Silte-Reporter's

Silte-Reporter's ይህ ገፅ ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎችና ትምህርቶች የሚሰራጭበት ?
(1)

13/12/2023
29/11/2023

“የትምህርት ጥራትን በማምጣት ብቁ ዜጋን ለማፍራት በሚደረገው ጥረት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል”!

ክብርት ወይዘሮ መህዲያ ቡሴር
የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ ከተናገሩት የተወሰደ!

25/11/2023

ዜና ሹመት
_________________________________________
የምስረቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት አዲስ የአመራር መዋቅር የተቀላቀሉ አመራሮችን ጨምሮ በሽግሽግ በምክትልና በካቢኔ ማዕረግ አደራጅቷል።

⏩በዚህም መሰረት:- በካቢኔ ማዕረግ ሽግሽግ የተደረጉና አዲስ የተሾሙ

1. አቶ ከይሬ ሀቢብ የወረዳው ምክትል አስተዳደሪና ትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ
2. አቶ አንዋር ሙስጠፋ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ
3. አቶ በህረዲን ጀማል ደንና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ሀላፊ
4. ወ/ሮ ናጂያ ሹክራላ ፐብሊክ ሰርቪስ ና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ
5. ዶ/ር ሙዲን ሸረፋ ፕላን ፅ/ቤት ሀላፊ
6. አቶ ቢረዳ አማን የእንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ
7.አቶ አብዱረህማን ጁሃር ጤና ጽ/ቤት ሀላፊ
8.አቶ አሽረቅ መህሙድ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ሀላፊ
9. አቶ አባስ ሱልጣን ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ
10. አቶ ሳዲቅ ሹክሬ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ሀላፊ
11. ወ/ሪት ሰኪና መሀመድ ሴቶችና ህፃናት ፅ/ቤት ሀላፊ
12. አቶ አብድል ሽኩር አለማር በብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት እንስፔክሽን ዘርፍ ሀላፊ
13. አቶ ሙባሪክ አወል የአስተዳደር የካቢኔ ጉዳዮች አማካሪ
14. ወ/ሮ ሸጊቱ ሸሄቦ የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የሰው ሀብት

በምክትል ማዕረግ ሽግሽግ የተደረጉና አዲስ የተሾሙ

1.አቶ ሰማን ከድር የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ም/ሀላፊ
2. አቶ ሱልጣን አህመድ የትምህርት ፅ/ቤት ምክትል ሀላፊ
3. አቶ ሙሰፋ አልማ የወጣቶች ሊግ ሀላፊ
4. አቶ ኑባሳ ጨፋ የከተማ ልማት ምክትል ሀላፊና የህብረተ ሰብ ተሳትፎና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ በመሆን ተሹመዋል።

15/07/2023

የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል!

ሐምሌ 10/2015 በአረንጓዴ አሻራ በአንድ ጀንበር ከአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ አራት ሺ በላይ የጥላ ዛፍ፣ የፍራፍሬና የእንሰሳት መኖ ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ማጠናቀቁን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ አከባቢ ጥበቃና ደን ልማት ጽ/ቤት አስታውቋል።

የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ አከባቢ ጥበቃና ደን ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባስ ሱልጣን እንዳስታወቁት የፊታችን ሰኞ ሐምሌ10 በወረዳችን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን በአንድ ጀንበር ለመትከል ሙሉ ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

በዕለቱም ከ1 504 765 ሺ በላይ የሚሆኑ የጥላ ዛፍ፣ የፍራፍሬና የእንስሳት መኖ ችግኞች ለመትከል ዝግጅት የተደረገ መሆኑን የጠቆሙት አቶ አባስ በዝግጅቱ ላይ በርካታ አካላት ከሁሉም ማህበራዊ መሠረት ተገኝተው የሚሳተፉ መሆኑን አስረድተዋል።

አቶ አባስ አክለውም ሐምሌ 10 ከለሊቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በወረዳው በሁሉም ቀበሌያት ተከላው እንደሚካሄድ የገለፁ ሲሆን ይህም በተቋማት ፣ በግለሰብ ማሳ ፣ በወል መሬቶች ፣ በመንገድ ዳርና በሌሎች በተለዩ ቦታዎች ላይ የሚተከል መሆኑን አስታውቀዋል።

ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች አረንጓዴ አሻራን ለማሳረፍ ከወዲሁ ዝግጁ እንዲሆን ያሳሰቡ ሲሆን ወረዳችን በአረንጓዴ የለመለመች፣ አየር ንብረቷ ይበልጥ ተስማሚ እንድትሆን አድርጎ ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ሁሉም አሻራውን ማኖር እንደሚጠበቅበትና ሐምሌ10 ላይ በየአቅራቢያው በመገኘት አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ሐምሌና08/2015 ዓ.ም፤ የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት፤ ቂልጦ

20/04/2023

የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አብዱልሰመድ መሃመድ ለ1444ኛው የኢድ-አል-ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል !!

አቶ አብዱልሰመድ መሃመድ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮችና ለወረዳችን ነዋሪዎች በሙሉ እንኳን ለ1444ኛው የኢድ-አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ ታላቁንና የተከበረውን የረመዳን ወር እርስበርስ የመደጋገፍ የመተሳሰብና የመቻቻል እሴቶችን በማጎልበት ያለው የሌለውን እየረዳ በሰላም ማሳላፉን በዚህ ወቅት ጠቁመዋል ፡፡

መላው የወረዳችን ነዋሪዎች በረመዳን ወር እያዳበራቸው የመጡትን መልካም ዕሴቶች ከረመዳን ውጪ ባሉ ጊዜያትም አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ሲሉ በመልዕክታቸው አክለዋል፡፡

በዓሉን ስናከብር ያለንን ለሌላቸው በማከፋል፣ አቅመ ደካሞችን በመጠየቅና የተለመደውን እርስ በርስ የመረዳዳት ልምዳችንን በማጎልበት መሆን እንዳለበት አስታውሰዋል ፡፡

ሰላም የእስልምና እምነት መገለጫ ከሆኑ እሴቶች ዋነኛው በመሆኑ እንደ ማህበረሰብ በዓሉን ከማክበር ጎን ለጎን በተለያዩ አፍራሽ ሀይሎች ሊከሰቱ የሚችሉ ጸረ ሰላም እንቅስቃሴዎችን በንቃት የመጠበቅና የመከላከል ሚናችንንም በተገቢው መወጣት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት የመተሳሰብና የመተዛዘን በዓል እንዲሆን እመኛለሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ኢድ ሙባረክ!! ሚያዚያ፣12፤2015 ዓ.ም፤ የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያና ህዝቅ ግንኙነት፤ ቂልጦ

06/04/2023
22/03/2023

የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አብዱል ሰመድ መሀመድ 1444ኛው ታላቁ የረመዳን ወርን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ!!

=========መጋቢት 13/07/2015 ዓ.ም፤ቂልጦ=========

የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አብዱል ሰመድ መሀመድ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ በሙሉ እንኳን ለ1444ኛው የረመዳን ወር በሰላም አደረሳቹ!! አደረሰን!! በማለት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

አቶ አብዱልሰመድ በነገው ዕለት የሚጀመረውን ታላቁ የረመዳን ጾምን አስመልክተው ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እንደገለጹት የረመዳን ወር ከወትሮው በተለየ መልኩ ህዝበ ሙስሊሙ እርስ በዕርስ የሚደጋገፍበት የሚተሳሰብበትና ያለው ለሌለው የሚያካፍልበት ወር እንደመሆኑ መጠን መላው የወረዳችን ህብረተሰብ እነዚህን ተግባራት በመፈፀም ሊያሳልፍ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

አክለውም በታላቁ የረመዳን ወር የመደጋገፍ፣ የመዋደድ፣ የተቸገሩትን የመርዳት እንዲሁም የመተዛዘንና የይቅር ባይነት ዕሴቶቻችን ይበልጥ የምናጠናክርበት ወር በመሆኑ እነኚህ ማስፋት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የረመዳን ጾም በአመት አንድ ጊዜ በመጠበቅ የሚተገበር በመሆኑ እንኳን አደረሰን!! አደረሳችሁ በማለት የፍቅር፣ የመቻቻል፣የመተባበርና የመልካም የጸሎት ጊዜ እንዲሆንልን ዘንድ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ።

በድጋሚ እንኳን ለ1444ኛው ለታላቁ የረመዳን ወር በሰላም፤ በጤና አደረሳቹ!! አደረሰን!! ረመዳን ሙባረክ!!

12/01/2023

ግልጽና ውጤታማ የአመራር ምዘና ስርዓት መዘርጋትና መተግበር መቻል የጠራና የበቃ አመራርን ለመፍጠር ጉልህ አስተዋፅዖ ያለው ነው!

አቶ አብዱልሰመድ መሀመድ
የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ

ቀጥሎ የተጠቀሱትን ሊንኮች በመጫን ተጨማሪ መረጃዎችን ያገኛሉ!

በቴሌግራም👉 https://t.me/azernatqilto

ቀዩትዩብ👉 https://youtube.com/

በቲውተር👉 https://twitter.com/MisrakAzerntPP

በእንስታግራም👉 https://www.instagram.com/

20/12/2022

ተገኝቷል!!🙏 አልሃምዱሊላህ !!!🙏

ባለፈው በዚሁ የፌስቡክ ገጻችን ፖስት አድርገን ስናፈላልግ የነበረው ወንድማችን ሻፊ መሀመድ ካሊድ በሁላችንም ትብብር ተገኝቷል::

ህዳር 29/ 2015 ዓ.ም ከቤት ወጥቶ ጠፍቶ የነበረውና በማህበራዊ ሚዲያው በተለጠፈው ማፈላለጊያ ማስታወቂያ መሰረት ሁላችሁም ትብብር ያደረጋችሁለት በዱዓችሁም ያስታወሳችሁት ወንድማችን ሻፊ መሀመድ ካሊድ ተገኝቷል።

መልዕክቱን በማዳረስ በተለያየ መልኩ ለተባበራችሁን፣ ለተጨነቃችሁልንና በዱዓችሁ ጭምር ላገዛችሁን አካላት በሙሉ አላህ የከይር ስራ ምንዳችሁን ይክፈላችሁ! አላህ ያክብርልን ላቅ ያለ ምስጋናችንን ከትልቅ አክብሮት ጋር እንገልጻለን ብለዋል አባቱ መሀመድ ካሊድና መላው ቤተሰቦቹ !!

18/12/2022
18/12/2022
14/12/2022

የትምህርት ቤቶች ስታንዳርዳቸው የተጠበቀና ደረጃቸው የተሻሻለ መሆን ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ጉልህ አስተዋፅኦ ያለው ነው። ስለዚህ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የትምህርት ቤቶችን ስታንዳርድ ማሻሻልና ደረጃቸውን መጠበቅ ቀዳሚው ስራችን ነው።

ለዚህ ደግሞ ማህበረሰባችን እያሳየው ያለው የነቃ ተሳትፎ እጅግ ደስ የሚል፣የሚበረታታና የሚደገፍ ነው።ይህን ጠንካራ ተሳትፎ በመጠቀም የሚፈለገውን የትምህርት ብልጽግናን ማረጋገጥ ይጠበቃል!!

ወይዘሮ መህዲያ ቡሴር
የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ

11/12/2022

Address

Woraby
Addis Ababa

Telephone

+468991701

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Silte-Reporter's posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share