East Gojjam Zone ICT

East Gojjam Zone ICT Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from East Gojjam Zone ICT, Performance & Event Venue, East gojjam, Debra Markos.

18/06/2024
18/06/2024
Yidegulih Belulgn
18/06/2024

Yidegulih Belulgn

ክብር ለገበሬዎች
14/05/2024

ክብር ለገበሬዎች

01/05/2024

ኪራላይሶን [አቤቱ ማረን] '
ኪራላይሶን፡..ኪራላይሶን፡..ኪራላይሶን፡(3)
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን፡....አማኑኤል ጌታ፣
ኪራላይንሶ፡ ኪራላይሶን.....በጥፊ ተመታ፣
ኪራላይሶ፡ ኪራላይሶን.......አለምን ሊታደግ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶንን....ተነዳ እንደበግ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን.....አዳምን ሊፈውስ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን...... ቆመ ከጵላጦስ፣
ኪራላይሶን፡.....ኪራላይሶን፣...ኪራላይሶን፡(3)
ኪራላይንሶ ኪራላይሶን........እጁን ቸነከሩት፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶ.....አጥንቱን ቆጠሩት፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶንን..የእሾህ አክሊል ደፍቶ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን.........ገዳዩን እረቶ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን .......የሁላችን በደል፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን...ተሻረ በእርሱ ቁስል፣
ኪራላይሶን....ኪራላይሶን... ኪራላይሶን፡(3)
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን........እጣ ተጣጣሉ፣
ኪራላይሶን፡ኪራላይሶን........ልብሱን ተካፈሉ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን........ለፍርድ ተወሰደ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን ........እንደበግ ታረደ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን.....ለብሶ ከደም ሜዳ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶንን.......ተከፈለ እዳ፣
ኪራላይሶን.... ኪራላይሶን...... ኪራላይሶ፡ (3)
ኪራላይንሶ፡ ኪራላይሶን...ሆምጣጤ አጠጡት፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን......በገመድ ጎተቱት፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን......በወንበዴው ፈንታ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን........ተሰቀለ ጌታ፣
ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን......ሁሉም ዘበቱበት ኪራላይሶን፡ ኪራላይሶን......በዘላለም ሕይወት፣
ኪራላይሶን..... .ኪራላይሶን......ኪራላይሶን፡

01/05/2024

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
"ሰሞነ ህማማት "
✔Please ✔share ✔

ነው?
ሰሙነ ሕማማት ለምን ይታሰባል?
የሚከለከሉ ና የሚፈቀዱ ነገሮች ምንድን ናቸው? ለምን?
ሰሙነ ሕማማትን ከሌሎች የዐቢይ ጾም ሳምንታት ልዩ የሚያደርገው ሥርዓት አለ፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት ሥርዓትና ደንብ መሠረት በሰሙነ ሕማማት ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ቅዳሴ አይቀደስም፤ ስብሐተ ነግህ አይደርስም፤ ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይም፤ ጸሎተ አስተሥርዮም አይደረግም፡፡ እንዲሁም ጥምቀተ ክርስትናም አይፈጸምም፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት የቤተክርስቲያን ሥርዓቶች አስቀድሞ በዕለተ ሆሳዕና ይከናወናሉ፡፡
በተጨማሪም ማንኛውም ክብረ በዓል በዚህ ሳምንት ቢውል ከትንሣኤ በኋላ እንዲከበር ይተላለፋል፡፡ ይህ ብያኔ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት ዘንድ የጸና መንፈሳዊ ሥርዓት ነው፡፡

ሕማምና ሞት የማይገዛው ጌታችንኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን ሕማምና ሞትለራሱ በማድረግ በዚህ ሳምንትለእኛቤዛሆኗል፡፡‹ደዌያችንንተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ ከዐመጸኞችምጋር ተቆጠረ፡፡እርሱግን ግፍን አላደረገም ተንኮልም ከክፉ አልተገኘበትም፡፡› (ኢሳ.42 4-12) ተብሎ እንተጻፈ፡፡ ምእመናን ክርስቶስ የተቀበለውን የእኛን ሕማም መሆኑን በማዘክር በሰሙነ ሕማማት ከማንኛውም የሥጋ ሥራ መታቀብ በዋዛ ፈዛዛ ባለመነጋገር፤ በሐዘን ልናከብረው ይገባል፤ ብድራትን የማያስቀረው አምላክም መተላለፋችንና በደላችንን በመደምሰስ የመንግሥቱ ወራሽ ያደርገናልና፡፡
ሰሙና ሕማማት እስከ አራተኛው ምዕተ ዓመት ድረስ ከጾሙ ተለይቶ ለብቻው ይከበር ነበር፡፡ በኋላ ግን በባሕረ ሐሳብ ቀመር መሠረት ጾሙም ሕማማቱም ትንሣኤውም ተያይዘው እንዲከበሩ ተደረገ፡፡ ምዕራባውያን ከአርባ ጾም ውስጥ የመጨረሻውን ሳምንት ሰሙና ሕማማት ያደርጉታል፡፡ የምሥራቃውያን /ኦሪየንታል/ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት የሆን ግን አርባውን ጾም ጨርሰን ከኒቆዲሞስ በኋላ ያለውን ተከታዩን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት አድርገን እናከብራለን፡፡

"በህማማት የሚነሱ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው"
1. በህማማት ለምን መስቀል አንሳለምም ወይስ ለምን አናማትብም ?
የመስቀል ክብር እና ሐይል የታወቀው ጌታ በመስቀል ከተሰቀለ በሗላ ነው፡፡ በሰሞነ ህማማት ከሰኞ እስከ አርብ ያሉት ቀናት የአመተ ፍዳ መታሰቢያ ናቸው፡፡በነዚህ ዘመናት ሰዎች የመስቀልን አገልግሎት እንዳልጀመሩ ለማሳየት በሰሞነ ህማማት በቤተክርስቲያን ስርዓት መሰረት መስቀል መሳለምም ሆነ ማማተብ ስርዓት አይደለም፡፡ግን አነድ ሰዉ ተሳሰቶ ቢያማትብ ምንም በደልም ሐጢአትም አይሆንበትም።
2. በሰሞነ ህማማት ለምን አንሳሳምም?
ይሁዳ ጌታውን በመሳም አሳልፎ ሰጥቷል እኛ ግን እንደ ይሁዳ ክፋት ካለው መሳሳም መለየታችንን ለማስረዳት ከዚህም በተጨማሪ ሰላም በዘመነ ፍዳ እንዳልነበረ ለማሳየት በሰምነ ህማማት እስከ መሳሳም የደረሰ ጥብቅ ሰላምታ የለም፡፡
3. በሰሞነ ህማማት የማይደረጉ ሌሎች ነገሮች ምን ምን ናቸው? ማንኛውንም ለስጋ የሚያደሉ ተግባራትን መቀነስ እና ቢቻለን አብዛኛውን ጊዜያችንን የጌታን ህማም መከራ በማሰብ በፆም በፀሎት በስግደት ማሳለፍ ፤ቢቻል አመጋገባችንን ከወትሮው መቀነስ፤በትዳር ያሉ በፆም ወቅት በመኝታ ከመተዋወቅ መታቀብ አለባቸው፡፡
4.ታቦት ከመንበሩ አይነሳም ምንም የንግሰ በዓልም አይከበርም
5.ፍትሐት፣ክረሰትና የለም

6.ሰላምታ ያለባቸው ጸሎቶች ለምሳሌ መልክዓ ቅድሳን አይጸለይም ከሱ ይልቅ መዝሙረ ዳዊት ውዳሴ ማርያም ግብረ ሕማማት እና መጽሐፈ ማሕያዊ የተባለ ብዙ ቃልኪዳን ያለው የጌታን መከራ የሚያወሳ መጽሐፈ ጸሎት
ይነበባሉ

ሰሙነ ሕማማት ለምን ይታሰባል?
ሰሙነ ሕማማትን ከሌሎች የዐቢይ ጾም ሳምንታት ልዩ የሚያደርገው ሥርዓት አለ፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት ሥርዓትና ደንብ መሠረት በሰሙነ ሕማማት ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ቅዳሴ አይቀደስም፤ ስብሐተ ነግህ አይደርስም፤ ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይም፤ ጸሎተ አስተሥርዮም አይደረግም፡፡ እንዲሁም ጥምቀተ ክርስትናም አይፈጸምም፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት የቤተክርስቲያን ሥርዓቶች አስቀድሞ በዕለተ ሆሳዕና ይከናወናሉ፡፡
በተጨማሪም ማንኛውም ክብረ በዓል በዚህ ሳምንት ቢውል ከትንሣኤ በኋላ እንዲከበር ይተላለፋል፡፡ ይህ ብያኔ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት ዘንድ የጸና መንፈሳዊ ሥርዓት ነው፡፡

ሕማምና ሞት የማይገዛው ጌታችንኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን ሕማምና ሞትለራሱ በማድረግ በዚህ ሳምንትለእኛቤዛሆኗል፡፡‹ደዌያችንንተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ ከዐመጸኞችምጋር ተቆጠረ፡፡እርሱግን ግፍን አላደረገም ተንኮልም ከክፉ አልተገኘበትም፡፡› (ኢሳ.42 4-12) ተብሎ እንተጻፈ፡፡ ምእመናን ክርስቶስ የተቀበለውን የእኛን ሕማም መሆኑን በማዘክር በሰሙነ ሕማማት ከማንኛውም የሥጋ ሥራ መታቀብ በዋዛ ፈዛዛ ባለመነጋገር፤ በሐዘን ልናከብረው ይገባል፤ ብድራትን የማያስቀረው አምላክም መተላለፋችንና በደላችንን በመደምሰስ የመንግሥቱ ወራሽ ያደርገናልና፡፡
ሰሙና ሕማማት እስከ አራተኛው ምዕተ ዓመት ድረስ ከጾሙ ተለይቶ ለብቻው ይከበር ነበር፡፡ በኋላ ግን በባሕረ ሐሳብ ቀመር መሠረት ጾሙም ሕማማቱም ትንሣኤውም ተያይዘው እንዲከበሩ ተደረገ፡፡ ምዕራባውያን ከአርባ ጾም ውስጥ የመጨረሻውን ሳምንት ሰሙና ሕማማት ያደርጉታል፡፡ የምሥራቃውያን /ኦሪየንታል/ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት የሆን ግን አርባውን ጾም ጨርሰን ከኒቆዲሞስ በኋላ ያለውን ተከታዩን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት አድርገን እናከብራለን፡፡

በሰሙነ ህማማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ
የተከናወኑትን ተግባራት
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
† #ሰኞ
~~~
ጌታችን ከቢታንያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን
በለስ ከሩቁ አይቶ በለሲቱን ቀረባት ነገር ግን
ከቅጠል በቀር ምንም አልተገኘባትም ከአሁን
ጀምሮ ማንም ከ አንች ፍሬን አይብላ ብሎ
እረገማት በለስ የተባሉ እስራኤላዊያን ናቸዉ፡፡..............
† #ማክሰኞ
~~~
ሻጮች እና ለዋጮችን ከቤተ
መቅደስ ባሶጣ ጊዜ ይኼንን በማን ኃይል
እንዳደረገዉ የአይሁድ መምህራን ጠይቀዉት
ነበር ማቴ 21-23
ስለሆነም የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡..............
† #ረቡዕ
~~~
ምክረ አይሁድ ይባላል ምክንያቱም የአይሁድ
ሊቃነ ካህናት እና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ
እንዳለባቸዉ ምክር ያጠናቀቁበት ቀን በመሆኑ..............
† #ሐሙስ
~~~
በቤተ ክርስቲያን የተለያየ
ስያሜዎች ያሏቸዉ በርካታ ድርጊቶች
የተፈጸሙበት ነዉ፡፡
|ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡
መድኃኒዓለም ክርስቶስ አይሁድ መጥተዉ
እስኪይዙት
ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ነዉና ጸሎተ ሐሙስ
ተባለ
|ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር
ጎንበስ
ብሎ በታላቅ ትህትና አጥቧልና
|የሚስጢር ቀን ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የሆነዉን ምስጢረ
ቁርባን በዚህ ዕለት ተመስርቷልና
|የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡-
ምክንያቱም የ ኦሪት መስዋዕት የሆነዉ
የእንስሳት ደም ማብቃቱን ገልጦ ለድህነተ
ዓለም ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ
ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ
|የነፃነት ሐሙስ ይባላል፡-
ምክንያቱም ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ
መሆኑ ማብቃቱና የሰዉ ልጅ ያጣዉን ክብር
መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን
ስ� #ዓርብ ፡-
~~~
ጌታችን ከ ጲላጦስ አደባባይ እስከ ሊጦስጥራ
የተንገላታበት ለአዳምና ለልጆቹ በምልዕልተ
መስቀል ለሞት እራሱን አሳልፎ የሰጠበት ቀን
ነዉ፡፡..............
† #ቅዳሜ ፡-
~~~
|በዚች ዕለት የጌታችን መከራ
በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትዉል ቅዳም
ሥዑር ወይም የተሻረችዉ ቅዳሜ
ትባላለች፡፡
|ካህናቱም ለምዕመናን ለምለም ቄጤማን
የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ ለምለም ቅዳሜም
ትባላለች፡፡
|እንደዚሁም ልዑል
እግዚአብሔር በዚህ ቀን 22ቱን ስነ ፍጥረታት
ፈጥሮ ከስራዉ ያረፈበት ዕለት በመሆኑ ቅ/
ቅዳሜ ይባላል፡፡
ከህማሙ ከመከራው በረከት ያሳፈን!!
በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸሙ ሥርዓቶች

1.ስግደት:-በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል::
2. ጸሎት:- በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው::
በነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ::
3.ጾም:-በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት /አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች/ አይበሉም:: በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል::
4.አለመሳሳም:-አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም:: መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ. 3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29
5.አክፍሎት:-እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው::
6.ጉልባን:-ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው::
7.ጥብጠባ:-ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው:: ይህም የጌታ ምሳሌ ነው::
8.ቄጠማ:-ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን::

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም
ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም::

18/03/2022

በጋን የተሞላዉ ጸበል ዚላን ዘርዓብሩክ
*************************
የዚላን ዘርዓብሩክ ቤተክርስትያን በምስራቅ ጎጃም ዞን ስናን ወረዳ የሚገኝ ሲሆን በፈዋሽ ጸበሉ ይታወቃል፡፡ የጸበሉ ታሪካዊ ዳራም እንደሚከተለው ነው፡፤

የዚላን ዘርዓብሩክ ፀበል በምስራቅ ጎጃም ዞን በስናን ወረዳ በዚላን ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከወረዳዋ ዋና ከተማ ረቡዕ-ገበያ በስተምስራቅ አቅጣጫ በግምት 12 ኪ.ሜ አካባቢ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ወደ ፀበሉ ቦታ ለመድረስ ከረቡዕ-ገበያ ዋሻ ሚካኤል ቀበሌ በሚወስደው የጠጠር መንገድ በመታገዝ ያለምንም ችግር ከቦታው መድረስ ይቻላል፡፡

ፀበሉ በስንተኛው ክፍለ ዘመን እንደተተከለ ባይታወቅም ብዙዎቹ የሚስማሙበት ግን አቡነ ዘርዓቡርክ ከግሽ አባይ መጥተው ከቦታው ላይ ከፀለዩበት በኋላ እንደተጀመረ ያስረዳሉ፡፡ ዚላን ዘርዓብሩክ የተመሰረተችው በአፄ ሲሲኒዮስ ዘመነ መንግስት ሲሆን በወቅቱ ታቦተ ህጉን ወደ ቦታው ያመጡት ቄስ ብሉሌ የሚባሉ ሲሆኑ ከእርሳቸው ጋር አብሮ የነበረ ጨዋ ሰው ደግሞ አቶ ጎጃሙ ይባሉ እንደነበር ይነገራል፡፡

በዚህ አካባቢ በድሮ ጊዜ እጅግ ከፍተኛ ጫካ የበዛበት ቦታ በመሆኑና ሰዎቹ ወደ ቦታው መጥተው በሚያዩበት ጊዜ ደን የበዛበትና ዘላን ይኖርበት ይመስል ስለነበር እንዲሁም የከብት መሳደጃ በመሆኑና በቦታው ሰዎች ስለማይኖሩበት ከዚህ ጋር አገናኝተው ስሙን እንዳወጡለት ይነገራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አቡነ-ዘርዓብሩክ ከግሽ አባይ ተነስተው ወደ ቦታው በሚመጡበት ወቅት ይህች ሀገር የገዳም ሀገር ትመስላለች ብለው አሁን ፀበሉ በሚገኝበት አካባቢ እንደፀለዩበት አባቶች ያስረዳሉ፡፡

እንደ አባቶች ገለፃ ከሆነ አቡነ- ዘርዓብሩክ በፀለዩበት ቦታ ላይ ከምን እንደመጡ ሳይታወቁ ከፀበሉ አናት ላይ ሦስት ጋኖች እንደተገኙና ከነዚህም ውስጥ አቡነ- ዘርዓብሩክ ሁለቱ ለሰው እይታ እንደማይገቡና /እንዳልተፈቀዱ/ ነገር ግን እነዚህ ጋኖች በስውር እንዲሰሩ ያዘዙ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ከሻንዳ ፀበሉ በላይ ወደ ውስጥ እንደጠለቁ/እንደሰረጉ/ እና ለሻንዳ ፀበሉ እንደምንጭ እንደሚያገለግሉ አባቶች ያስረዳሉ፡፡

ነገር ግን አንዱ ጋን በወቅቱም ሆነ በአሁኑ ሰዓት በግልፅ በሚታይ ቦታ የሚገኝ ሲሆን አባቶች እንደሚያስረዱት ይህ ጋን ለሰው ግልፅ እንዲሆንና ህዝብ እንዲጠቀምበት የተፈቀደ እንዲሁም የማይደርቅ የማይነጥፍ ይሁን ተብሎ እንደታዘዘ ይናገራሉ፡፡

በዚህ ቦታም ታላላቅ ሰዎች ከተለያዩ ስፍራዎች እየመጡ ይጠመቁበት እንደነበር ይነገራል፡፡ ለምሳሌ፡- በአፄ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት የራስ ሃይሉ ልጅ የሆነችው ሙሉ ሀይሉ በቦታው ድንኴን ተክላ እንደተጠመቀችና ከቦታውም ከህመሟ ተፈውሳ እንደሄደች አባቶች ያስረዳሉ፡፡

በሌላ በኩል በአፈ-ታሪክ አባቶች ሲያስረዱ አንድ መነሱሴ ለአቡነ- ዘርዓብሩክ የሚቀዳበት ሸክላ ከውሀ ጋር በስጦታ እንደሰጠቻቸውና አቡነ-ዘርዓብሩክ ጋኑን ውሀ ሞልተው አንድ ክንድ የሚሆን አስቀርተው መሬት ውስጥ ካስቀመጡ በኋላ ለፀበልነት እንዲሆን እንደፀለዩበት እና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ፀበሉ ለተለያዩ በሽተኞችን እንደሚፈውስ በተለይ ቁስል ነክ የሆነ ህመምን በይበልጥ እንደሚፈውስ አባቶች ያስረዳሉ፡፡

በጋን የተሞላ ፀበል፤

ይህ ፀበል በስናን ወረዳ በዚላን ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን ይህን ፀበል ድንቅ የሚያሰኘው ነገር ጋኑ የማያፈስ መሆኑ ሲሆን ፀበሉን ቢጠልቁለት አለመጉደሉ እንዲሁም ለቀናት ሳይጠልቁለት ቢቆይ ሞልቶ አለመፍሰሱ ነው፡፡ ይህም አቡነ-ዘርዓብሩክ ሞልተው እንዳስቀመጡት ይታመናል፡፡ ፀበሉ በግንብ ከለላ ተደርጐለት የሚገኝ ሲሆን ከአመት ሁለት ጊዜ ጥቅምት 13 እና ጥር 13 ይከፈታል፡፡ በአቡነ-ዘርዓብሩክ ክብረ-በዓል ለበዓሉ ድምቀትና ፈውስ ፍለጋ ከተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ረ/ገበያን ጨምሮ የሚመጡ ህሙማን ይፈወሳል፡፡ ከነዚህ ቀናት ውጭ ተገልጋዮች ከዚህ ፀበል ራቅ ያለ በቧንቧ የሚወርድ ፀበል በመጠቀም ከተለያየ ቦታ የመጡ በሽተኛዎች በመፈወስ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ፡፡

#ምስራቅ ጎጃምን ይጎብኙ

Address

East Gojjam
Debra Markos

Telephone

0922261405

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when East Gojjam Zone ICT posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share