርያ ጣዕም ለሥርዓተ አምልኮ፣ ለልመናና ለምስጋና ተጠቅመን በሕይወታችን በንስሐ መርተን ፍጻሜአችን ያማረ የተስተካከለ እንዲሆንልን አምላከ ዳዊት እግዚአብሔር ይርዳን።